👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻 ክፍል - ዘጠኝ [፱] የመጨረሻ ክፍል !
✍ (በጥላሁን ተስፋዬ).
.
.
ይህቺ ጉዷ እማያልቅ አሜሪካን ፎርጅድ ሚሽት ድራለት ነዋ ቲለኝ ግር አለኝ
ፎርጅድ ፎርጅድ ደግሞ ምን ማለት ነው እሱ? ትለው ሳቀብይ••••
ምን ያስቅሀል አንተው አለማወቅ ሀጥያት አይደለ! ባእድ ቋንቋ ቀላቅለህ ትታበቃ እኔ ላይ መሳቅ ምን ይሉታል በል ይልቅ እምታወጋይ ተሆነ ነገሩን እንዲገባይ በራሴ አፍ አውጋይ!'።
አልሁት ባሳሳቁ በሽቄ።ተዛ ቡሀላ ነገሩን እንዲህ ብሎ አጫወተይ•••
ዘመድ አዝማዷን ታይተዋወቅ እዛው አሜሪካን ተወልዳ ያደገች ጥቁር አሜሪካዊት ሴት ያገባል!
ዛድያ ተተጋቡ ቡሀላ እነሱ ዘንድ በመጣው ወንድሟ እና በሷ መሀል ያለውን የመልክ ልዩነት ቲያይ ለየቅል ብቻ ታይሆን ጭራስ ታንድ ማህጠን የወጡም አይመስሉ።
ወንዱሟን ቲያው ዝንጀሮ ቆሞ እምሄድ እይ ሰው ትለመሆኑ የሚያጠራጥር ሆኖ ሳለ እሷ ልቅም ያለይ ቆንጆ ነይ።
ታድያ ሁለቱ አጠገብ ላጠገብ ቁጭ ብለው ባያቸው ቁጥር እንዲሁ ቲያስገርመው!።
መገረም ብቻ አይደለም ቲያስደምመው!።
መደመምም ብቻ አይደለም አንዳንዴ እንደውም ቲያስደነግጠው ይቆይልሀል።
ማንን እንደሚጠይቅ ማንን እንደሚያማክር ግራ እንደተጋባ።
በዚህ መሀል አርግዛ ትወልዳለይ። ዛድያ ህጣኑ አደግ ቲል ወንድሟን መስሎ እርፍ።
ታክስቴ ልዥም ተሚሽቱም ምንም ያልወሰደ ጓጉንቸር ሆኖ ቁጭ።
የልዡ እና የወንድሟ መልክ መመሳሰል ውስጥ ውስጡን እየከነከነውም ቢሆን
ፈጣሪ የሰጠውን ልዥ በጠጋ ተቀብሎ ማሳደጉን ቀጠለ።
ያክስቴ ልጅ ለወንድሙ እንደነገረው ተሆነ•••
በመሀል ወንድማ የሚጠቀምበትን "ላብ ቶብ "ለብቶም"
የሚሉት "ኮምፒተሩን " ባጋጣሚ ክፍት ሆኖ አግኝቶት ኖራል ውስጥ ገብቶ ሲበረብር ተአመታት በፊት ሚሽቱ ተወንድማም፣ ተቤተሰቧም፣ ብቻዋንም የተነሳያቸውን ትክክለኛውን የቀድሞ መልኳን የየዙ ፎቶዋን ያያል! ክው አለ።
ያኔ በተፈጥሮ ተፈጣሪ የታደለይውን መልክ ዘመን አመጣሽ በሆነ "ቴክኖሎጂ" "የብላስቲካ ሴርጀሪ" ነው እሚባል ያለይ መሰል ብቻ በሱ ቴክኖሎጂ ገፅታዋን ሙሉ በሙሉ እንደቀየረይ ይደርስበታል።
ዝናቡ የፈረንጅ አፍ እየቀላቀሉበት ለሱ ያልገባውን ነገር ለኔ ሊያወጋይ ሲደክም ግራ እንደገባይ አይን አይኑን እያየሁ ታደምጠው አሁንም ቀጠለና•••
"የቀድሞ ፎቶዎቿን አንድ ባንድ እያሳየ ሲጠይቃት አይን ፍጥጥ !ጥርስ ግጥጥ!ዋሽታ እማታመልጠው ሀቅ ነውና አልካደይውም አመነይ። በጥቅሉ ያገባው በፈጣሪ የተሰራችውን ታይሆን በሰው የታደሰችውን ነው ስልህ!
ሲለይ ይበልጡን ተምያታብይ። ዝናቡ መዝነብ ተዥመረ መች ያቆማል አሁንም ቀጠለ•••
"ተዛ ቡሀላ የኛ ሰው ሀበሻ ያው እንደእልኸኛነቱ ሁሉ ተረታ /ታሸነፈ/ ቡሀላ ይቅር ባይነቱም የበዛ አይደል!
እውነቱን ታወቀ ቡሀላ ሁሉን ትቶ ይቅር ቢላትም በሷ ብሶ በጀ አላለይም። እውነቱ ተወጣ ቡሀላ ከሱ ጋር መቀጠሉ ጎረበጣት መሰል መፋታቱን መርጣ ተፋቱ። አንዳርጌ ሙት እሄን ስስማ ጉድ ጉድ ጉድ እያልሁ ጭንቅላቴን ይዤ ልጮህ ምን ቀረኝ!" ብሎ ያክስቱን ልጅ ታሪክ ቋጨ።
እንኳን የተዋቡ አባት እንዲህ ናላዬን አዙረውት በደናውስ ግዜ ቢሆን እንዲህ ለራሱ ያልገባውን ወሬ ለኔ አውርቶልዪ ቤት በኩል ይገባኛል።
ምናለ ሰው ለራሱ ያልገባውን ለሌላው ባያወራ
ምን እንዳናደደይ እንጃ ብቻ ብልጭ አለብይ•••
የነገሩ ባለቤት ያልጮኸውን አንተ ምን ቤት ነህ ጭንቅላትህን ይዘህ እምትጮኸው ጎበዝ??" ልለው አሰብሁና መልሼ ታጤነው ስንቱ በማያገባው እየጬኸም አይደል ብዬ•••
" እሄስ ያስጮሀል ዝንቡ ጮኽህ ቢወጣልህ ጥሩ ነበር ሙት!" አልኹት።
"ሙት እውነትህን ነው! ሳልጠጣ ሄጄ እንዢ ሞቅ ቢለኝማ መጮኼ አይቀርም ነበር አሁን ልጩህ እንዴ? አለዪ
ቆይ እኔ ልውጣና ትጮሀለህ ብዬው ሂሳቤን ከፍዬ ተጠጅ ቤቱ ወጣሁ።
ግቢ እንደደረስሁ መጠጡ በሰጠይ ድፍረት ትልቁቤት በር ላይ ቆምሁና ጮክ ብዬ ተዋቡ የኔ ብዬ ተጣራሁ።
በሩን በስሱ ከፈተይና •••
"በእጇ አባዬ ተኝታል አትጩህ!"
የሚል ምልክት አሳየችይ።
መስማታቸው አይቀርም ብዬ•••
ቅድም የሞተውን ሰው ስም በደንብ ሳላጣራ ስላስደነገጥሁሽ ይቅር በይይ ውብ አለም የስም ስተት ነው " ለጋሼ ዘርጋውም ንገሪልይ አልኋት።
በሩ ላይ እንደቆመይ አንገቷን አዙራ አባቷ ወደተኙበት ገልመጥ አረገይና።
በል አሁን ግባና ተኛ በቃ ደና እደር። አለችይ።
በጀ እያልሁ በሬን ከፍቼ እስትገባ ቆማ እያየችይ እንደሆነ ያወቅሁት የኔኑ ክፍል በር ልዘጋ ስዞር ነበር። ቆሜ ታያት እጇን አውለብልባ ተሰናበተችኝና ገብታ በሩን ጠረቀመችው።
በጥዋት ቁርስ ይዛልይ እንደገባይ።
ተዋቡ ላንድ ለሁለት ሳምንት ዘመድ ዘንድ ደርሼ እመለሳለሁ አንድ ሁለት ቅያሪ ልብስ ይዘሽልይ ነይ አልኋት።
ታፏ ቃል ታታወጣ ትክ ብላ እያየችኝ እንባዋ ሁለቱ አይኖቿ ላይ ግጥም ቲል ፊቷን መልሳ ተክፍሌ ወጣይ።
ትንሽ ቀየት ብሎ በሬ ቲንኳኳ ተዋቡ ልብሱን ይዝልይ መጥታ ነው ብዬ ማነው ታልል ብድግ ብዬ ብከፍተው አባቷ ናቸው።
ደንገጥ ብዬ ደና አደርህ ጋሼ ዘርጋው ምነው በጥዋት በሰላም ነው ብለው "ፈልጌህ ነው አንዳርጌ ለባብስና እላይ ቤት ና እጠብቅሀለው" ብሎኝ ተመለሰ።
ለምን ፈለጉይ ብዬ ፈራ ተባ እያልሁ ወደ ትልቁ ቤት ገባሁና ቁጭ አልሁ።
አንዴ አጠገባቸው ወደ ተቀመጠይው ተዋቡ አንዴ ወደኔ እየተመለከቱ •••
"ልጆቼ•••" ብለው መልሰው ዝም አሉ።
ገና መናገር ታይጀምሩ ፊታቸው ተቀያየረ።
ሁለመናቸውን የሀዘን ድባብ ጣለበት።
ልዦቼ እናቴ ገና የአስራ ሁለት አመት ልዥ እያለሁ ነው በወባ በሽታ የሞተችብይ።
ታድያ የናቴን ያህል የምወዳት አንድ ለናቷ የነበረይ አንድ ታላቅ ብቻ ነይ የነበረችይ።
ተዋቡ ትባላለይ ሲሉ እኔና የኔዋ ተዋቡ ግራ በመጋባት ተያየን።
ያንተን ሚሽት እቺ ልዤን ተዋቡ ያልኋት መልኳ ተሷ ጋር ስለሚመሳሰል ነው። እይ ጨቅላ ሆና እናቷ ያወጣይላት ሽም ሌላ ነበር።
አባታችን ብዙም ለልጅዥፊቱ የማይፈታ ሰው ነው። ስለዚህ እንደናትም ፣እንደህትም፣እንዳባትም የማያት ይችኑ እህቴን ነበር። ተራሴ በላይ እወዳት ነበር።
ማግባት አይቀርምና ባል ታገባይ ቡሀላ አባቴ ብዙም ስለማይቀርበይ ብቸኝነት ያጠቃይ ዥመር።
አብዛኛውን ግዜ እህቴ ዘንድ እየሄድኩ ብቀመጥም ባሏ አመለ ክፉ ነበርና ቲያሰቃያት እያየሁ ስለማያስችለዪ እሷን ሲያስለቅስብይ ሰድቤው ወደ ቤቴ እመለሳለሁ።
ግን አያስችለኝም አሁንም ስናፍቀኝ እሄዳለሁ አሁንም ተጣልቼው እመለሳለሁ።
በይህ ሁኔታ አመታት ቢቆዩም ልዥ አልወለዱም
ችግሩ ተሱ ይሁን ከሷ አላውቅም ብቻ ልዥ አልነበራቸውም።
ጠባቸው እየተደጋገመና እየከረረ ቲመጣ እህቴ ተባሏ በተጣላይ ቁጥር ወደኛ ዘንድ መምጣት ዥመረይ።
ስትመጣ አባቴ ልዥን ቀርቦ ? ምን ከፍቶሽ ነው? ሳይል ፣ ምንድን ነው በመሀከላችሁ ያለው ችግር?"
ብሎ የሚፈታ ችግር ከሆነ መፍትሄ እንዲያበጁለት መፍትሄ ከለለውና የሷ ምርጫ መለያየት ተሆነ እንዲለያዩ ፍላጎቷን ታይጠይቅ ፣ ከፍቷት በመጣች ቁጥር ሴት ልዥ ከቧላ ጋር በተጣላይ ቁጥር ሮጧ ወደቤተሰቦቿ የምትመጣ ከሆነ ደግ አደለም እያለ አሳቆ ሲመልሳት አለቅሳለሁ።
እኔ የባሏን ጠባይ አውቀዋለሁና ተጣልታ መጥታ ሂጂ ብሎ በሚያባርራት አባቴ እጅጉን እናደድ ነበር።
በመጨረሻም እሷው ጋር ሄጄ በሌላኛው ክፍል ውስጥ በተኛሁበት የገዛ ባሏ እህቴን በተኛችበት ገሏት ጠፋ።
ተንቅልፌ እንደተነሳሀ በተኛችበት ታርዳ የሞተይውን የገዛ እህቴን ሬሳ አየሁት።