ስት---ሄጂ ንገሪኝ-፪
(ሳሙኤል አለሙ)
°
°
ኩኩሉ...
ሻርቡን ተከናንበሽ
ኩኩሉ...
ሂጃማውን ለብሰሽ
ኩኩሉ...
ዘንቢሉን ሸከፍሽው
ነግቷልን ስጠብቅ
ናፍቆቱን ወሰድሽው።
°
°
የት አለሽ ከጓሮው
የት አለሽ ከጓዳው
እያየሽ ማድጋው
እያየሽ ዝም አለ
ከዘንቢሉ ሆድ ላይ ዓይኑን እንዳልጣለ
ዓይኑን በጨው አጥቦ
እንዴት ይጨክናል
እራሱም ተርቦ
°
°
ይኸው አደራ ያልሻቸው
እናቱ የሞተበት
ገበያ የሄደበት
ይለያሉ ከቶ...ከቶውን ይለያሉ
አንዴ በቁጣ አንዴ ባለንጋ
መምጣትሽን ሲያቀሉ
እንባዬም ተደበቀ ፥ ያለ ዓመሉ
°
°
ኩኩሉ...
መሄዱ---እንደ ያኔው ግዜ መስሎኝ
ኩኩሉ...
መምጣቱ ---እንደ ልጅነቴ መስሎኝ
መስሎኝ...መስሎኝ...መስሎኝ ብቻ!
የ'ናቴን መሳይ
የ'ናቴን አቻ
ካሁን አሁን ስጠብቃት
አሁን ካሁን ጋራ ተደባለቀብኝ
እንዴት ልለየው ነው...
መምጣት ከመቅረት ጋ ፤ ሲመሳሰለብኝ
ነግቶልኝ እስካገኝሽ...
ካሁን አሁን ፤ እያሉ የሚሸነግሉትን
ድንገት እየሄዱ ፤ ወጥተው የሚቀሩትን
ለምዶብኛል'ና ፤ እጠብቃለው ያደኩበትን።
ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
Join us 👉👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
(ሳሙኤል አለሙ)
°
°
ኩኩሉ...
ሻርቡን ተከናንበሽ
ኩኩሉ...
ሂጃማውን ለብሰሽ
ኩኩሉ...
ዘንቢሉን ሸከፍሽው
ነግቷልን ስጠብቅ
ናፍቆቱን ወሰድሽው።
°
°
የት አለሽ ከጓሮው
የት አለሽ ከጓዳው
እያየሽ ማድጋው
እያየሽ ዝም አለ
ከዘንቢሉ ሆድ ላይ ዓይኑን እንዳልጣለ
ዓይኑን በጨው አጥቦ
እንዴት ይጨክናል
እራሱም ተርቦ
°
°
ይኸው አደራ ያልሻቸው
እናቱ የሞተበት
ገበያ የሄደበት
ይለያሉ ከቶ...ከቶውን ይለያሉ
አንዴ በቁጣ አንዴ ባለንጋ
መምጣትሽን ሲያቀሉ
እንባዬም ተደበቀ ፥ ያለ ዓመሉ
°
°
ኩኩሉ...
መሄዱ---እንደ ያኔው ግዜ መስሎኝ
ኩኩሉ...
መምጣቱ ---እንደ ልጅነቴ መስሎኝ
መስሎኝ...መስሎኝ...መስሎኝ ብቻ!
የ'ናቴን መሳይ
የ'ናቴን አቻ
ካሁን አሁን ስጠብቃት
አሁን ካሁን ጋራ ተደባለቀብኝ
እንዴት ልለየው ነው...
መምጣት ከመቅረት ጋ ፤ ሲመሳሰለብኝ
ነግቶልኝ እስካገኝሽ...
ካሁን አሁን ፤ እያሉ የሚሸነግሉትን
ድንገት እየሄዱ ፤ ወጥተው የሚቀሩትን
ለምዶብኛል'ና ፤ እጠብቃለው ያደኩበትን።
ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
Join us 👉👇 https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA