፻፵ (140) የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞችና ትርጉማቸው
1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት
ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው።
73 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
74 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው።
75 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
76 ጽዮን፦አምባ ማለት ነው።
77 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
78 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
79 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
80 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
81 ኄራኒ፦ሰላም እና ፍቅር ማለት ነው።
82 ሐና፦ጸጋ ወይም ስጦታ ማለት ነው።
83 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
84 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
85 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
86 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
87 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
88 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
89 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
90 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
91 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
92 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ ማለት ነው።
93 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል ማለት ነው።
94 ዮርዳኖስ፦ወራጅ ውሃ ማለት ነው።
95 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
96 ገነት፦የአትክልት ስፍራ ማለት ነው።
97 ሰሎሜ፦ሰላም ማለት ነው። ነው።
98 ዲና፦ፈረደ ማለት ነው።
99 ማኑሄ፦እረፍት ማለት ነው።
100 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
101 ራማ፦ከፍታ ማለት ነው።
102 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
103 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ ማለት ነው።
104 ሕርያቆስ፦ኅሩይ ምርጥ ማለት ነው።
105 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ ማለት ነው።
106 ቶማስ፦ፀሐይ ማለት ነው።
107 ታዴዎስ፦እሸቱ ማለት ነው።(ግብራዊ ትርጓሜ)
108 ማትያስ፦ፀሐይ ወይም ምትክ ማለት ነው።
109 ቀሌምንጦስ፦ግንብ ማለት ነው።
110 አቤል፦በግ ወይም ደመና ማለት ነው።
111 ኖኅ፦ደስታ ማለት ነው።
112 ሴም፦ተሾመ ማለት ነው።
113 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም ይሳቅ ማለት ነው።
114 ሙሴ፦የውሃ ልጅ ማለት ነው
115 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ ማለት ነው።
116 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።
117 እሴይ፦ዋጋየ ማለት ነው።
118 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ ማለት ነው።
119 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ ማለት ነው፣
120 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ ማለት ነው።
121 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ ማለት ነው።
122 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው ማለት ነው፣
123 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
124 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ ማለት ነው።
125 ራኄል፦በግዕት ማለት ነው።
126 ዕዝራ፦ረዳቴ ማለት ነው።
127 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች ማለት ነው።
128 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ ማለት ነው።
129 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ ማለት ነው።
130 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ ማለት ነው።
131 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት ማለት ነው።
132 ሶምሶን፦ፀሐይ ማለት ነው።
133 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
134 ማርታ፦እመቤት ማለት ነው።
135 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር ማለት ነው።
136 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው ማለት ነው።
137 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች ማለት ነው።
138 ታዴዎስ፦ተወዳጅ ወይም ፍቁር ማለት ነው።
139 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር ማለት ነው።
140 ሄኖስ፦ሰው ማለት ነው።
@Nigatu5@Nigatu5@Nigatu5