MADO NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Your go-to source for the latest, most reliable news from Ethiopia and beyond! Get real-time updates, breaking stories, and insightful coverage from trusted sources. Stay ahead, stay informed, and never miss a beat! 📲
🔻ሼር በማድረግ እና ለወዳጆ በማጋራት ተባበሩን!

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


'የፕሪቶሪያው ውል ለመፈፀም ግዴታ የተጣለባቸው አካላት ሊያስፈፅሙ አልቻሉም' በሚል ሀሳብ በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ!

በመቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ፤ 'ይኣክል' ወይንም 'ይበቃል' የሚሉ መፈክሮችን የያዙ በርካታ ሺሕ ሰላማዊ ሰልፈኞች ጥያቄያቸውን ለፕሪቶሪያው ውል ተዋዋዮች አንስተዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው "ፅላል ሲቪል ማህበረሰብ ምዕራብ ትግራይ" በሰለፉ ላይ፤ ከ1 ሺሕ 500 እስከ 2 ሺሕ የሚገመት ሕዝብ መሳተፉን ለአሐዱ ገልጿል፡፡

ለአሐዱ ሀሳባቸውን የሰጡት ፅላል አባልና የ'ይአክል' ወይንም 'ይበቃል' ንቅናቄ አስተባባሪ ዳንኤል ነጋሽ፤ የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲከበር የሚጠይቅ ሰልፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ለራሱ ዓላማ ለመጠቀም የሚያስብ አካላቶች እጅ በመውደቁ ከነሱ በማውጣት ለሕዝቡ ጥቅም ላይ እንዲውል አስበው መካሄዱን ተናግረዋል፡፡ አካላት ያሏቸውን ግን ማን እንደሆኑ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

አቶ ዳንኤል በዛሬው ዕለት የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በዋነኝነት ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በአቢ አዲ እና በሌሎች መጠለያ ካምፖች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የሰላማዊ ሰልፈኞች ጥያቄ በዋናነት ለተደራዳሪ ወገኖች መሆናቸውን የሚያነሱት አቶ ዳንኤል፤ ጥያቄው በዋናነት ለፌደራል መንግሥት እና ለህወሓት ድርጅት እንዲሁም ይህንን ለማስፈፀም ለተቋቋመው ግዚያዊ አስተዳዳር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Via Ahadu


የግብጽን ጥቅም ለማስከበር ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉት አሜሪካዊው ሴናተር በ15 ዓመት እስር እንዲቀጡ ተጠየቀ

ጥፋተኛ የተባሉት ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ ከአንድ ሳምንት በኋላ የመጨረሻ ፍርድ ይተላለፍባቸዋል ተብሏል

ሴናተር ቦብ ሜንዴዝ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተገናኘ የግብጽን ጥቅም እንዲያስከብሩ እና በሌሎች ጉዳዮች ከ600 ሺህ ዶላር በላይ ሙስና ወስደዋል በሚል ክስ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3CiGqeq


በአዲስ አበባ ምድር ድሮኖቹ የታጠቁ በመሆናቸው እርምጃ ሊወስዱ ነው

እንደሚታወቀው ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማዋን የፀጥታ ሁኔታና የትራፊክ ፍሰት ለመቆጣጠር ድሮን አሰማራለው ማለቱ የሚታወስ ነው።

ድሮኖቹ ቀድሞ ስምሪት ተሰጥቷቸው ለዋናው መስሪያ ቤት መረጃ የሚያቀብሉ ሲሆን መረጃ ከመስጠት ባሻገር ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ፈጣን እርምጃ እንደሚወስዱም አቶ ጄይላ ተናግረዋል፡፡

ከመደበኛ የካሜራ ድሮኖች የተለዩ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው ለፖሊስ ወንጀል መከላከል፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተሰሩ ናቸውም ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በርካታ ድሮኖች አገር ውስጥ መግባታቸውን እና የሚቆጣጠሯቸው ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ስልጠና አጠናቅቀው በቀጣይ ጥቂት ቀናት ወደ ስራ እንደሚገቡ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡


በውጭ ምንዛሬ ለውጡ ሳቢያ የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እየተዘጉ ናቸው

via የአሜሪካ ድምፅ
በውጭ ምንዛሬ ለውጡ ሳቢያ የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እየተዘጉ ናቸው
የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ፣ የሳተላይት ስርጭት ኪራዩ በእጥፍ በመጨመሩ ለመክፈል መቸገራቸውንና ስርጭታቸውን አቋርጠው ለመውረድ መገደዳቸውን፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የቴሌቭዥን ሓላፊዎች ተናግረዋል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ባገኘው መረጃም መሠረት፣ በሳተላይት ስርጭታቸውን ከሚያስተላልፉ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መካከል እስከ አሁን 13 የሚኾኑቱ ከሳተላይት ወርደዋል፡፡ በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት...


ለ340 የፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤት ተላለፈ

2ኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ለመተግበር የፖሊሶችን ካምፕ ስንጎበኝ የሰራዊቱ አባላት ካምፕ ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው እና ከልጆቻቸው ጋር እጅግ በማይመች ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ መሆኑን በመረዳት ለነዋሪዎች እንዳደረግነዉ ሁሉ 340 ቤተሰብ ላላቸው የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤቶችን አስተላልፈናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ፖሊስ ቅድሚያ ለህዝብ እና ለሀገር ደህንነት ዋጋ እየከፈሉ የሚገለግል እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም ለሰራዊቱ ምቹ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖረዉ ከተቋሞቻቸዉ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምንሰራ ይሆናል ሲሉ አክለዋል።


በሚቀጥሉት ቀናቶች አንጻራዊ የደመና ሽፋን መጨመር ይኖራል‼️

በሚቀጥሉት ቀናቶች በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አንጻራዊ የእርጥበት መጠንና የደመና ሽፋን መጨመር እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የመካለኛው፣ በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅ፤ በሰሜን ምዕራብ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አንጻራዊ የእርጥበት መጠንና የደመና ሽፋን መጨመር እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የደቡብ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንሚያገኙም ነው የኢንስቲትዩቱ መረጃ የሚያመላክተው፡፡

በሌላ በኩል አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለው የበጋው ደረቅ፣ ጸሀያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ በሚቀጥሉት ቀናትም ቀጣይነት እንደሚኖረው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ተብሏል፡፡


ዜና: ተባብሶ በቀጠለው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ሳቢያ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ

በአፋር ክልል ከ2,250 በላይ የሚደርሱ ተፈናቃዮች ያለምንም እርዳታ ተቀምጠዋል ተብሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 5/2017 ዓ.ም፡- በአፋር እና በኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት “ሁለት ግለሰቦች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን” የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ (ኦቻ) የመሬት መንቀጥቀጡ በመኖሪያ ቤቶች፣ በጤና ጣቢያዎች፣ በትምህርት ቤቶች እና መንገዶችን ጨምሮ በመሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልጿል።

በመንግሳቱ ድርጅት የተቀናጀ የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪዎች እንዲሁም አጋር ተቋማት ድጋፍ በተዘጋጀው በዚህ ወቅታዊ ሪፖርት ላይ ሁሉን አቀፍ ሰብአዊ ምላሽ እየተካሄደ ቢሆንም ጉልህ ክፍተቶች መኖራቸው ተመላክቷል።

ሪፖርቱ በአፋር ክልል አዋሽ እና በኦሮሚያ ክልል መተሀራ አከባቢ በመንግስት ይመራሉ ያላቸው የዞን አደጋ ምላሽ አስተባባሪ ማዕከላት ተቋቁመው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት  እና የክላስተር ሰራተኞችን በማካተት ቅንጅታዊ አሰራር መፈጠሩን ጠቁሟል።

ባሳለፍነው ሳምንት 4 ሺ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞችን ጨምሮ ከ58 ሺ በላይ ግለሰቦች በገቢራሱ ዞን ዱለሳ እና አዋሽ ፈንታሌ ወረዳዎች በተደጋጋሚ እየተስተዋለ በሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ  ሰብዓዊ እርዳታ እያገኙ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ኦቻ በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሠረት የአደጋ አስተዳደር ኮሚሽን ወደ እነዚህ መጠለያ ጣቢያዎች 16 ምግብ የጫኑ መኪናዎችን መላኩን አመልክቷል፤ በተጨማሪም ከዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም እና ከወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ድጋፍ ይጠበቃል ብሏል።

እንዲሁም በአፋር ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ለ6 ሺ 780 ቤተሰቦች የምግብ እርዳታ መድረሱን ገልጾ ይሁን እንጂ 2 ሺ 250 ቤተሰቦች ምንም አይነት ድጋፍ ሳያገኙ ቀርተዋል።” ብሏል።

አዲስ ስታንዳርድ በቅርቡ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ሳቢያ ከ30 በላይ ቤቶች መውደማቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን መዘገቡ ይታወሳል። አስ

The post ዜና: ተባብሶ በቀጠለው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ሳቢያ ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ appeared first on Addis standard.

via Addis standard (author: Million)


ከባለስልጣኑ ፈቃድ በመውሰድ በተቋም ደረጃ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጀር መትከል የሚፈቅድ መመሪያ ጸደቀ!

ተቋማት ለሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሃይል ማቅረብ ከፈለጉ ከነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ፈቃድ በመውሰድ ማሽኑን መትከል የሚያስችላቸው መመሪያ መጽደቁ ተጠቆመ።የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሃይል ሙሌት ስርዕትን የተመለከተ ባጸደቀው መመሪያ መሰረት ለራስ አገልግሎት በተለያዩ ተቋማት የሚተከሉ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሃይል መሙያዎች ከባለስልጣኑ ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።

በግል በቤት ውስጥ ከሚተከሉ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሃይል መሙሊያ ማሽኖች ፈቃድ መጠየቅ የማይጠበቅባቸው መሆኑን ያመላከተው የተቋሙ መረጃ ከዚህ ውጭ ግን ማናቸውም የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ሃይል ሙሌት የሚሰጡ ማሽኖች መትከል የሚቻለው ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ መሆኑን አመላክቷል።መመሪያው ለህዝብ በሽያጭ የኤሌክትሪክ ሃይል ሙሊት አገልግሎት የሚሰጡ ታሪፋቸው በባለስልጣኑ ሲጸድቅላቸው ብቻ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያስገድዳል።

“ከኤሌክትሪክ ታሪፍ ጋር በተገናኘ ከባለስልጣን መ/ቤቱ የሃይል አቅርቦትና ሽያጭ ፈቃድ የወሰዱ ተቋማት ለበለስልጣኑ የታሪፍ ፕሮፖዛላቸውን አቅርበው ሲያፀድቅ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነ መመሪያው ያሳያል፡፡ለማሽኖቹ መትከያ ቦታዎችን በተመለከተ መመሪያው በየ50 ኪሎ ሜትር በየመንገዶቹ ግራና ቀኝ በኩል እንዲቋቋም መመሪያ የሚፈቅድ ሲሆን በተጨማሪም ለከባድ ተሸከርካሪዎች ማለትም አውቶቢስ እና የጭነት ተሸከርካሪዎች በየ120 ኪሎ ሜትር ቢያንሰ አንድ የሃይል መሙያ እንዲኖር ይፈቅዳል፡፡

Addis Standard


ከውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደር እየተዘጋጁ መሆኑን ባንኮች ገለጹ ‼️

የውጭ ባንኮች በሀገር ውስጥ በዘርፉ እንዲሰማሩ የሚፈቅደው የባንክ ሥራ አዋጅ በቅርቡ መጽደቁ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም ፋና ዲጂታል ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ጋር በዘርፉ ለመወዳደርና አቅማቸውን ለማሳደግ የሀገር ውስጥ ባንኮች ምን እየሰሩ ነው ሲል ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ÷ የውጭ ባንኮች በሀገር ውስጥ እንዲሰማሩ የሚፈቅደው አዋጅ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ከማሳደግ ባለፈ በዘርፉ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ ያስችላል፡፡

ንግድ ባንክ ከውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደርና ተመራጭ ለመሆንም አዳዲስ እና ዘመኑን የዋጁ ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተለይም የአገልግሎት ጥራት፣ የዋጋ ተወዳዳሪነት እና የተሻለ ቴክኖሎጂን እውን ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

የውጭ ባንኮች የተሻለ ካፒታልና አገልግሎት ይዘው እንደሚመጡ ይጠበቃል ያሉት አቶ አቤ÷ ለዚህም ባንኩ የካፒታል አቅሙን ከማሳደግ ጀምሮ ሁለንተናዊ ዝግጅት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከቅርንጫፎች ጋር ተያይዞም በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የባንኩን ቅርንጫፎች የማዋሃድ ሥራ መጀመሩን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የግሎባል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተስፋዬ ቦሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ባንኩ እንደ ሀገር የሚወጡ ሕጎችን ለመተግበር ሁሌም ዝግጁ ሆኖ እንደሚጠብቅ ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ጋር በዘርፉ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል የባንኩ ሒደቶች ላይ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለዚህም ከፍተኛ የዘርፉ ባለሞያዎችን ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎችንና ሀገራዊ ሁኔታዎችን እያጠና ይገኛል ብለዋል።


የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ነገ ያበቃል!

የ2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ በመጪው ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።

በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ካሉ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንዲመዘገቡ ያሳሰበው አገልግሎቱ፤ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ፈተናውን እንደማይፈተኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት አስጠንቅቋል።


በአውሮፓ የጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ቁጥር ቅናሽ አሳየ

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ስደተኞች በአውሮፓ ጥገኝነት ጠይቀዋል ተብሏል። ጀርመን፣ ስፔን እና ፈረንሳይ ዋነኛ ስደታኛ ተቀባይ ሀገራት ሆነዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fTzKl0


የሰው ህይወት አልፏል‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ከፍተኛ ምግብ እጥረት የእናቶች እና የህጻናት ሕይወት ማለፉ በዳሰሳ ጥናት ተረጋገጠ

ካለፈው ወር ጀምሮ በወረዳው ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የዘገቡ ሲሆን፤ ለዕይታ የሚረብሹ ምሥሎችም ይፋ ሆነዋል።
የአካባቢውን የምግብ እጥረት ለማረጋገጥ አጭር ዳሰሳ ያደረገው ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ቀውሱ ከተነገረው በላይ "ከባድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብሏል።

ስድስት ባለሞያዎችን ያካተተ ቡድን በቡግና ወረዳ አራት "ቁልፍ" ቀበሌዎች ላይ ባደረገው ምልከታ ከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ የህክምና አገልግሎት እጦት እና የውሃ ችግር ማኅበረሰቡ መጎዳቱን አመልክቷል።

ቡግና ወረዳ በድርቅ የሚታወቅ አካባቢ ከመሆኑ ባለፈ የሰሜኑ ጦርነት ጠባሳ ያረፈበት እና ባለፈው ዓመት የጎርፍ እና የበረዶ አደጋዎችን በማስተናገዱ ማኅበረሰቡ "ፍሬ" እንዳያገኝ አድርጎታል።

የወረዳውን የምግብ እጥረት እና የጤና ሁኔታን የሚዳስሰው ጥናት ከወሊድ ጋር በተያያዘ ከተመዘገቡ ሞቶች ውጪ አምስት ህፃናት እና ሁለት እናቶች በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ማለፉን ይገልጻል።

ሦስት ህፃናት በቆብ ቀበሌ (ክላስተር) ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ ብርቆ እና ቅዱስ ሀርቤ በተባሉ ቀበሌዎች ደግሞ በምግብ እጥረት የሁለት የህፃናት ሕይወት አልፏል።
በወረዳው ዋና ከተማ አይና ደግሞ ሁለት እናቶች በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ማለፉን ባለሙያው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአይና ከተማ በጎረቤቶቿ ቤት ለቡና በሚቀርብላት 'የቡና ቁርስ' ልጆቿን ትመግብ የነበረች አንዲት እናት "መቸገሯ ሳይታወቅ" ሕይወቷ አልፎ እንደተገኘች ማወቃቸውን ባለሙያው ተናግረዋል።


በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው መያዝና ወደ ማቆያ ማዕከላት ማስገባት ሊቆም ይገባል-ኢሰመኮ

ድርጊቱ የሰዎቹን የነጻነት መብት ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶቻቸውን የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም ጠይቋል

via جديد አል ዐይን ኒውስ


በኦሮሚያ ክልል ለቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠና መሰጠት ጀመረ‼️

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሰላም መንገድን የመረጡ የቀድሞ ታጣቂዎችን የተሃድሶ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

ከምዝገባ ጀምሮ፣ የትጥቅ ርክክብ፣ መልሶ ማቋቋምና ማቀላቀልን ማዕከል ያደረገው ስልጠናው የሚሰጠውም በአዋሽ ቢሾላ የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል ነው።

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከዚህ ቀደም በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች በተመሳሳይ በሺዎች ለሚቆጠሩ ታጥቀው ይንቀሳቀሱ ለነበሩ ታጣቂዎች ተመሳሳይ ስልጠናዎችን መስጠቱ ይታወሳል።


በዱባይ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያን ከአንድ እስከ አስር ወጡ!

በ2025 የዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች ከአንድ እስከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀቁ።
በወንዶች ማራቶን ቡቴ ገመቹ 2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ በመግባት አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ብርሀኑ ፀጋ ሁለተኛ ሽፈራው ታምሩ ሦስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በሴቶች ማራቶን አትሌት በዳቱ ሂርጳ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ በመግባት አንደኛ ሆናለች። ደራ ዲዳ እና ትዕግስት ግርማ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ወጥተዋል።

በወንዶች ማራቶን ከአስር እስከ አስራ አራት ያለውም ደረጃ የተያዘው በኢትዮጵያውያን ነው። በሴቶቹም እንዲሁም እስከ 16 ያለውን ደረጃ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይዘውታል።

በአምናው የዱባይ ማራቶን 2024 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ከአንድ እስከ አራት በሴቶች ደግሞ ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸው አይዘነጋም።


አሜሪካ የቪንዙዌላው ፕሬዝደንት ማዱሮ ያሉበትን ለጠቆማት 25 ሚሊዮን ዶላር እከፍላሁ አለች

ከአሜሪካ በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት እና ብሪታንያም ለፕሬዝዳንት ማዱሮ እውቅና እንደማይሰጡ አስታውቀዋል

via جديد አል ዐይን ኒውስ


በካሊፎርኒያ የተነሳዉ ሰደድ እሳት አሁንም መቆጣጠር አልተቻለም ፡፡

አሜሪካ ያላትን አቅም ለመጠቀም ብትሞክርም እስካሁን እሳቱን መቆጣጠር አልቻለችም ፡፡

አሁን ደግሞ በምስራቃዊ ክፍል እሳቱ በከፍተኛ መጠን እየተዛመተ በመምጣቱ የግዛቱ ነዋሪዎች በፍጥነት ከአካባቢዉ ለቀዉ እንዲወጡ ትእዛዝ ተላልፏል ፡፡


በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራዎች መካከል መሬት ውስጥ ያለው ቅልጥ አለት ወደ ሰሜን ምስራቅ 50 ኪሎ ሜትር አዳርሷል ተባለ

👉🏼እየተከሰተ ያለዉ የመሬት መንቀጥቀጥ በተለይ በአካባቢው ህንጻዎችን ሊያፈርስ ይችላል

በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራዎች መካከል እየተከሰተ የሰነበተው ርዕደ መሬት በተለያዩ ከተሞች እያስከተለው ያለው ንዝረት መጠኑ ቢለያየም አሁንም ቀጥሏል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዝክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) በተለይ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም እንዳሉት፥ በተራራዎቹ መካከል መሬት ውስጥ ያለው ቅልጥ አለት ወደ ሰሜን ምስራቅ 50 ኪሎ ሜትር አዳርሷል።

የርዕደ መሬቱ መነሻ በሁለቱ ተራራዎች መካከል ያለ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ሌዊ፤ የንዝረቱ መጠን ቢለያየም አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ አዋሽ፣ መተሀራ እና ደብረ ብርሃን  ድረስ መሰማቱን ዳጉ ጆርናል ከኢቢሲ ዘገባ ተመልክቷል።

በአዋሻ አርባ፣ በሳቡሬ፣ በመተሀራ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው የንዝረት መጠኑ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል። 

ከፈንታሌ ወደ ዶፈን ባለው አቅጣጫ የውስጥ ለውስጥ ቅልጥ አለቱ ባለፈው መስከረም ሲጀመር እስከ 10 ኪሎ ሜትር ነበር፤ በመሀል ቆም ብሎ ነበር፤ አሁን ግን እስከ 50 ኪሎ ሜትር አዳርሷል ብለዋል ዶ/ር ኤሊያስ።

አዲስ አበባን ጨምሮ እየተከሰተ ያለው የንዝረት መጠን መነሻው በተራራዎቹ አካባቢ መሆኑን አንስተው፤ በተለይም እዛው አካባቢ ቤቶችን እና ህንፃዎችን ሊያፈርስ ይችላል ብለዋል።

ቅልጥ አለቱ መሬት ውስጥ ሊቀር ይችላል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በተቃራኒው እሳተ ገሞራ በማንኛውም ሰዓት ወደ ገፀ መሬት ሊወጣ የሚችልበት ዕድልም ስላለ፣ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ኢቢሲ


ሞያሌ‼️

ትናንት ምሽት በሞያሌ የ12 አመት ህጻን መገደሉን ተከትሎ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። ዛሬ ጠዋት ተቃዋሚዎች ወደ ጎዳና የወጡ ሲሆን ተኩስ ተከፍቶ ሁለት ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል።


የሶማሊያዉ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ አዲስአበባ ገቡ።

Показано 20 последних публикаций.