በሰሜን ሸዋ የቀጠለዉ እገታና አንድምታዉ ዝምታዉ ለምን?
(ታዬ ደንደአ )
➖➖➖
ሰሜን ሸዋ ኦሮሚያ ክልል... እጅግ አደገኛ የእገታ ወንጀል ለዓመታት ቀጥሏል። የዞኑ ነዋሪዎች በየተራ ከከተማና ከገጠር ይታገታሉ። እገታዉ በተመሳሳይ በመንገደኞች ላይም ሲፈፀም ዛሬ ደርሷል። ለታጋቾች ማስለቀቂያ በሚሊየኖችና በመቶ ሺዎች ይጠየቃል። የቻለ ጥሪቱን ሽጦ ወይም ዘመድ አዝማድ አስቸግሮ በመክፈል ይለቀቃል። ከፍያዉ ደግሞ ከካሽ ባሻገር በባንኮች ጭምር እንደሚፈፀም ኢሰመኮም አረጋግጧል። መክፈል ያልቸለዉ እንደሚገደልም ታዉቋል። በዚህ ምክንያት ብዙዎች ጥሪታቸዉን በመነጠቅ ለከባድ ችጋር ተጋልጧል። በርካቶችም ህይወታቸዉን አጥቷል።
ትላንትም በሰሜን ሸዋ ወረ-ጃርሶ ወረዳ የተለመደዉ አሳዛኝ የእገታ ወንጀል መፈፀሙን ሰምተናል። አንድ የመንገደኞች አዉቶቢስ ላይ ተኩስ ተከፍቶ በርካቶች ሲቆስሉ ከአስር በላይ ንፁኃን ዜጎች መገደላቸዉ ተዘግቧል። ታፍነዉ የተወሰዱ ስለመኖራቸዉም ይነገራል። ዜጎች በዚህ ሁኔታ መንገድ ላይ መቅረታቸዉ እጅግ ያሳዝናል። የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት አካል ግን የፓርክና የሪዞርት ግንባታ ላይ አተኩሯል።
ከሁለት ቀን በፊት አንድ የፖሊስ ኢንስፔክተር ሁለት መቶ ብር ጉቦ መቀበሉ ትልቅ ዜና ነበር። ኢቲቪና ፋናም "ሌብነት ላይ ለተጀመረዉ ትግል አበረታች እርምጃ" ብለዉታል። ከሳምንት በፊትም "ሀሰተኛ መረጃን ለማጋለጥ" ጥረዋል። ጉዳዩ የማይመለከታቸዉ ባለስልጣናት ጭምር በየተራ ወጥተዉ የብርቱካን ድራማ "ኢትዮጵያን ለመግደል የተሸረበ ሴራ ነዉ" ብለዉናል። የበርካታ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈዉና አካል ያጎደለዉ የትላንቱ ወንጀል ግን ዝም ተብሏል። የሁለት መቶ ብር ጉቦ ያንበገባቸዉ ኢቲቪና ፋና በሚሊዬኖች እየዘረፈ ብዙ ዜጎችን ለመከራ ያጋለጠዉ ተደጋጋሚ የእገታ ወንጀል ምንም ያልመሰላቸዉ ለምን ይሆን? የኢትዮጵያ ህዝብ በሀሰተኛ መረጃ እንዳይጎዳ በዚያ ልክ የተረባረቡት ሚዲያዎችና ባለስልጣናት ንፁኃን ዜጎች በየግዜዉ በመታገት ሲገደሉና አካላቸዉን ሲያጡ ለምን አያማቸዉም? በድራማዉ የታሰበለት የኢትዮጵያ ህዝብ የትላንቱን ተጎጂዎች አያጠቃልልም እንዴ?
ተጨማሪ ጥያቄዎችም አሉ። መጠኑ ቢለያይም በኦሮሚያ የነዋሪዎች እገታ በየቦታዉ ተለምዷል። በሰላም ወጥቶ መግባት በአብዛኛዉ ቅንጦት ሆኗል። ሰላም ሳይረጋገጥ ስለብልፅግና መስበክም ቀልድ ይሆናል። ይሁንና በዚህ ሁሉም ይመሳሰላል። በመንገደኞች እገታ ላይ ግን ግልፅ ልዩነት ይታያል። ከመንገዶች ሁሉ የጎጃም መስመር በዋናነት ተደጋጋሚ ጥቃቶችን አስተናግዷል። የዚህ መስመር ላይ ብዙዎች ተዘርፈዉ ለመከራ ሲጋለጡ በርካቶች ህይወታቸዉንና አካላቸዉን አጥተዋል። ሚስጢሩ ምንድ ነዉ? አጋቹስ በትክክል ማን ይሆን? ተመሳሳይ ወንጀል በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ቦታ ላይ ለምን ይፈፀማል? ኃላፊነት ያለበት አካልስ ለምን ዝም ይላል? ይህ አደገኛ ወንጀል በመንግስት ሚዲያ የማይዘገበዉስ ለምንድነው? በርግጥ የእገታዉ ዓላማ ገንዘብ ማግኘት ብቻ ነዉ ወይስ የፖለቲካ ቁማር አለበት? ምናልባት የፖለቲካ ቁማር ኖሮበት ዓላማዉ ኦሮሞንና አማራን ለማጣላት ከሆነ ውጤቱ ማንን ይጠቅማል? ኢቲቪና ፋና ልክ እንደብርቱካን "ድራማ" ተረባርበዉ ቢያጋልጡትስ?
ለሟች ወገኖቻችን እጅግ አዝኛለሁ! የቆሰሉትም ፈጥነዉ ይድኑ ዘንድ እመኛለሁ! ዋናዉ ጉዳይ ግን የፖለቲካ ቀዉሱንና እንቆቅልሹን መፍታት መሆኑን ልብ እንበል እላለሁ!
@showapress