እውቀትና የእውቀት ባለቤቶች ደረጃ ክፍል - 23 ኡለማን ማላቅ … አላህን ማላቅ ነው ኡለማዎች በሸሪዓ ከፍተኛ ቦታ አላቸው፡፡
ኢማም አህመድ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል:-“በዚህ ኡመት ውስጥ ኡለማዎች የሩሱሎች ምትክ ናቸው፡፡ ኡለሞች ከነብዩ ﷺ
ሱና የሞተውን ህያው ያደርጋሉ። ኪታቡ የቆመው በእነርሱ ነው ፣ እነርሱ የቆሙትም በእርሱ ነው፡፡ ኪታቡ የተናገረው በእነርሱ ነው ፣ እነርሱም የተናገሩት በእርሱ ነው፡፡ ጠማማው ወደቅኑ ጎዳና እንዲመጣ ጥሪ ያደርጋሉ ፣ በሚደርስባቸው መከራ ይታገሳሉ፡፡ በአላህ መጽሐፍ ሙታንን ህያው ያደርጋሉ፡፡ በአላህ ብርሃን የእውራንን አይኖች ይከፍታሉ፡፡ ኢብሊስ የገደላቸውን ስንቶችን ህያው አደረጉ! የሚዋልሉ ጠማማዎችን ስንቶችን መሩ! በሰዎች ላይ የእነርሱ ተጽእኖ ምን አማረ ! የሰዎች ተጽእኖ በእነርሱ ላይ ምን አስቀያሚ ሆነ!" ኡለሞች :- በዲን ውስጥ ከሚፈጠሩ ፈጠራዎች እና ማደናገሪያዎች ህዝባቸውን ይጠብቃሉ፡፡ ከልብ ወለድ ፣ ካልሆነ ጥላሸት ፣ ከመጣመም ዲኑን ይጠብቃሉ፡፡ የሸሪዓዊ እውቀትን ፍትሃዊ ከሆኑ ትውልዶች ተረክበው ወደሌላ ፍትሀዊ ትውልድ ያሸጋግራሉ። ከአላህ ﷻ ቁርዓን ላይ የድንበር አላፊዎችን ማጣመም ፣ የጃሂሎችን ተገቢ ያልሆነ ተፍሲር ይከላከላሉ። ይህን ዲን ለመጠበቅ አላህ አዘጋጅቷቸዋል፡፡
ኡለሞች በቁርኣን እና በሱና ኢስላምና ቁርዓን የኡለሞችን ክብር ከፍ አድርጓል፡፡ ጌታችን አሏህ ﷻ በቁርዓኑ አወድሷቸዋል ፡
يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
"አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡ አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡"(ሙጃደላ ፡ 11)
አሏህ ﷻ በትልቅ ጉዳይ ላይ ኡለሞችን አስመስክሯል፡፡ እርሱም ተውሂድ ነው። እርሱም ዲንን ለእርሱ ብቻ ማጥራት ነው፡፡
شَهِدَ اللَّهُ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَالْمَلَائِكَةُ وَأُولُو الْعِلْمِ قَائِمًا بِالْقِسْطِ ۚ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
"አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲሆን ከእርሱ በስተቀር (በእውነት የሚመለክ) ሌላ አምላክ የሌለ መሆኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)፡፡ ከእርሱ በስተቀር (በእውነት የሚመለክ) ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡"(አልኢምራን ፡ 18)
ኢማም አልቁርጡብይ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል ፡ “ይህ አንቀጽ የእውቀትን እንዲሁም የኡለሞችን ደረጃና ትልቅነት ጠቁሟል ፤ ከኡለማ ልቅና የሚበልጥ አንድ ነገር ቢኖር ኖሮ ልክ አሏህ መላኢካን እና ኡለማን ከስሙ ጋር እንዳቆራኘው ያቆራኘው ነበር፡፡” አላህ ﷻ
ኡለሞችን በደረጃ ከሌሎች ለያቸው ፣ ከፍም አደረጋቸው፡፡ قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ
«እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡"(ዙመረ ፡ 9)
ኡለሞች አላህን በጣም ፈሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ
"አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡"(ፋጢር ፡ 28)
ቀደምት ኡለሞች የትክክለኛ አሊሞችን መገለጫ እንደሚከተለው አቅርበውታል:-
አሏህ ብሎ ያለው አክሪሙል ኡለማለተቅዮቹ ነው ላልሆኑት ጠማማቀልቡ የሚሸበር ኪታቡን ሲሰማ ኡለሞችን ቁርኣን በመልካም እንዳወደሳቸው ነብዩም ﷺ እንደሚከተለው አወድሰዋቸዋል፡፡
ሙዓውያ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል
"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"
“
አላህ መልካምን የሻለት ሰው ፣ ዲንን ያስገነዝበዋል” ومن حديث أبي هريرة : "من سلك طريقا يلتمس فيه علما ، سهل الله له طريقا إلى الجنة" (رواه أبو داود والترمذي)
አቡሁረይራ የሚከተለውን የረሱል ﷺ ሐዲስ አሰተላልፈዋል ፡
“እውቀትን ፍለጋ መንገድን የተጓዘ ፣ ወደጀነት የሚወስደውን መንገድ አላህ ያመቻችለታል” ኢብን አለቀይም “ኢእላም አልሙወቂዒን” በተባለው ኪታባቸው የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
“በምድር ላይ የሚገኙ ኡለሞች ልክ በሰማይ እንደሚገኙት ከዋክብት ናቸው፡፡ በጨለማ የሚዋልሉት በእነርሱ ይመራሉ፡፡ ለሰው ልጅ የእነርሱ አስፈላጊነት ከምግብ እና ከመጠጥ በላይ ነው፡፡” ኢክሪማ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
"إياكم أن يؤذوا أحدا من العلماء ، فإن من آذى عالما فقد أذى رسول الله صلى الله عليه وسلم"
“ ከኡለማዎች አንዱን ከማወክ አስጠነቅቃችኋለሁ ፣ ኡለማን ያወከ የአላህን መልእክተኛ አወከ” ኡበይዱሏህ ብን ጀዕፈር የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
"العلماء منار البلاد منهم يقتبس النور الذي يهتدى به"
“ኡለሞች የአገር ምልክት ናቸው። ሰዎች የሚመሩበት ብርሀን የሚቀሰመው ከእነርሱ ነው።” ኡለማን ማክበርና ፤ ሀቃቸውን ማወቅ ኡለማን ማክበር በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። የኡለሞችን ደረጃ ጠንቅቆ ማወቅ ፣ አላህ በሰጣቸው ደረጃ ማስቀመጥና ማላቅ ተገቢ ነው።
የአላህ መልክተኛ ﷺ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል :-
"ليس من أمتي من لم يجل كبيرنا ، ويرحم صغيرنا ، ويعرف لعالمنا حقه" رواه أحمد وحسنه الألباني
“ታላላቆቻችንን ያላላቀ ፣ ለታናናሾቻችን ያላዘነ ፤ የኡለሞቻችንን ሀቅ ያላወቀ ከኡመቶቸ አይደለም፡፡” ኡለማን ማላቅ አላህን ማላቅ ፣ሸሪኣውንም ማላቅ ፣ ትእዛዙንም ማክበር ነው፡፡ አቡሙሳ አልአሽአርይ የሚከተለውን የረሱል ﷺ ሐዲስ አስተላልፏል ፡"إن من إجلال الله إكرام ذي الشيبة المسلم ن وحامل القرآن غير الغالي فيه ، ولا الجافي عنه ، وإكرام ذي السلطان المقسط" رواه أبو داود ، وحسنه الألباني
“የሽበት ባለቤት የሆነን ሙስሊም ፣ ድንበር አላፊ ያልሆነንና ያልዘቀጠ የቁርአን ተሸካሚን እንዲሁም ትክክለኛ የስልጣን ባለቤትን ማላቅ አላህን ከማላቅ ነው።" ኢማም አጥጧሀዊይ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡“ከቀደምቶችም ይሁን ከእነርሱ በኋላ የመጡ ታብእዮች የመልካም ባለቤቶችን የፊቅህ በላቤቶችን በመልካም እንጅ አያወሱም፣ በመጥፎ እነርሱን ያነሳ ከመንገድ ውጭ ነው፡፡” ሸእብይ የሚከተለውን ተናግሯል ፡ ዘይድ ብን ሳቢት ከጀናዛ ላይ ሰገደ፡፡ ከዚያም በቅሎ እንዲጋልብ አቀረብኩለት፡፡ ኢብን አባስ መጣ፡፡ እርካቡን ያዘና "የረሱል የአጎት ልጅ በቅሎውን ያዝ" አለው ለኢብን አባስ፡፡ ኢብን አባስም ፡ "በኡለማ እና በታላላቆች ሲሰራ የነበረውም ይኸው ነው" አለው፡፡
ኸለፍ የሚከተለውን ተናግሯል ፡