"ይህ የመጨረሻው የሚያነባ የአማራ ትውልድ ይሆናል"
ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ!
ባለፉት 500 ዓመታት ለነጋሪም፣ ለሰሚም ለፀሐፊም ያስቸገሩ ለታሪክ ገፆች የከበዱ ፍጅቶች በአማራ ህዝብ ላይ ተፈፅመዋል። በተለይ ባለፉት ሰማንያ ዓመታት ውስጥ ጠላቶቻችን አማራ አልቦ ምድር ሊፈጥሩ ጥረዋል። የጠላቶቻችን የጦር መኳንንት አማራ የሌለባት ኢትዮጵያን ለአለቆቻቸው ሊያስረክቡ ቃል ገብተው ሊፈፀሙት ተንቀሳቅሰዋል። በመሆኑም ሚሊዮን አማራዎች በዚህ እቅድ የተነሳ አልቀዋል። ይህንን ግፍ ለማስቆም ቀደምቶቻችን በተለያየ ጊዜ የተሳካም ያልተሳካም የጀግንነትና የአርበኝነት ስራ ሰርተዋል። በነዚህ ሰማንያ ዓመታት ውስጥ አንድ የአማራ ጭንቅላት ተቆርጦ ሰላሳ ብር ተሽጧል። የአማራን አንገትበላይ በብዛት ያመጣ ባንዳ ለስኬቱ ተሸልሟል። አካላችንም መሬታችንም እየተቆራረጠ ተጥሏል፤ ተሸጧልም። በዚህ ሁሉ ረጅም ዘመን ውስጥ አማራ ፈጅ ጥፋቶችና ክፋቶች ምንጫቸው አንድ በመሆኑ የዚሁ ተቀጥላና ዲቃላ ሕዝብ አውዳሚ መንፈስ የወለደው የአብይ አህመድ የጥፋት ዘመን ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ሰባተኛ ዓመቱን አስቆጥሯል::
አማራም ከአምስት መቶ ዓመት የውድቀትና የውርደት ዘመን በኋላ በዚህኛው ትውልድ ጊዜ ነቅቶ ተደራጅቶ ታጥቆና የመከራ መሻገሪያ ርዕዮቱን ሰንቆ የተነሳ ሲሆን ከሰባት መቶ ዓመታት በላይ የከበዱ ሰባት ዓመታት እያሳለፈ ይገኛል። አብይ አህመድ የአማራ ህዝብ አንድ አንገት ኖሮት በአንድ ጊዜ በአንድ ቅፅበት በአንዳች ሰይፍ ቆርጦ ጥሎት ቢገላገል ደስታውን መሸከም የማይችል የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያዊ ካሊጉላ ነው። በአማራ ህዝብ የሺህ ዓመታት ታሪክ ጉዞ በተለያየ ጊዜ ብቅ እያለ ሲያደማንና ሲያወድመን የኖረ መንፈስ አሁንም በአብይ አህመድ ዘመን አብይን ፈጥሮ በአብይ አህመድ በኩል እየወጋንና እየጨፈጨፈን ይገኛል።
ጉዳዩ ተራ ፖለቲካዊ ግብግብ አይደለም። የአማራ ህዝብ እየተከላከለ ያለው ጦርነት ጥልቅ የማንነት የታሪክና የእሴት ጦርነት ነው። ከፖለቲካ ትግል አለፍ ያለ ውስብስብ ጦርነት ነው። ጠላቶቻችን አማራ አልባ ኢትዮጵያን ሊፈጥሩ ለራሳቸው ቃል እንደገቡት ሁሉ ተመሳሳይና አንድ መንፈስ የወለደው አብይ አህመድና ዘመኑ አማራ የሌለባት ኢትዮጵያን ሊፈጥሩ አየተጉ ይገኛሉ። ይህ የጥፋት ፕሮጀክት ነው ዛሬ መጋቢት 24/2017 ዓ/ም ሰባት ዓመት የሞላው!
ሰባት የውድመትና የመንቃት፣ የደምና የድል፣ የመውደቅና የመነሳት፣ የእልቂትና ጠላትን በኩራትና በጀግንነት የመጋፈጥ ተጋፍጦም የማሸነፍ አስገራሚ አመታት!
ሰባት በደምና በድል የተነከርንባቸው፣ በእንባና ሳቅ የታጠብንባቸው፣ ከሞት ውቅያኖስ ተስፋ፣ ከእልቂት ባህር ድል የቀዳንባቸው ግራጫ አመታት!
አሁን የአማራ ልጆች ተነስተናል ነቅተናል ተደራጅተናል ታጥቀናል ድልን ለምደናል። ህልውናችንን የምናረጋግጥበት ዘመን እሩቅ እንደማይሆን ከተረዳንም ውለን አድረናል። እንደ ህዝብ ለእልቂት ሳይሆን ለድል መፈጠራችንን አምነናል። ውስጣዊ አማራዊ አንድነታችን በመዋቅር ደረጃ ማረጋገጥ ብቻ ይቀረናል። ይህም በቅርቡ እውን ይሆናል። ከዛማ ማን ከፊታችን ይቆማል? ማንም። ተራሮች እንኳን ቀና ብለው አያዩንም። ውሃው ይጎድልልናል፤ ነፋስም ይታዘዘናል።
ይህ የመጨረሻው የሚያነባ ትውልድ ይሆናል።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት !
ድላችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ በሸዋ
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
የአማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ-አማራ)
የአማራ ፋኖ በጎጃም
ዘመቻ አንድነት ግለቱን ጠብቆ ይቀጥላል
መጋቢት 24/2017 ዓ/ም
@showapress