ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


🇪🇹🇪🇹🇪🇹ስለ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀን በቀን የሚወጡ ዜናዎችን እና እንዲሁም አለም አቀፍ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን 🙏ሰላምና ፍቅር ለእናት ሀገራችን ይሁን❤
👉 ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @Gebrel or @Wizbeki7 ያናግሩን።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


🚨🚨 የ125 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ




🚨TVTI_Exit_Exam

የመውጫ ፈተና የምትወስዱ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች በኦንላይን ምዝገባ አድርጉ!

ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫኑ የምታገኙትን ቅፅ በመሙላት ምዝገባ ያድርጉ 👇
https://forms.office.com/r/3KgnK1esuc

ኦንላይን መመዝገብ የማትችሉ በዋናው ግቢ በአካል በመገኘት በየትምህርት ክፍላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦
የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የምትወስዱ ተፈታኞች ፈተናው በኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ እና በአዲስ አበባ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

የመዝገባ ብር 500 በኢንስቲትዩቱ የንግድ ባንክ አካውንት በማስገባት ክፍያ በመፈፀም ደረሰኝ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

የምዝገባ ጥሪው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጋርመንት ቴክኖሎጂ ሰልጣኞችንም ይመለከታል።

የመውጫ ፈተናው ከመጋቢት 6-11/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

@ethiobestzena🤩


ባለፈው ሳምንት ከተሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የ Comprehensive Nursing ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አቅርበዋል፡፡

ፈተናው ከBlue Print ውጪ መዘጋጀቱን እንዲሁም የጥያቄ መደጋገም መኖሩን የገለፁት ተፈታኞቹ፤ ትምህርት ሚኒስትር ቅሬታቸውን በማየት በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ከነርሲንግ ተማሪዎች ጋር ተያይዞ የትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡ ቲክቫህ ጥያቄውን ለሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ያቀረበ ሲሆን፤ የሚሰጡንን ምላሽ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል "ፈተናዎቹ ዘግይተው መሰጠት በመጀመራቸው የሰዓት ዕጥረት እንዲፈጠር ማድረጉ" እንዲሁም "የኔትወርክ እና የመብራት መቆራራጥ ችግሮች" ሌሎች በፈተናው ወቅት የታዩ ችግሮች እንደነበሩ ተፈታኝ ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ገልፀዋል፡፡

እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያሉ የተከለከሉ ነገሮችን ወደ ፈተና ጣቢያ ይዞ ለመገባት መሞከር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ማጋጠሙን መግለፃችን ይታወሳል፡፡

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሞባይል ስልክ ሲጠቀሙ የተያዙ እና በመፈተኛ ክፍሎች ሞባይል ስልኮችን ይዘው የተገኙ 128 ተማሪዎችን ከፈተና ማዕከሉ እንዲሰናበቱ ማድረጉንና ውጤታቸው እንዲሰረዝ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

📷፦ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ

@ethiobestzena🤩


#መቄዶንያ

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው !

ትላንት የካቲት 1/2017 ዓ/ም በጀመረው የመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እስኩን 120,000,000 ብር ተሰብስቧል።

መቄዶንያ በሚያስገነባው ሆስፒታል ጭምር ያለው ህንፃ ለማጠናቀቅ የገንዘብ እጥረት አጋጥሞታል። ህንፃው ለማጠናቀቅ ገንዘብ ተቸግረናል። ለማጠናቀቅ ወደ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል።

በቀጥታ ይከታተሉ 👇
https://www.youtube.com/live/q0bMjwt9PvM?feature=shared

የምትችሉትን ሁሉ ድጋፍ አድርጉ።


🚨" የመክፈያ ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብራችሁን ያልከፈላችሁ እንድትከፍሉ እናሳስባለን " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ " በተለመዶ የጣራና ግድግዳ ግብር እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩን ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ እንድትከፍሉ እናሳስባለን " ብሏል።

በዚሁ መግለጫው ግብሩ የከተማ ቦታና ቤት ግብር በከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 መሰረት የሚሰበሰብ ግብር መሆኑ መገንዘብ እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን 429 ሺህ 829 ግብርከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል ብሏል።

የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " ግብር ከፋይ ነዋሪዎች ያለቅጣት መክፈያው ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከየካቲት 30 በፊት እንዲከፍሉ እና ያልከፈሉ ነዋሪዎች ግን ቅጣቱን ከነወለዱ ለመክፈል እንደሚገደዱ " ገልጸዋል።

አቶ ሰውነት " እናት ፓርቲ ካስተላለፈው መልእክት ጋር በተያያዘ እኛን የሚመለከተን ነገር የለም " ያሉ ሲሆን ለቢሮው የደረሰው ምንም አይነት የፍርድ ቤት እግድም ሆነ መመሪያ አለመኖሩን በመግለጽ " ሰው ጋር መዘናጋት ይታያል ይህ ደግሞ ለቅጣት ሊዳርጋቸው ይችላል በቀረው ጊዜ ክፍያችሁን ፈጽሙ " ሲሉ አሳስበዋል።


ከደረጃ በታች የሆኑ ስስ የፌስታል ምርቶች እንዳይመረቱ መከልከሉን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ውስጥ የፕላስቲክ ከረጢት ወይም "ፌስታል" በሚል የሚታወቁ የፋብሪካ ምርቶችን መጠቀም፣ ማምረት ብሎም ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን የሚከለክል ረቂቅ ሕግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወቃል።

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የፕላስቲክ ምርቶች በአካባቢ ላይ ብሎም በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ብዙ በመሆኑ ስስ የፌስታል ምርቶች እንዳይመረቱ መከልከሉን ገልጿል።

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ቡድን መሪ ሰናይት ተስፋዬ፤ የፕላስቲክ ምርቶች በአፈር ውስጥ ተቅበረው በመቶ ዓመታት የማይበሰብሱ ከመሆናቸው ባሻገር በአፈር ውስጥ በቂ አየር እንዳይዘዋወር እና ምርት እንዳይኖር የሚያድጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

እንዲሁም በፕላስቲክ ምርቶች ውስጥ የሚገኘው 'ፒቢሲ' የተሰኘው ንጥረ ነገር በጥናት ባይረጋገጥም ሙቀት ሲነካው በመትነን ዜጎችን ለካንሰር በሽታ የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 

የፕላስቲክ ምርቶች የሚያደርሱት ጉዳት በተመለከተ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ  በሰፊ ንቅናቄ እየሰራበት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ "የውፍረት መጠናቸው ከፍ ያለ ረዘም ላለ ጊዜ ማገልገል የሚችሉ የፕላስቲክ ምርቶች እንዲመረቱ እየተደረገ ነው" ብለዋል፡፡

በዚህ መስፈርት ለመስራት በርካታ ፈቃድ የጠየቁ አምራቾች መኖራቸውን አንስተው፤ ከተቀመጠው የፕላስቲክ ደረጃ በታች ያመረቱ በርካታ ፋብሪካዎች መዘጋታቸውን እና ደረጃውን ጠብቀው እንዲያመርቱ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።


በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለ108 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማጎልበቻ ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጥቷል።

ተማሪዎቹ ከአርባ ምንጭ፣ መቐለ እና ድሬዳዋ ከተሞች የተውጣጡ ናቸው።

English Access Scholarship የተሰኘው ፕሮግራሙ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በትምህርታቸው ስኬታማ እንዲሆኑና ወደፊት የስኮላርሺፕ ዕድሎችን ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ክህሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።

ተማሪዎቹ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠና፣ ዓለም አቀፍ ዜግነት እንዲሁም የአሜሪካ ባህልና ዕሴቶች ላይ ስልጠና እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ስልጠናው የተማሪዎቹን የተግባቦት፣ ትብብር እና መሪነት ክህሎቶች በሚያጎለብት መልኩ ይሰጣል ተብሏል።


Репост из: ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ ተጠባቂ ጨዋታ

09:15 | ለይተን ኦሪየንት ከ ማንችስተር ሲቲ
12:00 | ኤቨርተን ከ በርንማውዝ
02:45 | ቤርንግሃም ከ ኒውካስትል
05:00 | ብራይተን ከ ቼልሲ

🇪🇹በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

09:00 | ኢትዮጵያ ቡና ከ መቻል
12:00 | ሀድያ ሆሳዕና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

🇪🇸በስፔን ላሊጋ

10:00 | ሴልታ ቪጎ ከ ሪያል ቤቲስ
12:15 | አትሌቲክ ቢልባኦ ከ ጅሮና
02:30 | ላስ ፓልማስ ከ ቪያሪያል
05:00 | ሪያል ማድሪድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

🇩🇪በጀርመን ቡንደስሊጋ

11:30 | ዶርትሙንድ ከ ስቱትጋርት
11:30 | ፍራይበርግ ከ ሃይደናይም
11:30 | ሆፈናየም ከ ዩኒየን በርሊን
11:30 | ሜንዝ ከ ኦግስበርግ
11:30 | ወልቭስበርግ ከ ባየር ሌቨርኩሰን
02:30 | ሞንቼግላድባህ ከ ፍራንክፈርት

🇮🇹በጣሊያን ሴሪ ኤ

11:00 | ቬሮና ከ አታላንታ
02:00 | ኢምፖሊ ከ ኤሲ ሚላን
04:45 | ቶሪኖ ከ ጀኖዋ

🇫🇷በፈረንሳይ ሊግ 1

01:00 | ኒስ ከ ሌንስ
03:00 | ሊል ከ ሌ ሃቬር

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


Репост из: ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ትላንት የተደረጉ ጨዋታዎች

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ

ማንችስተር ዩናይትድ 2-1 ሌስተር ሲቲ

🇪🇹በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

አዳማ ከተማ 0-0 ሲዳማ ቡና
ሽሬ እንደስላሴ 1-0 ወልዋሎ አዲግራት

🇪🇸በስፔን ላሊጋ

ራዮ ቫልካኖ 1-0 ቫላዶሊድ

🇩🇪በጀርመን ቡንደስሊጋ

ባየር ሙኒክ 3-0 ቨርደር ብሬመን

🇮🇹በጣሊያን ሴሪ ኤ

ጁቬንቱስ 2-1 ኮሞ

🇫🇷በፈረንሳይ ሊግ 1

ናንትስ 0-2 ብረስት
ፒኤስጂ 4-1 ሞናኮ

🇸🇦በሳውዲ ፕሮ ሊግ

አል ናስር 3-0 አል ፍሃ

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


በክረምት መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ መምህራን የመውጫ ምዘና ነገ ቅዳሜ የካቲት 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በክረምት መርሐግብር ለተከታታሉ መምህራን የመውጫ ምዘና እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

ወደ መፈተኛ ማዕከል ስትሔዱ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ መያዝ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያሉ የተከለከሉ ነገሮች ይዞ ወደ ፈተና ማዕከል መሔድ አይቻልም፡፡ ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ ቀድማችሁ ልትገኙ ይገባል፡፡


🚨ነዳጅ

የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።

የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

▶️ አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር

▶️ አንድ ሊትር ናፍጣ 98.98 ብር

▶️ አንድ ሊትር ኬሮሲን 98.98 ብር

▶️ የአውሮፕላን ነዳጅ 109.56 ብር

▶️ አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 105.97 ብር

▶️ አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 108.30 ብር


🚨ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ተወሰነ።

ከዚህ ቀደም የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑ ተገልጾ ነበር።

በዚህ መሰረት ቁጥራቸው 88,717 የሆኑ ግብር ከፋዮች የህትመት ጥያቄ ማቅረብ መቻላቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ገልጸዋል፡፡

ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ጥያቄያቸውን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸው ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም በውይይቱ ተወስኗል፡፡

እስከ አሁን ድርስ የህትምት ጥያቄ ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የህትምት ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተባለ ሲሆን የሲስተም መጨናነቅ እንዳይፈጠር የሲስተም ማሻሻያዎችን ማከናውን፣ የህትመት እና ስርጭት ተግባራት በሚፈለገው ደረጃ ለማከናወን ተጨማሪ የህትመት ማሽኖችን ወደ ስራ ማስገባት እና አትሞ በፍጥነት ማሰራጨት እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።


በአሜሪካ አላስካ ግዛት10 ሰዎችን የጫነ አውሮፕላን መጥፋቱ ተገለፀ።

የቤሪንግ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ሴስና ካራቫን አውሮፕላን አናላክሌት ከተባለ አካባቢ ወደ ኖም እያቀና ሳለ መጥፋቱ ነው የተገለፀው።

አውሮፕላኑ 9 ሰዎችን ያሳፈረ ሲሆን፤ በ1 ፓይለት አብራሪነት እየተጓዘ እንደነበረም ተጠቁሟል።

የአየር መንገዱ ባለሙያዎች ከአብራሪው ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጉት የመረጃ ልውውጥ አብራሪው የማረፊያ ቦታ እስኪስተካከል አየር ላይ ለመቆየት መወሰኑን ሲያሳውቅ ነው ተብሏል። ይህም ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ነበር። እስከ አሁን የጠፋውን አውሮፕላን ለማግኘት በአየር እና በምድር አሰሳ እየተደረገ ይገኛል።

የአላስካ ግዛት ባላት ከባድ የአየር ንብረት ሳቢያ በርካታ አውሮፕላኖች የተሰወሩባት አካባቢ መሆኗ ይነገራል።


ከጋራ መኖሪያ ብሎኩም የተጠቀመ ቢኖር ለይቶ እነሱን ተጠያቂ ማድረግ የአገልግሎቱ ሃላፊነት ነው ሁሉም ባላጠፋው ለወር ያህል ነዋሪው ለምን ይቀጣል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

አገልግሎቱም በምላሹ " ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን መረጃ ከእናንተ እንፈልጋለን " ቢልም ነዋሪዎች ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ በመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሪጅኑ ዳይሬክተር በቦታው በተገኙበት ወቅት ለነዋሪዎች መፍትሔ ለመስጠት ሃይሉን እንዲቀጠልላቸው ያደረጉ ሲሆን ለህገ ወጥ ድርጊት ምክንያት የተባለውን ቆጣሪም ከቦታው እንዲነሳ አድርገዋል።

ዳይሬክተሩ አቶ ብርሃኑ ሲጠቀሙ የነበሩትን አካላት ማንነት ከነዋሪዎቹ ወይም ኮሚቴዎቹ ማግኘት እንደሚፈልጉ እና በጊዜ ሂደት ማንነታቸውን የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ ሃይሉ በድጋሚ እንዲቀጠል በተደረገበት ወቅት በብሎኩ ካሉ ሁለት ቆጣሪዎች ለመታዘብ እንደተቻለው 1,500 ብር የተሞላው በ19/02/17 ዓ/ም የነበረ ቢሆንም ሃይል እስከተቋረጠበት 15/04/17 ዓም ድረስ ባለው ሁለት ወር ውስጥ ከካርዱ ጥቃም ላይ የዋለው ከ 10 ብር በታች ሆኖ ተገኝቷል።

" ቆጣሪው ሲገናኝ ያሳየው የብር መጠን 1,492. 5  አና 1,455.32 ብር ነው ይህ ማለት በ2 ወር ጊዜ ውስጥ የተጠቀሙት ከ10 ብር በታች ነው ይህ ሁሉ ህብረተሰብ በ10 ብር 2 ወር ሊጠቀም አይችልም ያማለት ቀጥታ ሲጠቀሙ እንደነበር ተጨባጭ ማስረጃ ነው " ሲሉ አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።

በብሎኮች በመዟዟር በተደረገው ምልከታ በቀጥታ ያለቆጣሪ ከመስመር ላይ በመቀጠል ሃይል የሚጠቀሙ ሰዎች ስለመኖራቸው ለመታዘዘብ ተችሏል።


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት " በህገ-ወጥ መንገድ ቆጣሪን እንዳይቆጥር በማድረግ ሃይል ሲጠቀሙ እንደነበር ደርሼበታለሁ " በማለት ሃይል ካቋረጠባቸው አራት ብሎኮች ውስጥ ሁለቱ ማለትም ብሎክ 550 እና 551 ሃይል ተቀጥሎላቸው አገልግሎት እያገኙ ነበር።

የእነዚህ ቆጣሪዎች እዳ ባልተከፈለበት እና ከሌሎች ብሎኮች ጋር በጋራ ሃይል በተቋረጠበት ሁኔታ ለእነርሱ በማን እና በምን ሁኔታ ተቀጠለ ? የሚል ጥያቄ ለሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ዳይሬክተሩም ፤ የቆጣሪዎቹ እዳ ባልተከፈለበት ሁኔታ የእነሱ ሃይል መጠቀም ከእርሳቸው እውቅና ውጪ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተቋረጠ በኃላ በራሳቸው ሃይሉን ቀጥለው ይጠቀሙ ወይስ የአገልግሎቱ ሰው ቀጠለላቸው የሚለውን ጉዳይ ማጣራት በማድረግ " አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

በመቀጠለም ምልከታ የተደረገው ብሎክ 534 እና 535 ላይ ሲሆን እነዚህ ብሎኮች " ሃይል በህገ ወጥ መንገድ ቀጥለው ሲጠቀሙ በኢንስፔክሽን ወቅት ተገኝተዋል " በሚል ሃይል ከተቋረጠባቸው ወር እንዳለፋቸው ተናግረዋል።

አገልግሎት በበኩሉ " ሃይሉን ያቋረጥኩት ከጋራ መኖሪያ መንደሩ ነዋሪዎች ለአንድ ዓመት ከአራት ወር በላይ ቀጥዬ ተጠቅሚያለው ያሉ እና የሚጠቀምም ስለመኖሩ በደረሰኝ ጥቆማ መሰረት ነው " ብሏል።

ነዋሪዎች ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ቀጥለው አለመጠቀማቸውን ተከራክረዋል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሞያዎች ግን የቆጣሪውን ሃይል ባቋረጡበት ወቅት እነዚህ ብሎኮች መጨለማቸውን እንደማስረጃ በመጥቀስ ሃይል በህገወጥ መንገድ እየተጠቀሙ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል።

" ሃይል የተቋረጠብን ለብሎካችን የገባው ስሪ ፌዝ ቆጣሪ በመቆረጡ እንጂ ከተጠቀሰው ቆጣሪ ላይ ሃይል አልቀጠልንም " ሲሉ የተከራከሩት ነዋሪዎች " ቆጣሪው መንገድ ላይ ያለ በመሆኑ ማንም ሰው እየቀጠለ ይጠቀማል ሌሎች በተጠቀሙት እኛ ልንጠየቅ አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።


➡️ " ቆጣሪው መንገድ ላይ ያለ በመሆኑ ማንም ሰው እየቀጠለ ይጠቀማል ሌሎች በተጠቀሙት እኛ ልንጠየቅ አይገባም " -ነዋሪዎች

🔴 " ከእነዚህ ቆጣሪዎች ሃይል ሲጠቀሙ የነበሩ ሰዎችን መረጃ ከእናንተ እንፈልጋለን " -የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በቦሌ አራብሳ ሳይት 3 ብሎክ 534 እና 535 ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር የገቡበትን ውዝግብ በሚመለከት የአገልግሎቱ የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኦልጅራ በአካባቢው በመገኘት እውነታውን መመልከት እንደሚቻል ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ያለውን እውነታ ለመመልከት እና ቅሬታውን ለመፍታት ከቀናት በፊት የአገልግሎቱ የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ዳይሬክተር ፣ የሪጅኑ የህግ ክፍል፣ የጸጥታ አካላት እና ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ምልከታ ተደርጓል።

በምልከታው ወቅትም የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብም በቦታው በመገኘት ከአገልግሎቱ ሃላፊዎች እና ነዋሪዎች እውነታውን ለመመልከት ጥረት አድርጓል።

አገልግሎቱ በአራብሳ የጋራ መኖሪያ መንደር ሳይት ሶስት ሃይልን ከቆጣሪ ላይ በህገወጥ መንገድ ቀጥለው ሲጠቀሙ እንደተደረሰባቸው በመግለጽ የቆጣሪውን እዳ እንዲከፍሉ በማሳወቅ ሃይል ያቋረጠባቸው ብሎኮች 534፣ 535፣ 550 እና 551 ናቸው።


" ከግምገማ በኋላ በደረስንበት ውጤት ነዋሪዎቹ መቶ በመቶ ጥፋተኞች ናቸው " - የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ለኮንስትራክሽን ሥራ በገቡ እና እንዲነሱ ባልተደረጉ ቆጣሪዎች ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ከእነዚህ ቆጣሪዎች በህገወጥ መንገድ ሃይል እንዲጠቀሙ ምክንያት ሆኗል መባሉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተመዘገቡት ቆጣሪዎች አማካኝነት በጋራ መኖሪያ መንደሩ በሚኖሩ ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ አገልግሎት ላይ የዋለ ከ400 ሺህ ብር በላይ እዳ ተመዝግቧል " ይከፈለኝ " ሲል በተደጋጋሚ ኮርፖሬሽኑን በደብዳቤ መጠየቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቆ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን ምላሽ ጠይቋል።

ኮርፖሬሽኑ ጥፋቱ ያለው ነዋሪዎች ጋር ነው ብሏል።

" በህገ ወጥ መልኩ ቀጥለው ለምን ጸጥ ብለው ይጠቀማሉ ?  " ሲልም ጠይቋል። ' እንዳይቆጥር አድርገው ቀጥለው ሃይል ተጠቅመዋል ለገንዘቡም ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉት እነርሱ ናቸው " ሲል መልሷል።

ጉዳዩን በተመለከተ ግምገማ መደረጉ የገለጸው ኮርፖሬሽኑ " በደረስንበት ውጤት ነዋሪዎቹ መቶ በመቶ ጥፋተኞች ናቸው በቅርቡ የነዋሪ ኮሚቴን፣ ኮንትራክተሮችን ጠርተን የጠራ ነገር እንይዛለን " ሲል አሳውቋል።


🚨USA

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።

ትራምፕ " በአሜሪካ እና የቅርብ አጋሯ እስራኤል ላይ ቅቡለነት እና መሠረት የሌለው ተግባር እየፈጸመ ነው " ሲሉ የከሰሱትን የዓለም አቀፉ የጦር የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ላይ ማዕቀብ የጣሉበት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ላይ ፈርመዋል።

ትራምፕ ICC ላይ የጣሉት ዕቀባ እና ቪዛን የሚያጠቃልል ነው።

የቪዛ ዕቀባው የአሜሪካ ወይም የአጋሯቿ ዜጎች ላይ ምርመራ የሚያደረጉትንና የሚረዱ ግለሰቦች እና ቤተሰቦቻችን ዒላማ ያደረገ ነው።

ታራምፕ ይህንን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የፈረሙት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ዋሽንግተንን እየጎበኙ ባሉበት ወቅት ነው።

ባለፈው ጥቅምት ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ኔታኒያሁ በጋዛ ፈጽመውታል ባለው የጦር ወንጀል ምክንያት የእስር ትዕዛዝ አውጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

አሜሪካ የዚህ ዓለም አቀፍ ተቋም አባል አይደለችም። በተደጋጋሚም በአሜሪካ ዜጎች ላይ በፍርድ ቤቱ የሚተላለፍ ውሳኔዎችን ውድቅ ማድረጓን ቢቢሲ ዘግቧል።

Показано 20 последних публикаций.