ሌላ ሴት ልታገባ ያልክ ቀን እንኳ ብደውልልህ እሷን ትተህ እኔ ጋር ነው አይደል የምትመጣው...? እለዋለሁ ሁሌ ….
ፈገግ ብሎ ያየኝና “ደፋር ኮ ነሽ….ይለኛል።
ካለው ነገር ሁሉ እኔን አስበልጦ እንደሚወደኝ ጠንቅቄ አውቃለሁ...
ሲሳሳልኝ...ከራሱ ሲያስቀድመኝ...ሲጨነቅልኝ...ለኔ ሲኖር ዓይቻለሁ።
....በእርግጥ እንዲ ማለት ከባድ ይመስላል።
እኔ ግን ዓይኑን ሳያርገበግብ...ይሄን ልጅ ግን ምን አስነክታው ነው እስኪባል... የሚያውቁን ሁሉ እስኪገረሙ ድረስ ሳናድደዉ... እና ሳበሳጨው ችሎ በክፉ ቀናቶቼ ላይ ለደስታዬ ሲፈጋ አብሮነታችንን ለማቆም ብዙ ሲለፋ አውቅ ነበር....
ይመስለኛል የበዛ መውደዱ.... የትም አይሄድም ብዬ እንዳስብ... ለኛ እንዳልጨነቅ እና በተወዳጅነት ተኮፍሼ ለሚሰጠኝ መውደድ እና ክብር ትንሽ እንኳ አፀፌታን መስጠት የማልችል ሴት አድርጎኛል...
ከዛ በአንዱ ቀን በትንሽ ነገር ተጋጨን እና ….ሂድልኝ አልኩት...
ለመነኝ አስለመነኝ…ከቀልቤ መሆን ያልቻልኩት እኔ ግን ግድ አልሰጠኝም እና ምንም እንደጎደለብኝ አልተሰማኝም።
መሄዱ እንደሚያም እንዴት እንደሚናፍቀኝ ለመረዳት ብዙ ረፈደብኝ...
ሄደ...
ከዛ አልተመለሰም...
ልመልሰዉ ሞከርኩ…መሄድ አለማምጄው ኖሮ መመለስ አቃተኝ...
እናማ አሁን የገፋሁት እኔ....ወዶኛል አይጠላኝም ያልኩት እኔ በተራዬ እጅግ እየናፈቀኝ...እያመመኝ...ነው።
እያስመሰልኩ አብሮነታችን ማክበር ያልቻልኩት እኔ … ሲያቅፈኝ ሕይወት እንደሚቀለኝ ችግሮቼን ችሎ ማሸነፍ ብቻን ያለማመደኝ እሱ እንደነበር...በጣም እንደሚናፍቀኝ...በጣም እንደማመሰግነው ያልነገርኩት እኔ...
....የሄደበትን ቀን ሻማ እያበራሁ አስታውሰዋለሁ።
(ወግ ብቻ)
(በማ ሂ )
✈️@Enmare1988