Репост из: ኢትዮ መረጃ - NEWS
በድሬዳዋ ከተማ ሀዘን ላይ ከነበሩ ወላጆቿ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት የዘረፈችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች!!
የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አራት ልዪ ስሙ መብራት ሃይል አብዩ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሀዘን ላይ ከተቀመጡ ወላጆቿ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት ዘርፋ ለማምለጥ የሞከረችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላለች።
ወላጆቿ የስርቆት ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ለፖሊስ አመልከተው የነበረ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ አስተባባሪ ተወካይ ዋና ሳጅን ስንዱ ካሳሁን ተናግረዋል።
ተከሳሿ ግለሰብ በአንድ ትምህርት ቤት አብሯት የሚማሩ ጓደኞቿን ከቤተሰቦቿ ንብረቱን እንዲዘርፉ በመንገር እና ንብረቱን ሸጠው ከተማ ቀይረው የራሳቸውን ህይወት እንደሚመሩ አሳምናቸው የነበረ መሆኑ ተጠቁሟል።
ቤተሰቦቿ ሀዘን ላይ ባሉበት ሰዓት ከጓደኛዋ ጋር ተባብራ በሳጥን ተቀምጦ የነበረ ወድ የሆነ ጌጣጌጥ እና ንብረት ሰርቀው በደላላ አማካኝነት ወርቁን በማሽን አስፈትሸው አብሯት የሰረቀችውን ጨምሮ ሁለት ጎደኞቿን ወደ ሀረር ከተማ የላከቻቸው መሆኑ ተረጋግጧል ።
ወላጆቿ ጉዳዩን ለፖሊስ ማመልከታቸውን ያወቀችው ልጅ ድርጊቱን መፈጸሟን ፖሊስ ጥርጣሬው ውስጥ እንዳስገባት ስታውቅ ድርጊቷን አምና ቃሏን እንዲሁም ጎደኞቿ ያሉበት ቦታ ልታመለክት ችላለች ።
የድሬዳዋ ፖሊስ ከሀረሪ ፖሊስ ጋር በመነጋገር ባደረገው ጠንካራ ክትትል በሀረር ከተማ ሆቴል ውስጥ ተከራይተው በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውንና መዝገቡም እየተጣራ እንደሚገኝ ዋና ሳጅን ስንዱ ካሳሁን ተናግረዋል።
@sheger_press