እንማር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Цитаты


እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯 መፅሀፎች
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
የተለያዩ PDF መፅሐፍት እንደፍላጎቶ አሉ
    Ads - @Kiya988
https://youtube.com/channel/UCr7-LDddhyqtFUCH0OHhM2Q
Buy ads: https://telega.io/c/Enmare1988

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Цитаты
Статистика
Фильтр публикаций


ስሜታዊ ሆኖ ለተናገረን ፣ ሊረዳን ፈልጎ ለሳተ ፣ ኑሮ አስክሮት ለገፋን ፣ ንዴት ገፍቶት ላጠፋ ፣ ግዜ አጣሁ ብሎ ላልጎበኘን ፣ ስናሸንፍ ላላጨበጨበ፣ ስንወድቅ ላላነሳን ፣ ስናስብለት ላልተረዳን ፣ ማደጋችንን ላላየ...

...."ትንሽ ቦታ ለይቅርታ..." ማዘጋጀት ይጠበቅብናል።

አማረልን ብለን ላሳዘንን ፣ አጉል ተስፋ ለሰጠነው ፣ ውድቀቱ ላይ ለሳቅነው ፣ ማድረግ ችለን ላላደረግነው ፣ ችለን ለተጣመምነው ።

ለራሳችንስ ይቅርታ አደርገናል...?

መልካም ቀን!

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988


📚📚መጽሐፍ መዋስ ወይም መግዛት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ ምንም process በሌለውና በቀላሉ ለመዋስ እንዲሁም ለመግዛት በ ስ.ቁ
0900973100 እና 👉 @DASH_Book ላይ ማዘዝ ትችላላችሁ።

አድራሻ፦ 4 ኪሎ ሲሆን ለመዋስ መስፈርቱ
📍የተለያዩ ማንነትን የሚገልፁ ነገሮች (መንጃ ፈቃድ፣  ፍይዳ መታወቂያ ፣የቀበሌ መታወቂያ...)
📍 የመጽሐፉን ዋጋ አስይዘው መዋስ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ እንዲሁም፤

✔️የመጽሐፍ review
✔️የተለያዩ ጠቃሚ እና አዝናኝ ጽሁፎች
✔️ አድስ የሚወጡ መጽሐፎችን ማሳወቅ
✔️ የራሳችንን ገጠመኞች እና ጽሁፎች የምናስተላልፍበት ( በውስጥ መላክ ትችላላችሁ)

+++  የመጽሐፍ event ሲኖር፣ የመጽሐፍ ምርቃት ሲኖርና በአጠቃላይ ከመጽሐፍ ጋር የተገናኙ ማንኛውንም ነገር እንዳያመልጥዎ ከፈለጉ Join 👉


✈️@DASH_Book_Reviews
✈️@DASH_Book_Reviews
✈️@DASH_Book_Reviews


ሌላ ሴት ልታገባ ያልክ ቀን እንኳ ብደውልልህ እሷን ትተህ እኔ ጋር ነው አይደል የምትመጣው...? እለዋለሁ ሁሌ ….

ፈገግ ብሎ ያየኝና “ደፋር ኮ ነሽ….ይለኛል።

ካለው ነገር ሁሉ እኔን አስበልጦ እንደሚወደኝ ጠንቅቄ አውቃለሁ...

ሲሳሳልኝ...ከራሱ ሲያስቀድመኝ...ሲጨነቅልኝ...ለኔ ሲኖር ዓይቻለሁ።

....በእርግጥ እንዲ ማለት ከባድ ይመስላል።

እኔ ግን ዓይኑን ሳያርገበግብ...ይሄን ልጅ ግን ምን አስነክታው ነው እስኪባል... የሚያውቁን ሁሉ እስኪገረሙ ድረስ ሳናድደዉ... እና ሳበሳጨው ችሎ በክፉ ቀናቶቼ ላይ ለደስታዬ ሲፈጋ አብሮነታችንን ለማቆም ብዙ ሲለፋ አውቅ ነበር....

ይመስለኛል የበዛ መውደዱ.... የትም አይሄድም ብዬ እንዳስብ... ለኛ እንዳልጨነቅ እና በተወዳጅነት ተኮፍሼ ለሚሰጠኝ መውደድ እና ክብር ትንሽ እንኳ አፀፌታን መስጠት የማልችል ሴት አድርጎኛል...

ከዛ በአንዱ ቀን በትንሽ ነገር ተጋጨን እና ….ሂድልኝ አልኩት...

ለመነኝ አስለመነኝ…ከቀልቤ መሆን ያልቻልኩት እኔ ግን ግድ አልሰጠኝም እና ምንም እንደጎደለብኝ አልተሰማኝም።

መሄዱ እንደሚያም እንዴት እንደሚናፍቀኝ ለመረዳት ብዙ ረፈደብኝ...

ሄደ...

ከዛ አልተመለሰም...

ልመልሰዉ ሞከርኩ…መሄድ አለማምጄው ኖሮ መመለስ አቃተኝ...

እናማ አሁን የገፋሁት እኔ....ወዶኛል አይጠላኝም ያልኩት እኔ በተራዬ እጅግ እየናፈቀኝ...እያመመኝ...ነው።

እያስመሰልኩ አብሮነታችን ማክበር ያልቻልኩት እኔ … ሲያቅፈኝ ሕይወት እንደሚቀለኝ ችግሮቼን ችሎ ማሸነፍ ብቻን ያለማመደኝ እሱ እንደነበር...በጣም እንደሚናፍቀኝ...በጣም እንደማመሰግነው ያልነገርኩት እኔ...

....የሄደበትን ቀን ሻማ እያበራሁ አስታውሰዋለሁ።

(ወግ ብቻ)
(በማ
ሂ )

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

4.9k 0 39 6 144

እድሜያቸው በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ፓርቲ ለማድረግ ሲቀጣጠሩ የመረጡት ቦታ "አክሰስ ክበብ" የሚባል ቤት ነበር

ምክንያት? - ሙዚቃቸው ቀውጢ ነው: አስተናጋጆቹ ቆንጆ እና ቀበጦች ናቸው: ነጻ ዋይ ፋይ አላቸው: ሺሻቸው ምርጥ ነው: ለመጠባበስ አሪፍ ቦታ ነው

***

እነዚሁ ወጣቶች ከ10 አመት በኃላ በ30 አመታቸው ለመገናኘት ሲቀጣጠሩ የመረጡት ቦታ "አይቢኤም ሆቴል" ነበር

ምክንያት? - ለማውራት ይመቻል: ዋይፋይ ጥሩ ነው: የማጨሻ ቦታ አላቸው: ጫጫታ እምብዛም የለም: መገፋፋት የለበትም :አስተናጋጆቹ ምቾት አይነሱም: ለጠበሳም እድል አለ😂

***

ወጣቶቹ በድጋሚ በ40ዎቹ እድሜያቸው ለመገናኘት ሲወስኑ የመረጡት ቦታ "ሰሪኒ ላውንጅ" ይባላል

ምክንያት? - ዝምታው ደስ ይላል: የወይን እና ኮክቴሎች አማራጭ አላቸው:ወሚከፍቱት ሙዚቃዎች የቆዩ ናቸው:  ምግባቸው ቅባት የበዛበት አይደለም: የሚንቀዠቀዥ ሰው በብዛት የለም

****

እነዚህ ወጣቶች በ50ዎቹ የእድሜ ክልል ሲገናኙ የመረጡት ቦታ "አንባ-ራስ" ሆቴል ነበር

ምክንያት? - የዛፎቹ እና የአበባዎቹ ውበት ልዩ ነው: ሀይቁን ማየት ይቻላል: ሙዚቃቸው ክላሲካል ነው: ሱሪያቸውን አውርደው ፓንታቸውን የሚያሳዩ ወጣት ወንዶች አይመጡበትም: ለአይን ምግብ የሆኑ ቆንጅዬ ወጣት ሴቶች ይመጡበታል

****

እነዚህ ጏደኛሞች በ60 አመታቸው ሲገናኙ የመረጡት ሆቴል "ኤደን ገነት" ሪዞርት ነበር

ምክንያት? - ሪዞርቱ ለአስፋልት ቅርብ ነው: ሽንት ቤቶቹ ብዙ ደረጃ የሚያስወጡ አይደሉም: ወንበሮቹ አይቆረቁሩም: ምግባቸው ጨው እና ቅባት አይበዛበትም: አስተናጋጆቹም የደስ ደስ ፈገግታ ያላቸው ናቸው

*

በ70 አመታቸው ለመገናኘት የመረጡት ቦታ "እፎይታ ሆቴል " ነበር

ምክንያት? - የድሮ ትዝታዎችን እያወሩ ለመጫወት ዝምታው ደስ ይላል: አልኮል በብዛት አይሸጥበትም: የኮት ማንጠልጠያ እና የከዘራ ማስቀመጫ አላቸው

ሰው እና እድሜ

🙌🏼❤️
Repost

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

5.8k 0 44 7 191

አንድ ሰው ሚስቱ ጋር ወደ መካነ አራዊት (Zoo) ተጉዘው እየጎበኙ ሳለ፤

ከሚስቱ ጋር በስሜታዊነት የሚጫወት ዝንጀሮ አገኙ። ሚስትየዋ ይህን ስትመለከት እንዲህ አለች፤

"ምን አይነት ፍቅር ነው ?"

በመቀጠል አንድ ወንድ አንበሳና ሴት አንበሳ ተለያይተው አገኙ።  ወንዱ አንበሳ ሴቷ አንበሳ የሌለች ያህል ርቆ ተቀምጧል።  ሚስትየዋ ይህን ስትመለከት እንዲህ አለች:

"ፍቅር የሌለበቴ እንዴት ያለ አሳዛኝ ትዕይንት ነው።"

ከዚያም ባለቤቷ እንዲህ አላት  "አንቺ እሄን ድንጋይ ወደ ሴቷ አንበሳ ወርውሪው እና ተመልከቺ።" አላት።

እሷም በወረወረችው ጊዜ አንበሳው አንበሳዋን ለመከላከል እያገሳ ዘለለ። ተገረመች፣ ባልዋ ያንኑ ትዕይንት እንድትደግም አደረገ።

  እሷም ድንጋዩን ወደ ዝንጀሮዎቹ እንደገና በመወርወር ተመሳሳይ አደረገች፣ ዝንጀሮውም ዘሎ ራሱን ለማዳን ሴቷን ትቷታል ዛፍ ላይ ወጣ።

ባሏም በኋላ እንዲህ አላት።

"በአንዳንዶች ዘንድ እንደ ሮማንቲሲዝም በምታዩት ነገር አትታለሉ። ብዙ ጊዜ ባዶ ልብን የሚደብቅ አሳሳች መልክ ነው፣ ሌሎች ምንም ፍቅራቸውን ሳያሳዩ ነገር ግን ልባቸው በቅን ፍቅር እና እንክብካቤ የተሞላ ነው።"

እንደ አለመታደል ሆኖ ዛሬ እኛ በጣም ብዙ ዝንጀሮዎች እና ጥቂት አንበሶች
አሉን።

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

5.9k 0 90 5 196

እማማ አፀደ የሚባሉ ጎረቤት አሉን የእናቴ ጓደኛ ናቸው። እማማ አፀደ አመም አድርጓቸው ሕመማቸው በባሰ ቁጥር እናቴን ጠሏት።

ይሰድቧታል... ሌባ ናት...መሠሪ ናት...ልትገለኝ ትፈልጋለች...መርዝ አበላቺኝ ይላሉ።

አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ።

.... ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ።

....ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ።

እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች...

ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....

እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች።

በእህታቸውን ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...

ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል....

እቆጣታለሁ "ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?"....እላታለሁ!!

"ጭንቅላታቸው ዕጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ፤እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም"...ትለኛለች

በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን ትገዛላቸዋለች።

እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ...ድግምታም... ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ።

እኔ ጠላኋቸው... !!

አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም...? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት

"ጓደኛዬ ናቸው..! እዚህ ሠፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ።

ዕድር ያስገቡኝ... የሌለኝን ዕቃ ያዋሱኝ...የተቆረቆሩልኝ....የአረሱኝ ....የመከሩኝ...እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው።

ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት....ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...

በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም...!!

የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው...

...በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም።

አፀዱ እንዴት ዓይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ሕመም ተጣብቷቸው እን'ጂ...

ስንት ቀን መሰለህ እጦት በእርሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው....

አፀደ ደግ ....ሩህሩህ ናቸው...

እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...

የአፀደ ውለታ አለብኝ.... !

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

6.6k 0 12 2 169

እኩለ ለሊት አልፏል። እንቅልፍ በአይኔ መዞር ካቆመ ሰነባብቷል። ዞሬ ሳየው ገፅታው ሰላማዊ ነው። እሱ ብቻ ነው ወይስ ሁሉም ሰው ሲተኛ ያሳዝናል? እንደህፃን ያሳሳል።አተኛኘቱ ጥፋት የሌለበት ንፁህ ያስመስለዋል።

ዳሩ እሱ ምን አጠፋ?! አንደኛ ደረጃ ተማሪ ሆኜ ከመፅሀፌ ጀርባ የፃፍኩትን የ"ምርጥ ባል" ደረጃ በሙሉ ያሟላል።እኔ ነኝ የእሱን የምርጥ ሚስት ደረጃ ማሟላት ያልቻልኩት።

ችግሩ ማለቴ ችግሬ ምንድነው? መውደድ ረስቻለሁ ወይ ጠፍቶብኛል ነው። ብዙ ቦታ ልቤን አባክኜው ነው መሰለኝ አሁን ስመኘው የነበረው ሰው እግዜር እንኪ ሲለኝ መቀበል ያቃተኝ

የለመድኩት መከልከል ነው እድሌ ወስዶ የሚጥለኝ ጭራሽ እጣ ክፍሌ ካልሆነ ሰው ጋር ነበረ። እልል ያለ ፍቅር ውስጥ ነኝ ተዉኝ ብዬ ማወጅ ስጀምር ድንቅፍቅፉ እየበዛ ምናልባት ለእኔ ባይለው እያልኩ ያተኮሰችውን ልቤን ማብረድ ነበረ የለመድኩት። አሁን እንኪ ይኸው የተፈቀደልሽ ስባል በየት በኩል ልብ በግድ ውደድ ይባላል?!

አታለልኩት እንዳልል እዚህ ደረጃ ሳንደርስ ገና ጓደኝነታችን ድክ ድክ ማለት ሲጀምር ነግሬው ነበረ የሚሆን አይመስለኝም ብዬው ነበረ። "ለጊዜው የኔ ፍቅር ይበቃል በጊዜ ሂደት ትወጂኝ ይሆናል" ብሎ ነበር የጀመርነው ከዛስ?! ሁሉም አንድ አንድ ሲሉ ጓደኞቼ "እሱ ካመለጠሽ እድሜ ልክሽን ነው የሚያንገበግብሽ" እያሉ ሲያስፈራሩኝ

የሆነ እቃ ሊያቀብለኝ ቤቴ መጥቶ እያወራን በአጋጣሚ እናቴም መጥታ ተገናኝተው ትንሽ እንዳወሩ ልሂድ ብሎ ሲነሳ ካልቆየህ ብላው እኔን ረስተው ሲጫወቱ ውለው "አትጥፋ ታድያ" ብላው ሲለያዩ

የተቋጨ ነጠላዋን ደግማ እየቋጨች "ያው በጊዜ መሰብሰብ ጥሩ ነው ሁልጊዜ እድል የለም" እያለች በዘወርዋራው እንዳገባው እንደፈለገች ስትነግረኝ

"ምነው እድሌን ባልዘጋ ምናልባት በጊዜ ሂደት እወደው ይሆናል" ብዬ ከጓደኝነት የዘለለ ምንም ሳይሰማኝ አገባሁት።

ያጎደለው ነገር ቢኖር እኮ ለሁሉም መልካም ነበረ። ያልሞቀ ያልበረደ ማንነቱ ለፀብ እንኳን አልመች አለኝ። ሌላ ሰው ቢሆን አይናደድም ወይ ትግስቱ አያልቅም እላለሁ እንደሱ ልትወደው ሴት ይገባው አልነበር እላለሁ።

እንደዚህ እንቅልፍ አጥቼ እያየሁት ስፀፀት ወደራሱ ጎተት አድርጎ ያቅፈኝና "ብዙ አታስቢ በጊዜው ሁሉም ይሆናል አሁን ተኚ" ይለኛል

✍ናኒ

https://t.me/justhoughtsss

6.8k 0 28 16 138

Репост из: Thoughts


አለን 🙌❤

መወደዳችንን አንለምደውም ፣ስንፈለግ ትርጉም ይሰጠናል ፣ አልነበርንም ከማለታችን በፊት የት ጠፋህ ስንባል ደስስ ይለናል ፣
ሃብታችን ወዳጆቻችን ናቸው ።
መመኪያችን አምላካችን ነው ። በፈተናችን ለመፅናት እንታገላለን ። ያለን እንዲታወቀን እምንፈልገው እንዲገለጥልን እንፀልያለን ።

ህይወት ከከበደችው በላይ እንዳናከብዳት ጥበብ እንቃርማለን ። ሃዘናችንን አናጎላውም ለእጦታችን ፊት አንሰጥም ደስታችንን ችላ አንልም

ኻዬ❤

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988


የመጀመሪያዋ ላትሆን ትችላለህ፣ የመጨረሻዋም ወይም ብቸኛዋ ላትሆን ትችላለህ። ከዚህ በፊት አፍቅራ ታውቃለች እና ደግማ ልታፈቅርም ትችላለች። ግን አሁን አንተን ካፈቀረችህ፤ ሌላው ምን ለውጥ ያመጣል?

ፍጹም አይደለችም፣ አንተም አይደለህም፣ እና ሁለታችሁ መቼም ፍጹም አትሆኑም። ግን ቢያንስ አንዴ እንኳን ልታስቅህ የምትችል ከሆነ፣ ሁለቴ ደግመህ እንድታስብ፣ ሰው መሆንህን አምና ከነእንከንህ ከተቀበለችህ እንዳትለቃት፤ የምትችለውን ሁሉ ስጣት።

ለአንተ ብላ ቅኔ አትቀኝም፤ ሁሉንም ሰዓት ስላንተ እያሰበች አይደለም፤ ግን ልትሰብረው እንደምትችል እያወቀች ውድ ክፍሏን ትሰጥሃለች– ልቧን!

አትጉዳት፣ አትቀይራት፣ እናም መስጠት ከምትችለው በላይ እንድትሰጥህ አትጠብቅ። ከመጠን በላይ አታስብ። ደስተኛ ስታደርግህ ፈገግ በል፤ ስታበሳጭህ ጩህ፤ እና ካጠገብህ ሳትኖር ስትቀር ናፍቃት። ፍቅሯን ስትሰጥህ በሙሉ ልብህ አፍቅራት።

ምክንያቱም ፍጹም ሴቶች የሉም፤ ግን ሁሌም ላንተ ፍጹም የሆነች ሴት አለች
!

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

7.8k 0 107 23 194

✔️የሆነ ቦታ የሆነች የተረጋጋች ሴት ያለች ይመስለኛል። የሰውን ትኩረት የማትፈልግ ፤ ሰዎች እንዲወዷት የተለየ ነገር የማታደርግ የራሷን ኑሮ የምትኖር...

✔️ህይወቷ በእውነት እንጂ በፈጠራ ድራማ ያልተሞላ ፤ ሰዎች እግረመንገድ ላይ ድንገት ዋነኛዋ ሴት የምትሆን ። የተሰማትን የፈለገችውን ደስ ያሰኛትን የምታደርግ ፤ ምታደርገው የማይፀፅታት ...

ምድር ላይ ያለውን የህይወት ብሶቷን አልያም ችግሯን ለመደበቅ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወ'ታ ከመንዘባዘብ ይልቅ ከአምላኳ ጋር የምትነጋገር። ስለራሷ እሷ እና አምላኳ ብቻ የሚያውቁ። ይህቺ ሴት ብርቱ ናት....

ለጓደኝነት ትመቻለች። ነፃነት ትሰጣለች። ለጊዜያዊ የፍቅር ግንኙነት ታስፈራለች። ወንዶች ይጠነቀቁላታል። የትኛውም ወንድ ደፍሮ ሌላዋን ሴት የሚያወራበት መልኩ ይቺን ሴት ሊያወራት አይችልም። ልባም ናት። ለዘላቂ ትዳር የምታስተማምን ሴት። የቤቱ ራስ መሆን የሚችል ፣ ሚስቱ እንድትገዛለት ሆኖ መኖር የሚችል ባል የሆነ ወንድ የሚመኛት እና የሚያገኛት ሴት ናት።

ይህቺ ሴት ብርቅ ናት ! ፀሎቷ ልኬት ያለው ይመስለኛል። ከሚያስፈልጋት በላይ እንዲሰጣት አትለምንም። ተመስገንን ታውቃለች በተሰጣት አታማርርም ።

📷pic Tuba Büyüküstün ❤ 😍🥰🙏🙏🙏🙏

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

7.6k 0 145 36 246

✅️ምርጥ ምርጥ መጽሀፎችን በስልካችሁ ማግኘት ትችላላችሁ!
የኢትዮጵያ ዲጅታል ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library)
በተጨማሪም
ለትምህርታዊ መፅሀፍቶች
ቴክኖሎጂ መፃሀፍቶች
የሳይንስ መጽሀፍቶች
ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎች
የሳይኮሎጅ መጽሀፍት
የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ መጽሀፍት
የመደበኛ ተማሪዎችን መጽሀፍትን፣
የሶሻልና የናቹራል መጽሀፎች
የዩኒቨርስቲ የመማሪያ ሀንዳውት፣
የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
የጥያቄና መልስ
ወርክ ሽቶች

✅የሚያገኙበት ትልቁ
የኢትዮጵያ ዲጅታል ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library) በመግባት ማግኘት ይችላሉ።
ጊዜው የቴክኖሎጂ ነው አብረው ከቴክኖሎጂ ጋር ይጓዙ!

👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇
✈️https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
✈️https ://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary


🟪🟥🟦
🔵የ አዶቤ ፎቶ ሾፕ ሙሉ ትምህርት በአማርኛ


🟡😄ማንኛውንም አይነት የህትመት ስራዎች ለመስራት ይጠቅማችሃል።
ትምህርቱ አዶቤ ፎቶሾፕ ሶፍትዌርን ይጠቀማል።


📱https://t.me/EthioLearning19/2591
📱https://t.me/EthioLearning19/2591


....የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደነበርን ነው...

አንድ ቀን የሆነ አስተማሪያችን ቀረ....በዛ ክፍት ክፍለጊዜ ሁላችንም ደስ ያለንን ስንሠራ ነበር

አብዛኞቻችን ወሬና መንጫጫት ላይ ነበርን።

...አንድ ምስጋናው የሚባል የክፍላችን ልጅ ብላክቦርድ ላይ በወዳደቀ ቾክ ሁለት ሰወችን ሳለ።

ሥዕል ስላችሁ ይሄ ዝም ብሎ የልጅ ሥዕል አይደለም፣ ባስታወስኩት ቁጥር የሚገርመኝ የግንባራቸው መስመር፣ ፊታቸው ላይ ያረፈው ጥላ ልብሳቸው ላይ ያለው ፓተርን ሳይቀር ፎቶ የሚመሳስሉ ፖርትሬቶች...

...ደግሞ የሳለው ምንም እያየ አልነበረም።

...እማሆይ ቴሬሳ ሁለት እጆቻቸውን እንደህንዶች ሰላምታ አገናኝተው ግንባራቸውን እንዳስነኩ እጃቸው መሀል መቁጠሪያ ተንጠልጥሎ፣ እንዲሁም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከነ ንጉሳዊ ልብሳቸው ወደጎን ዞር ብለው።

ሁላችንም በምስጋናው የሥዕል ችሎታ ተገረምን ተደነቅን።

ቀጣዮ ክፍለግዜ ጅኦግራፊ ነበር...

ኮስታራው አስተማሪያችን ገባና ሥዕሎቹን ዓየት አድርጎ "ማነው የሳለው?" አለ ።

በአንድ አፍ "ምስጋናው" አልን በአድናቆት ጭምር።

መምህሩ ወደምስጋናው ወንበር ተራምዶ የያዘው ልምጭ ተሰባብሮ እስከሚያልቅ ምስጋናውን ቀጠቀጠው።

እና በቁጣ "ይሄ የተከበረ የትምህርት ገበታ ነው ! ማንም እየተነሳ የሚፀዳዳበት አይደለም ደደብ" ብሎ ደነፋ።

ዳስተሩን አንስቶ አንዴ እጁን ሲያስወነጭፈው ኃይለስላሴን ለሁለት እማሆይ ቴሬሳን አናታቸውን ገመሳቸው።

አጠፋፍቶ ማስተማሩን ቀጠለ። ምስጋናው ከዛ በኋላ እንኳን ሰሌዳ ላይ ወረቀት ላይ ሲስል አላስታውስም።

...ብዙ ዓመታት አለፉ።

አንድ ቀን አዲስ አበባ ፒያሳ መርከብ የምትባል ምግብ ቤት ምሳ በልተን ስንወጣ በር ላይ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በፌስታል ፍርፋሪ ሲበላ ዓየሁ ምስጋናው ነበር።

ቢጎሳቆልም አልጠፋኝም ነበር።

ዛሬ በምን አስታወስኩት? አንድ አሜሪካዊ ህፃን ሰሌዳ ላይ በቾክ የሳለው ስዕል በአስተማሪዎቹ እና በትምህርት ቤቷ ርዕሰ መምህር ስለተደነቀ በቀስታ ሰሌዳውን አንስተው አንድ ቢሮ ግድግዳ ላይ እንደሰቀሉት አነበብኩ።

ሥዕሉ ለዓመታት እንዲቆይ የሆነ ነገር እናስደርጋለን ብላለች ርዕሰ መምህርቷ።

ሀገር ባከበረቻቸው ትከብራለች ባከሸፈቻቸው ትከሽፋለች።

(wegoch)
(በአሌክስ አብርሃም
)

7.9k 0 45 8 276

ይህ ደብዳቤ በ1939 በጦርነት ከሞተ ወታደር
ኪስ ውስጥ የተገኘ ነበር!💔

አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎች ከገባናቸው ቃላቶች ይበልጡና።
ቃለ-አባይ ያስመስሉናል 😢

ቃላችን እንዳይሳካ ያደረገው ያለአቅማችን መመኘታችን አልነበረም። የነገሩ ግዝፈት አቅማችንን ቀጭቶ እንዳይፈፀም አደረገብን እንጂ!

7.5k 0 55 97 185

"ትክክለኛው ጥያቄ :
ከሞት በሗላ ህይወት አለ ወይስ የለም የሚለው ሳይሆን ከመሞትህ በፊት እየኖርክ ነው ወይ??የሚለው ነው።"

osho

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

9.5k 0 57 24 209

አንድን ፈላስፋ
እውነተኛ ጓደኝነትን እንዴት ትገልፀዎለህ? ተብሎ ሲጠየቅ

"እውነተኛ ጓደኝነት ማለት በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ አካላት ውስጥ የሚገኙ ነፍሶች ውህደት ነው።"

'አስመሳይ ጓደኛንስ እንዴት ትገልፀዎለህ??' ተብሎ ሲጠየቅ

"አስመሳይ ጓደኛ በፀሀይ ወቅት ጥላውን ይሰጥሃል፣ዝናብ በመጣ ጊዜ ግን የሰጠህን ጥላ ይነጥቅሃል።"በማለት ነበር በአጭሩ የገለፀው።

በህይወታችን ፀሃያማ ዘመናት ውስጥ የነበሩ፣ በዝናቡም የህይዎት ጉዟችን ውስጥ ጥላቸውን ሳይነፍጉን የቀጠሉት ምን ያህሎች ይሆኑ????

9.6k 0 88 7 156

✔️ በአንድ ወቅት ትኖር የነበረች በህይወቷ ሙሉ አንድም በጎ ነገር ያልሰራች፣ በክፉ ስራዎ ብቻ የምትታወቅ ሴት ነበረች።ታዲያ ይህች ክፉ ሴት ስትሞት፣ነፋሷ ወደ አሳት ባህር ትወረወራለች።

✔️ ይህቺን ሴት ይጠብቅ የነበረ መላዓክ፣በህይወት በነበረችበት ወቅት የሰራችው በጎ ስራ ካለ በሚል ለማስታወስ ሲሞክር፣ በአንድ ወቅት ይለምን ለነበረ ሰዉ የሰጠችዉ ፣አንድ ራስ ሽንኩርት እንደነበረ ያስታዉሳል።

መልዓኩ'ም ወደ እግዜር በመቅረብ "በአንድ ወቅት ይለምን ለነበረ ሰዉ ሽንኩርት ሰጥታ ነበር...ይህ ሊያድናት አይችልምን...."ሲል ይጠይቃል።

እግዜር'ም ..."ሽንኩርቱን በመያዝ ልታወጣት ትችላለህ!!"ሲል ፈቃዱን ይሰጠዋል።

መለዓኩ'ም፣ ወደ አሳት ባህሩ ዝቅ በማለት ሽንኩረቱን ይሰጣታል።እሷም ሽንኩርቱን በመያዝ ቀስ በቀስ ከእሳቱ እየወጣች ሳለ፤የእሷን መዉጣት የተመለከቱ ሌሎች በእሳት ባህሩ ዉሰጥ የነበሩ ሃጢያተኞች፣አግሯን በመያዝ ፣ከእሷ ጋር አብረዉ ለመዉጣት ይሞክራሉ።

ሴትየዋም በቁጣ እየጮኸች..."ይህ የእኔ ሽንኩርት ነዉ!!!!የእኔ ብቻ ነዉ!!!" በማለት አሷ ላይ ተንጠላጥለው ለመወጣት የሚሞክሩትን፣ እየመታች እግሯን ለማስለቀቅ ትሞክራለች።

በዚህን ጊዜ ሽንኩርቱ ከእጇ ያመልጣትና እሳት ባህሩ ዉስጥ ይወድቃል፤እሷም ተመልሳ ወደ እሳት ባህሩ ወደቀች....

በምህረት ለመዳን የነበራትን ብቸኛ እድል፣በእራስ ወዳድነቷ ምክንያት አጣችዉ!!!!!

Brother Karamazov ከሚለዉ የዶስቶቭስኪ መፀሃፍ የተወሰደ

selfishness and lack of compassion can destroy even that chance


✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

9.3k 0 41 2 206

✔️ፈገግታህ አለምን ይቀይር እንጂ ፤አለም ፈገግታህን እንዲወስድብህ አትፍቀድ።ደስታ ሁሉንም ነገር ማግኘት ሳይሆን ባለህ ነገርሮች መደሰት ነዉ።

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

9.2k 0 45 1 143

ዉሃ ያለ አሳ ዉሃነቱን አያሳጣዉም፤ አሳ ግን ያለ ዉሃ ምንም ነዉ፣አፈር ያለ ዛፍ አፈርነቱን አያሳጣዉም፤ዛፍ ያለ አፈር ግን ምንም ነዉ፣እግዚአብሔር ያለ ሰዉ ፈጣሪ መሆኑን አያሳጣዉም፤ ሰዉ ግን ያለ እግዚአብሔር ምንም ነዉ።
አሳ ከዉሀ ከወጣ እንደሚሞተዉ፣ዛፍንም ከአፈር ከለየኸዉ እንደሚሞተዉ ሁሉ፣ሰዉም በተመሳሳይ ከአምላክ ጋር ያለዉ ግንኙነት ከተቋረጠ ይሞታል።ህይወት የሚቀጥለዉ ከአምላክ ጋር ያለን ግንኙነት እስከጠበቀ ድረስ ብቻ ነዉ።

ፈጣሪን የምናመሰግንበትን አንደበት ሰዉን ለማማት፣ሰዉን ለመስደብ አንጠቀምበት!!!!!

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

10k 0 101 12 344
Показано 20 последних публикаций.