━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━
ይናገራል ፎቶ-፪
(ሳሙኤል አለሙ)
ከኮሞዲኖው ላይ
ከግድግዳውም ላይ
አንቺኑ አንቺኑ ሳይ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፥ ፎቶሽን ታቅፌ
ምላሽ ጠብቃለው
ይናገራል ፎቶ ፥ የሚል ግጥም ፅፌ
...
[
ይናገራል ፎቶ
ብጠብቃት ቀ.....ና.....ት
ብጠብቃት ሳ...ም...ን...ታ...ት
ብጠብቃት ወ..........ራ............ት
ብጠብቃት አ........መ.......ታ.........ት
እኔን ከማናገር ፥ ዝምታ በልጦባት
ከፎቶው ላይ ቀረች፤
ሳሎን እየዋለች ፥ ሳሎን እያደረች።
]
ወረቀቱን ቀደድኩ ፥ ግጥሙን ሰርዤው
ፎቶውን መለስኩ ፥ ከአልበሙ ሸጉጬው
...
እንግዲህ ምን ትሆኚ!
አልፎ አልፎ እየመጣ
እንግዳ ያይሻል ፥ እስረኛ ስትሆኚ።
ሲናፍቅሽ ኮሞዲኖው
ሲናፍቅሽ መደርደሪያው
ሲናፍቅሽ የትላንቱ
ታወሪኝ ይሆናል ፥ ልክ እንደ በፊቱ
ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏
Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA
ይናገራል ፎቶ-፪
(ሳሙኤል አለሙ)
ከኮሞዲኖው ላይ
ከግድግዳውም ላይ
አንቺኑ አንቺኑ ሳይ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፥ ፎቶሽን ታቅፌ
ምላሽ ጠብቃለው
ይናገራል ፎቶ ፥ የሚል ግጥም ፅፌ
...
[
ይናገራል ፎቶ
ብጠብቃት ቀ.....ና.....ት
ብጠብቃት ሳ...ም...ን...ታ...ት
ብጠብቃት ወ..........ራ............ት
ብጠብቃት አ........መ.......ታ.........ት
እኔን ከማናገር ፥ ዝምታ በልጦባት
ከፎቶው ላይ ቀረች፤
ሳሎን እየዋለች ፥ ሳሎን እያደረች።
]
ወረቀቱን ቀደድኩ ፥ ግጥሙን ሰርዤው
ፎቶውን መለስኩ ፥ ከአልበሙ ሸጉጬው
...
እንግዲህ ምን ትሆኚ!
አልፎ አልፎ እየመጣ
እንግዳ ያይሻል ፥ እስረኛ ስትሆኚ።
ሲናፍቅሽ ኮሞዲኖው
ሲናፍቅሽ መደርደሪያው
ሲናፍቅሽ የትላንቱ
ታወሪኝ ይሆናል ፥ ልክ እንደ በፊቱ
ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏
Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA