ሽርክና ቢድዓን እንጠንቅቀ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


የኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ የተውሂድ ክፍል
https://t.me/AbuTekiyKaeidBastBot
አላማችን ሰፊውን ህዝብ ከሺርክና ከቢድኣ ማስጠንጠንቀቅ ነው።
በሱና በተውሂድ የተሳሰራችሁ፣
ወንድምና እህቶች በየትም ያላችሁ፣
አገራችሁ የትም ምእራብ ምስራቅ ቢሆን፣
በሌላም አቅጣጫ ሰሜን ደቡብ ቢሆን፣
ከመሃል እር ቆ ምን ዳርቻ ቢሆን፣
አስተያየት 📞 @CommentAnd1_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የአስጎሪ ፣ጭረቻ እና አካባቢው. ማህበረሰብ ኑ እንወያይ የሀገራችንን አካባቢ ማህበረሰብ ከጨለማ፣ ከድህነት፣ከተያያዥ ችግሮች ተወያይተን መፍትሄ እንድመጣ እናድርግ።


ኑ ተወላጆቹ እንወያይ


አስጎሪ፣ጭረቻና አካባቢው።
ይህ በደሴ ዙሪያ ወረዳ የአስጎሪ፣ጭረቻ እና አካባቢው ማህበረስብ መወያያ የቴሌግራም ቻናላችን ነው።

https://t.me/joinchat/AAAAAE0ky7ikO7dI6zxM2A
አስተያየት መቀበያ↓↓
https://t.me/AsgoriChirechaAndEnvironmentBot


Channel
https://t.me/AsgoriChirechaAndEnvironment


አስጎሪ ጭረቻና አካባቢው

https://www.facebook.com/114473143591650/posts/148987030140261/?app=fbl


Репост из: ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
عيدكم مبارك!
تقبلﷲ منا ومنكم صالح الأعمال!
ኢዳችሁ የተባረከ ይሁን!
አላህ ከኛም ከናንተም መልካም ስራችንን ይቀበለን
አሚን
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ወንድማችሁ፡ አቡ ተቅይ ቃዒድ


ውዷ እናቴን………

إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُوْنَ، اَللَّهُمَّ أْجُرْنِيْ فِيْ مُصِيْبَتِيْ وَأَخْلِفْ لِيْ خَيْرًا مِنْهَا.

‘ኢንና ሊልላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን፤ አልሏሁምመ አጂርኒ ፊ ሙሲበቲ፤ ወአኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሀ እኛ የአላህ ነን፡፡ ወደርሱም ተመላሾች ነን፡፡ አላህ ሆይ! ለደረሰብኝ ችግር ምንዳ ስጠኝ፡፡ በርሷ ምትክም የተሸለ ነገር ተካልኝ፡፡ ’

26/05/1442ዓ ሂ
10/01/2021 እኤአ
02/05/2013 እ ኢ አ እለተ እሁድ ከሰዓት በኋላ ውዷ እናቴ ትንሽ ህመም ተሰምቷት ነበር ከዚያም ህመሟ እየበረታ በመሄዱ በተቻለመጠን ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ለ4 ቀን ያህል አልጋ ይዛ የህክምና እርዳታ ለማገኘት ብንሞክርም. አላህ ሱብሃነ ወተዓላ የኔነሽ ይቺ ዱኒያ በቃሽ ብሏት
13/06/1442 ዓ ሂ
26/01/2021 እ ኤ አ
19/05/2013 እ ኢ አ እለተ ማክሰኞ ከሌሊቱ 10:00 አካባቢ ወደ ማይቀረው አሄራ ሄደችበኝ ። እለተ ረብዑ አስክሬን ይዘን ወደ መኖሪያ ቦታ በመሄድ እለተ ሀሙስ የሙስሊም ሀቋን በማድረስ. አፈር አለበስን።

አላህ ውዷ እናቴን ይምራት ዘንድ፣ ለእኛም ቀጥተኛውን መንገድ ይመራን ዘንድ. ሙስሊም ወገኖቼ ከልባችሁ ዱዓ አድርጉልኝ።

በግል ማግኘት ከፈለጋችሁ
@CommentAnd1_bot

@KunSelefiyeBot

@AbuTekiyKaeid
+251931489529
+251987787882


حَدَّثَنَا عَبْدَانُ، عَنْ أَبِي حَمْزَةَ، عَنِ الأَعْمَشِ، عَنْ شَقِيقٍ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم كَلِمَةً وَقُلْتُ أُخْرَى قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏
"‏ مَنْ مَاتَ وَهْوَ يَدْعُو مِنْ دُونِ اللَّهِ نِدًّا دَخَلَ النَّارَ ‏"
-.‏ وَقُلْتُ أَنَا مَنْ مَاتَ وَهْوَ لاَ يَدْعُو لِلَّهِ نِدًّا دَخَلَ الْجَنَّةَ‏.‏

اردو ترجمہ دستیاب نہیں ہے .

Narrated Abdullah: The Prophet (ﷺ) said one statement and I said another. The Prophet (ﷺ) said "Whoever dies while still invoking anything other than Allah as a rival to Allah, will enter Hell (Fire)." And I said, "Whoever dies without invoking anything as a rival to Allah, will enter Paradise."

የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
💎{ ከአላህ ውጭ ብጤ አድርጎ እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ። }

📚ቡኻሪ በቁጥር(4497) ላይ ዘግበውታል።


USC-MSA web (English) reference : Vol. 6, Book 60, Hadith 24
Arabic reference : Book 65, Hadith 4497
ሽርክና ቢዲዓን እንጠንቀቅ📥
http://t.me/AbuLoveHome
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል📥
https://t.me/KunSelefiyeAllMineOfIniformation

ግሩፕ📥
https://t.me/PomeChannelGroup
📤📤📤📤📤📤📤📤📤📤


تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
Eid mubarek
ዒድ ሙባረክ
የደስታ የሰላም እና የተባረከ ዒድ ይሁንልን!!

አቡ ተቅይ ቃዒድ




ከሽርክ እና ከቢዲዓ ከሆረፋት ነገሮች ለመጠበቅ አንድኛች ለአንድኛችን መስተዋት መሆን አለብን፣ አልበዚያ ተያይዘን ከእሳት ላይ እንወረወራለን።

ለዛም ነው በጥሩ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል የኢማን አካል የሆ ነው።

🔻
"ኑዕማን ኢብኑ በሽር (ረዲየለሁዐንሁ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

"ከአላህ ድንበር ላይ የሚቆም (ድንበሩን የማይዳፈር) እና የሚጥስ ሰው ምሳሌ ከአንዲት መርከብ ላይ እንደተሳፈሩ ሰዎች ነው። ከፊሎቹ ከመርከቧ የላይኛው ክፍል፥ ከፊሎች ደግሞ ከታች ተሳፍረዋል። ከታችኛው የመርከቧ ክፍል ያሉት ውሃ መጠጣት በሚፈልጉበት ወቅት በላይኛው ክፍል ማለፍ ግዴታቸው ነው:: "ድርሻችን በሆነው የመረከቧ አካል (ለውሃ መቅጃ የሚሆነን) ቀዳዳ ብናበጅ ከላይ ያሉትን አንጎዳም" የሚል ሐሳብ አፈለቁ። ከመርከቧ የላይኛው ክፍል ያሉት ሰዎች እነዚህኞቹን ያሻቸውን እንዲፈጽሙ ከተዋቸው አብረው ይጠፋሉ። እጃቸውን ከያዟቸው ግን ሁሉም ከጥፋት ይድናሉ።"
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ስለዚህ ወገኖች ሆይ ተያይዘን እንዳንከስር የአላህን ትዕዛዝ እና የነብዩን ሱና ብቻ አጥብቀን እንያዝ።



ሽርክና ቢዲዓን እንጠንቀቅ📥
http://t.me/AbuLoveHome
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል📥
https://t.me/KunSelefiyeAllMineOfIniformation

ግሩፕ📥
https://t.me/PomeChannelGroup
📤📤📤📤📤📤📤📤📤📤


እነዚያ ድንቅ ትውልዶች
እንዲህ ነበሩ🔻


"ኢብኑ ወሊድ ዑባደት ኢብኑ ሷሚት (ረዲየላሁ.ዐንሁ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦

"በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ በታዛዥነታችን ልንፀና የመልዕክተኛውን ፍላጎት ከፍላጎታችን ልናስቀድም ከአላህ ዘንድ ለመረጃ የሚሆንን ግልፅ ኩፍር እስካላየን ድረስ ሙስሊም መሪያችንን ላንቀናቀን፥ የትም ብንሆን ከሀቅ ውጭ ላንናገር፥ የአላህን እርካታ በመሻት በምንፈፅመው ተግባር የሰዎችን ትችት ላንፈራ ከአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ.ዐለይሂ.ወሰለም) ጋር ቃል ተጋባን።"
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
እኛስ የት ነው ያለ ነው⁉️

ሽርክና ቢዲዓን እንጠንቀቅ📥
http://t.me/AbuLoveHome
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል📥
https://t.me/KunSelefiyeAllMineOfIniformation

ግሩፕ📥
https://t.me/PomeChannelGroup
📤📤📤📤📤📤📤📤📤📤


ኸይር ፈላጊ ወደ ሸዋ ሮቢት


اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎

ውድ የተከበራቹህ አህለል ኸይሮችየ እደት ናቹህ ረመዷን ሄደብን ኢዱን አሳለፍን አልሀምዱሊላህ ነገራቶች ሁሉ እያለፉ የጀመርነው የሸዋሮቢት መስጅድ ጉዳይ ግን ዛሬም እንደጠበቀን እርዳታችንን በመፈለግ እንዳለ ነው እና አሁን ለኸይር ነገር ምን ያክል ቦታ አላቹህ በአድስ መልኩ ለመንቀሳቀስ ተነስተናል ከጎናችን ለመሆን ዝግጁ ናቹህን??

ነአም አወ እደምትሉ አልጠራጠርም የሱና ሰወች አኩሪወቻችን ናቹህ አሏህ ይጠብቃቹህና እናማ ተነቃቁ መንገድ ላይ ነን መተናል ለመሳተፍ ለማሳተፍ ተዘጋጁ ሊንኩን ሸር አድርጉ ባረከሏህ ፊኩም‼️

የሸዋሮቢት መስጂድ ማሰባሰቢያ. የዋትሳፕ ግሩፕ
📍 ወደ ግሩፑ ስንቀላቀል አላማውን አውቀን እና በኢኽላስ ይሁን!!

💎ወንዶቹም በወንዶች
👑ሴቶችም በሴቶች ብቻ ጆይን በሉ

የወዶች ብቻ
Follow this link to join my WhatsApp group: https://chat.whatsapp.com/BlVbEUhxeh1ENI6gPx7pnB


የሴቶች ብቻ
Follow this link to join my WhatsApp group: https://chat.whatsapp.com/GzzeDpeEhH0J2ZmpZYmuSz


የሰብሳቢዎች ስምና ስልክ ቁጥር⤵⤵⤵⤵

ኢትዮጵያ

የአካውንት ቁጥር⤵
ዳሽን ባንክ 29280164255111
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ⤵️
አካውንት 1000325792829
የተወካዮች ስም⤵
ሙሀመድ መኮንን
ቁጥር +251925221042
አክረም ተሾመ
ቁጥር +251920153478
ከድር አደም
ቁጥር +251913826562

📍የ3ቱንም ስም ማስገባት እዳይርሱ


[[ሳዑዲ ጂዳ🔃]]

~ሀያት ኑሩ
+966592293714

~ሀቢባ ቢንት ሙርሰል
+966544529350◄ ዋትሳፕብቻ
+9665 31072572◄ ከዋትሳፕ ውጪ

[[መዲና🔃]]

~ሶፊያ ሞገስ
+966559152060

~አበባ ጋሻው
+966599781521

[[ዱባይ/ኢማራት🔃]]

~ሀዲያ ኡሙ ፈይሰል
የቀጥታ +971556288945
የዋትሳፕ +971552342870


~ሀሊማ ኡሙ ፈውዛን
+971505823048


~ሚስኪያ ጦሃ
+971569589030

[[ኩዌት🔃 ]]

~ሒክማ ያሲን
+96550798686


~ሀናን ቢንት ካሳው
ቀጥታ +96555368637
ዋትሳፕ +966597683150

[[ ኳታር🔃 ]]

~ዓኢሻ ቢንት ኢብራሒም
+966582171865 ◄ዋትሳፕ ብቻ
+97433445029 ◄ከዋትሳፕ ውጪ


~መኪያ ዩሱፍ
+97430077436


🔃ለሌሎች ኸይር ፈላጊዎችም ሊንኩን ሼር በማድረግ ጆይን ብለው እንዲገቡ ይጋብዙ🔃🔃🔃🔃🔃

https://t.me/ye_shewa_robit_mesjid


✔️ ሸዋል ፍች(ትንሿ ፍች) በኢስላም
(በቁርአንና በሐዲስ) እይታ

⬅️ فإن الله شرع للمسلمين عيدين عيد الفطر وعيد الأضحى.

《አላህ በኢስላም ውስጥ ሁለት አመታዊ በዓልንና አንድ ሳምንታዊ በዓልን ብቻ ነው የደነገገው። ለዚህም ማስረጃው…

⬅️ ودليل ذلك ما رواه أبو داود في سننه عن أنس رضي الله عنه قال قدم رسول الله صلى الله عليه وسلم المدينة ولهم يومان يلعبون فيهما فقال: "ما هذان اليومان؟ قالوا: كنا نلعب فيهما في الجاهلية فقال يا رسول إن الله قد أبدلكم بهما خيراً منهما يوم الأضحى ويوم الفطر "
رواه أبوا داود.

《ነብዩ ﷺ ወደ መዲና በተሰደዱበት ወቅት የመዲና ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው በመጨፈር የሚያከብሯቸው ሁለት አመታዊ በዓላት(ዒዶች) ነበሯቸው።
ነብዩﷺ እነዚህ ሁለት የምታከብሯቸው ቀናት ምንድናቸው ብለው ሲጠይቋቸው የመዲና ነዋሪዎችም ከድንቁርና(ከጃሂሊያ) ዘመን ጀምሮ እናከብራቸው ነበር አሏቸው ነብዩም ﷺ አላህ እነዚህን ሁለት አመት_በዓሎችን በተሻለ ሌላ ሁለት አመት_በዓላት(ኢዶች) ቀይሮላቹሀል እነሱም ዒደል ፊጥርና ዒደል አድሐ ናቸው። ብለዋቸዋል።》
አቡዳውድ ዘግበውታል።

➡️ ከዚህ የምንረዳው በኢስላም ውስጥ የተደነገጉ አመታዊ በዓላት ሁለት ብቻ እንደሆኑና እነሱም ዒደልፊጥርና ዒደል አድሐ ብቻ እንደሆኑ ነው።

➡️ ሳምንታዊው ዓመት_በዓል ደግሞ አንድ ብቻ ሲሆን እሱም የጁምዓ እለት ነው።

➡️ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ግን በቁርአንም ሆነ በትክክለኛ(በሰሒህ) ሐዲስ ያልተደነገጉ ኢ_ኢስላማዊ በዓላት ሲከበሩ ይስተዋላል።

➡️ ከእነዚህ በኢስላም ካልተደነገጉ በዓላት መካከል መውሊድ፣ሸዋል ፍችና ዐሹራ ናቸው።

➡️ እነዚህ ሶስቱ በዓላት መውሊድ፣ሸዋል ፍችና ዐሹራ በቁርአንና በትክክለኛ ሐዲስ(በሰሒህ) ያልተነገጉ ነገር ግን ሰዎች ስሜታቸውን በመከተል የፈበረኳቸው የአላህ ሳይሆኑ የሰዎች በዐላት ናቸው።

➡️ ይህ ማለት መውሊድ፣ዐሹራ እና ሸዋል ፍች ኢስላማዊ በዐላት ሳይሆኑ ኢ_ኢስላማዊ በዐላትና ኢስላም ውስጥ ከሚተገበሩ ከቢዳዓ ተግባራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

➡️ እስኪ ነብዩ ﷺ ኹጥባ ሲያነቡ ሁሌም ሳያነቡ ማያልፏትን ዐረፍተ ነገርን እናስታውስ…

⬅️ وشر الامور محدثاتها وكل محدثة بدعة وكل بدعة ضلالة وكل ضلالة في النار》

《በዲን ውስጥ የነገራቶች ሁሉ መጥፎ(ሸር) ተግባር ማለት ከመሰረቱ በዲን ያልነበረና ወደ በወኋላ አዲስ የሚፈጠር መጤ ነገር ነው፣ አዲስ ነገር ሁሉ ደግሞ መጤ(ሰርጎ ገብ) ነው፣ በዲን ውስጥ ከጅምሩ ያልነበረ አዲስ መጤ ተግባር ደግሞ ጥመት ነው፣ እያንዳንዱ የጥመት ተግባር ደግሞ የእሳት ድርሻ ነው(ለእሳት የሚያበቃ ነው》ብለዋል።

➡️ መውሊድ፣ዓሹራና ሸዋል ፍች በቁርአንና በትክክለኛ ሐዲስ እስካልተደነገገ ድረስ ማንም አለ ብሎ ይናገር ማን ንግግሩ ውድቅ(ረድ) ሊደረግ ግድ ነው።

⬅️ عن أم المؤمنين عائشة رضي الله عنها قالت : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد ) رواه البخاري ومسلم ،

《ዓኢሻህ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና ባስተላለፈችው ሐዲስ ነብዩ ﷺ《በዚህ ዲናችን ውስጥ ከጅምሩ ያልነበረን ነገር ያስገኘ ሰው ያ ያስገኘው ነገር ሊስተባበል(ረድ) ሊደረግ የሚገባ ነው።》ብለዋል።

📚ኢማሙ ቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

⬅️ وفي رواية لمسلم : ( من عمل عملاً ليس عليه أمرنا فهو رد ) .

《በሌላ የነብዩ ﷺ ንግግር《አንድ ሰው የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ነገር በዲን ውስጥ ከተገበረ ይህ ተግባሩ ሊስተባበል(ውድቅ) ሊደረግ የሚገባ ተግባር ነው።》 ብለዋል።

📚ሙስሊም ዘግበውታል።

➡️ ነገ በአብዛሀኛው ባህልን ዲን አድርገው በሚገነዘቡና ዲንን በባህላዊ መንገድ በዘልማድ በሚያራምዱ የህብረተሰባችን ክፍል ዘንድ የሚከበረው የሸዋል ፍች በዲን ስም ከሚከበሩ ሰው ሰራሽ አመት_ በዓሎች(ዒዶች) መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ይህንን የቢዳዓ በዓልን የሚያከብሩ ሰዎች ከዲን የሚፃረር ባህላዊ እምነት እያከበሩ መሆናቸውን በሚገባ ሊያውቁ ይገባል።

➡️ ማንኛውም ከዲን ተፃራሪ አስተምህሮትና ተግባር ደግሞ በኢስላም ውስጥ አፍራሽ አመለካከት ነው።

👌በመሆኑም በቁርአንና በትክክለኛ የነብዩ ﷺ ሐዲስ የተደነገገውን ብቻ በመከተልና በመተግበር እንዲሁም በቁርአንና በትክክለኛ(በሰሒህ) በነብዩ ﷺ ሐዲስ ያልተደነገገን ነገር በሙሉ በመፀየፍና በመራቅ የትክክለኛው የኢስላም አስተምህሮት የሱና(የሰለፊያህ) ተከታይና አራማጅ መሆን የእያንዳንዱ ሙስሊም የነፍስ ወከፍ ግዴታ ነወ።

✍ አቡ ኢብራሂም
ግንቦት 22/09/2012 ዓ ል
ሸዋል 07/09/1441 ዓ ሂ

ሽርክና ቢዲዓን እንጠንቀቅ📥
http://t.me/AbuLoveHome
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል📥
https://t.me/KunSelefiyeAllMineOfIniformation

ግሩፕ📥
https://t.me/PomeChannelGroup
📤📤📤📤📤📤📤📤📤📤


ትንሹ ዒድ ባህላዊ በዓል ወይስ እንደ አምልኮ ዘርፍ የተያዘ ቢድዐ?!

ቅድሚያ ለተውሒድ /


ከዒደል ፊጥር ማግስት ጀምሮ የሚፆመውን 6ቀን የሸዋል ፆምን ተከትሎ ዒደል ፊጥር በወጣ በሳምንቱ የተወሰኑ ሙስሊሞች ዘንድ የሚከበር የሸዋል ፍቺ ወይም ትንሹ ዒድ በመባል የሚታወቅ በዓል አለ። ይህ በዓል እንደ ሸሪዓ ምንም አይነት ማስረጃ የሌለው በዋናነት ወደ ደቡብ ያሉ ጥቂት ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበር መሰረተ ቢስ የሆነ በዓል ነው። በተለይ አላህ ምንም አይነት ማስረጃን ያላወረደበት ይህ በዓል ስልጤና ጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ በልዩ ሁኔታ የሚከበር በዓል ነው። ዲናችን ሙሉ ነው። ከሁለቱ ዒድና ከሳምንታዊ ጁምዓ ውጪ ምንም ይሁን ምን አዲስ ፈጠራ ነው። በዲናችን ላይ አዲስ ፈጠራ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በየ ሳምንት ጁምዓ ኹጥባቸው ላይ እንዲህ ይሉ ነበር:–

 «…የነገሮች ሁሉ ሸር ማለት (በዲን ላይ) አዲስ ፈጠራ ነው፣ አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ሁሉ ጥመት ነው» ሙስሊምና ነሳኢይ የዘገቡት ሲሆን ነሳኢይ «ጥመት ሁሉ የእሳት ነው» የሚል ጨምሯል፣ ሰነዱም ሶሂህ ነው።


ይህ በዓል ከላይ የጠቀስኩላችሁ ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበር መሰረቱ ገጠር የነበረ ቢሆንም ከጊዜ ወዲህ ግን በየ ከተማውም በተለየ መልኩ ሌሎች ብሔረሰቦችም ተሳትፈውበት መከበር ጀምሯል። ለበዓሉም ልክ እንደሌሎች በሸሪዓ እንደተጠቀሱ በዓሎች (እንዲያውም በበለጠ መልኩ) የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ይስተዋላል። ታዲያ ማስረጃ የሌለው በዓል እስከሆነ ድረስ ምንም ይሁን ምን፣ መውሊድን ጨምሮ መላው የአለማችን ህዝብ ቢያከብረው እንኳን ቢድዐ ከመሆን አይወገድም!!፣ ቢድዐ ደግሞ ጥመት ነው፣ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።


በትንሹ ዒድ ላይ አንዳንድ ስለ ዲናቸው ግንዛቤ አላቸው የሚባሉ፣ ሸሪዓው ከሚያግራራው ውጪ እያግራሩ ህዝብ ዘንድ ተደማጭነት ለማግኘት የሚዳክሩ ሰዎች የሚያነሱት ብዥታ አለ። እሱም "ምን ችግር አለው? ቢከበር ባህል ነው እንጂ ሃይማኖታዊ ይዘት የለውም" ይላሉ።


1ኛ, ባህላዊ በዓል ቢሆንስ በዚህ መልኩ በየ አመቱ እየጠበቁ በድምቀጥ ማክበሩን ማን ፈቀደው?

ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢምሙ ዐብዲልዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁላህ) በውስጣቸው ሸሪዓን የሚፃረር ነገር ባይኖርባቸው እንኳን እንደ ባህል (ልማድ) ተደርገው የሚከበሩ በዓላትን በተመለከተ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ:– “ከሁለቱ ዒዶች ውጪ ማንኛውንም ዒድ አድርጎ መያዝ አይፈቀድም!። የእርዱ ቀን ዒድ (ዒደል አድሃ) እና ዒደል ፊጥር፣ እነዚህ ናቸው የሙስሊሞች ዒድ ማለት፣ እንዲሁም በየ ሳምንቱ የሚመጣው የሚሰገድበት እለተ ጁም ነው። በተረፈ በየ አመቱ የሚሽከረከር የሚሰባሰቡበት የሆነን ዒድ መያዝ መሰረት የሌለው ተግባር ነው። ከነቢዩ  (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በኋላ ሶሃቦችም ይሁኑ ታቢዒዮች 3ቱ ክፍለ ዘመናት ውስጥ የነበሩ ትውልዶችም እንዲህ ያሉ በዓላትን አላከበሩም!። በኛ ላይ ግዴታው እነሱ የተጓዙበትን መከተልና በመንገዳቸው መጓዝ ነው… ሰዎች መልካም ነው ብለው የሚያስቡት የሚደጋገም ባህል ካላቸው ሀቁን ካወቁና ከተረዱ በኋላ ያንን ባህል መተው ግዴታ ይሆንባቸዋል…” [የሸይኹ ዌብሳይታቸው ላይ በድምፅም በፅሁፍም አለ።]


2ኛ, እንደ አምልኮ ዘርፍ ነው የሚይዙት። 

1, ለዒደል ፊጥ ከሚያደርጉት ዝግጅት የበለጥ ለዚህ ቀን ነው  የሚዘጋጁት።

2, በዋናናት አባቶችና እናቶች የሸዋልን 6ቀን አከታትለው የሚፆሙት የዚህን ቀን ፍቺ ለማክበር ነው።

3, በተጋነነ መልኩ ለዒደል ፊጥር ሀይላቸውን ቆጠብ አድርገው ለዚህ ቀን ግን ሀይላቸውን አሟጠው ይጨርሱና ከፊታችን ለሚመጣው ዒደል አድሃ እንኳን በቂ ዝግጅት አያደርጉም። ለዚህም ነው ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች "አንድ ቢድዐ በተተካ ቁጥር ሌላ አንድ ሱንና ይሰርዛል" የሚሉት።

4, ዝግጅቱን በዋናነት የሚያከብሩ ሰዎች ሲጠየቁ የሸዋል 6ቀን ፆም ፍቺ (ዒድ) ነው ብለው ነው የሚናገሩት እንጂ ባህል ነው የሚል አመለካከት የላቸውም። ይህ አመለካከት ጠንካራ አቋም ያላቸው የሱና ሰዎች "ትንሹ ዒድ ቢድዐ ነው" ብለው ሲያስጠነቅቁ እነ ሸህ ገራገር ህዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት ለማግኘት ሲጠየቁ የፈበረኩት አመለካከት ነው። ይህን አመለካከት ሲፈበርኩ ግን ይህን ሁሉ እውነታ ያውቁታል። እያወቁ ሀቁን ይደብቁታል፣ ያምታቱታል። ይህ ደግሞ አላህ እንዲህ በማለት አይሁዶችን የወቀሰበት አደገኛ ተግባር ነው:–


وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

 

«እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡» አል በቀራህ 42


እንዲህ ያሉ በዓላት ላይ ሌላው ከባድ አደጋ!! የተለያዩ የኢስላምና የሙስሊሙ ጠላቶች እንዲህ ያሉ አዳዲስ በዓላትን ቀና መስለው በተለየ መልኩ በየ ሚዲያዎቻቸው እያስተዋወቁ ሙስሊሙ በሀይማኖቱ ከተደነገጉ ብርቅዬ በዓላት እንዲዘናጋ ይሰራሉ።

ወላሁ አዕለም!!

✍🏻 ኢብን ሽፋ: ሸዋል 6/1441 ዓ. ሂ
https://t.me/AbuLoveHome


عيدكم مبارك!
تقبلﷲ منا ومنكم صالح الأعمال!
ኢዳችሁ የተባረከ ይሁን!
አላህ ከኛም ከናንተም መልካም ስራችንን ይቀበለን
አሚን
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ወንድማችሁ፡ አቡ ተቅይ ቃዒድ


በሀገራችን በተለይ በገጠሩ ክፍል በሀይለኛው ሽርክ ተጠናውቶት ይገኛል ። በተለይ ተወልጀ ባደኩበት ወሎ አከባቢ በአፄዎቹ ተፅኖ እምነት እና ባህሉ ተደባልቆበት ይገኛል።
ከአከባቢየያችን በቂ የድን ትምህርት ስለማይሰጥ ለስራ ወደ አድስ አበባ የሚመጡ ሰዎች እምነታቸውን የሚቀይሩ ሰዎች ብዙ ናቸው። በአከባቢው  ያሉ ሰዎች አብዘሀኛው ሰው ሰላት አይሰግድም ፆም ብቻ  ይፆማሉ ፣ለጅን ይገብራሉ ማክሰኞ ኑሩ ሁሴይን ረቡዕ አብዶየ አንዳንዶችም ዛሬ አቦ ፣ገብርኤል ፣ፃድቁ ነው ወዘተ በማለት ቀኑን ስራ ባለ መስራት የሚያከብሩ ሰዎች ብዙ ናቸው።
ከእንደዚህ አይነት ማህበረሰብ የወጣን ብዙ ሰዎች አለን ስለዚህ ይህ የተረሳውን የገጠሩን ማህበረሰብን ተውሂድን ተደራሽ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ ለመፍጠር ይህን ግሩፕ ከመሰረትንበት አላማ አንዱ ነው።


ለዚህ ወደዚህ ግሩፕ የምትገቡ በሙሉ አላማውን አውቃችሁ ለዚህ በጎ ተግባር በምንችለው እንተባበር እላለሁ።


http://t.me/sunnacom


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሰሞኑን ጥቂት ወንድሞች በራስ ተነሳሽነት የከፈቱት የቴሌግራም ግሩፕ አለ። የግሩፑ አላማ ውስጥ ላይ የተገለፀ ቢሆንም እዚህ ላይ በአጭሩ ለመጠቆም ያክል በሃገራችን ያለውን የተውሒድና የሱና እንቅስቃሴዎችን ማጠናከርና በተሻለ መልኩ ማገዝ ነው። አላማውን አቅሙ በሚፈቅደው ለመደገፍ ፍላጎቱ ያለው በዚህ ሊንክ በመቀላቀል የዘመቻው አካል መሆን ይችላል።

http://t.me/sunnacom


#ከወንድም_ሳዳት_ከማል🔻
እንኳን ለተከበረው ታላቁ የረመደን ወር አደረሰን።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! የሚከተሉትን ነገሮች ነፍሴንም እናንተንም አደራ ልላችሁ እወዳለሁ
1) አደራ በተውሒድ ላይ፣ አደራ ሺርክን በመራቅ ላይ
አላሁ ሱብሃነሁ ወተኣላ "እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ፆም በናንተ ላይ ተደንግጓል…" ነው ያለው። ያመናችሁ ሰዎች የሚለው ላይ አስምሩበት። የተበላሸ እምነት፣ ተውሒድን የሚፃረር ሺርክ እኛ ላይ ካለ አላህ ብንፆምም አይቀበለንም።
2) አደራ በሱና ላይ፣ አደራ ቢድአ (በዲን ላይ አዲስ መጤ ጉዳዮችን) በመራቅ ላይ
በረመዳን አብዛኛው ሰው በስሜት ተነስቶ ያልተደነገጉ አምልኮዎችን መፈፀም ይፈልጋል።
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) "የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (አላህ አይቀበለውም)።" ብለዋል
3) አደራ በሰላት ላይ
ሰላት ታላቅ አምልኮ ነው። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሰለትን የተወ ከሃዲ እንደሆነ ተናግረዋል። ለአለማቱ ጌታ በስግደት ያልተደፋች ፊት ምንኛ በደለኛ ናት።
ሰላትን ትቶ መፆም በሀይማኖት ላይ መቀለድ ነው።
3) አደራ ቅርኣንን በመቅራት፣ በመስማት ላይ፣
4) አደራ በቸርነት ላይ
የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቸር ነበሩ ይበልጥ ቸር የሚሆኑት ደግሞ በረመዳን ወር ነው። በግማሽ የተምር ፍሬ ሰደቃ ነፍሳችሁን ከእሳት አድኑ የሚል ታላቅ ሃይማኖት አላህ ሰጥቶናል።

አላህ በሰላም ፆመን፣ መስጂዶቻችን ድጋሚ ተከፍተው፣ ተውሒድና ሱና የበላይ ሆኖ ሺርክ እና ቢድአ የበታች ሆነው ለማየት ያብቃን።
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
@SadatTextPosts
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ
ግሩፕ📥
https://t.me/PomeChannelGroup
📤📤📤📤📤📤📤📤📤📤


ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል📥
https://t.me/KunSelefiyeAllMineOfIniformation

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹


👉 አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
የተከበራችሁ የሱና ቤተሰቦች የረመዳን ወር ጨረቃ ስለታየች ነገ ጁምዓ ረመዳን አንድ ነው
አላህ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስጨርሰን
ይህንን ፈተና አንስቶ ወደየ መስጂዶቻችን ይመልሰን


بسم الله الرحمن الرحيم المقدمة إن الحمد لله، نحمده ونستعينه ونستغفره، ونعوذ بالله من شرور أنفسنا وسيئات أعمالنا، من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمداً عبده ورسوله، صلي الله عليه وعلى آله وأصحابه ومن تبعهم بإحسان إي يوم الدين وسلم تسليناً كثيراً. أما بعد:

اسلم عليكم ورحمة الله وبركاته
እንዴት ናችሁ ውድ #የኩንሰለፍያአለልጀዳአሰለፍይመነሀጅኦፊሲላዊቻናል እና በስሩ በሚገኘው የቻናል፣ የግሩፕ እንድሁም የቦት አባላቶች በሙሉ።
አላህ ሱበሀነ ወተዓላ ከክፉ ነገር ይጠብቃችሁ።

እንደሚታወቀው አሁን ላይ መደበኛውም ሆነ በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በጣቢያዎቼ መረጃዎች እየደረሷችሁ አይደለም፣ ምክንያቱ ደግሞ አሁን ባለንበት አስገዳጅ ሁኔታ ከቤት ቁጭ ብለን ስለሆነ፣ ለኢንተርኔት አገልግሎት ምቹ ሁኔታ ላይ አይደለሁም ። በመሆኑም በዱዓችሁ አትርሱኝ፣ ሁላችንም ካለንበት፣ ከመጣብን በላዕ አላህ እንዳነሳል ዱዓ እናድርግ።

ቀጣይም ምን እንደሚሆን ስለማላውቅ እናንተ ትጠቀሙበት ዘንድ የሚከተለውን #ሊንክ በመጠቀም የሱና ወንድሞችን ቻናል ተቀላቅላችሁ ፣ ትምህርቱንም ሆነ ወቅታዊ ሁኔታን ተከታተሉ።
ባረከሏሁ ፊኩም
ሊንኩ በርካታ ሊንኮችን አካቶ የያዘ ነው ተጠቀሙበት።📌📌📌
🌹የሱና ሊንኮችን በመቀላቀል ተከታተሉ📌 - https://t.me/AbuTekiyKunSelfiya/92


Репост из: አቡ ሙዓዝ (ሐሰን ኢድሪስ)
#ሳዳት ከማል

ወንድማችን ሳዳት ከማል (ሐፊዞሁሏሁ ተዓላ)
እንድህ አለ

"የሽርኩ ንጉስ ሙሐመድ አወል ከኮረና በላይ ነው አይደለም?
ኮረና ይዞ ቢያስነጥስህ ሽርክ ይይዝሃል?"

http://t.me/abumuazhusenedris




Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በኮቪድ 19 (ኮሮና ቫይረስ) ጉዳይ ብዙ ሰው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እየገባ ነው። በመጨነቅ የሚቀየር ላይኖር መጨነቅ አያስፈልግም። ይልቁንም የሚያስፈልገው:–
① ስለበሽታውና ጥንቃቄዎች በቂ ግንዛቤ መያዝ፣
② ተጋላጭነትን ከሚጨምሩ ነገሮች መጠንቀቅ፣ ከአላስፈላጊ ቅልቅል በመታቀብ ሰበቡን ማድረስ፣
③ የተያዘንም ሆነ ያልተያዘን የሚመለከተውን ሸሪዐዊ ህግ መጠበቅ (በሽታው ወዳለበት ሃገር አለመሄድና በሽታው ካለበት አለመውጣት)፣
④ በሽታው አገር ውስጥ መግባቱ ኦፊሻሊ ቢነገር ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ነገሮች በማሰብ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ፣
⑤ ዱዓእና ዚክር ማድረግ፣
⑥ ህመሙ ካጋጠመ ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ ጥንቃቄ መውሰድ፣ ሃኪም ማማከርና አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ፣
⑦ የበሽታው የገዳይነት ደረጃ እስካሁን እየተዘገበ ባለው ከ2%–4% ብቻ ነውና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ መግባት አይገባም። ከዚያህም የከፋ ቢሆን ከአማኝ የሚጠበቀው በጌታው ላይ ያለውን ተስፋ ከፍ ማድረግ ነው።
⑧ የሚመጣው አይታወቅምና ለማንኛውም ነገር እራስን ማዘጋጀት። እዳ ካለ በመክፈል፣ ተውበት ማድረግ። ሙእሚን እያንዳንዱን ክስተት ወደጌታው ለመቃረብ ነው የሚጠቀመው።

Показано 20 последних публикаций.

510

подписчиков
Статистика канала