ታምሪን ሚዲያ(Tamrin Media)✍✍✍✍✍


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Introducing daily news and information all over the world including our country ethiopia
ለፈጣን እና ተዓማኒ መረጃዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ቻናላችንን በመቀለቀል ወቅታዊ መረጃዎቸችን በፍጥነት ያግኙ👇👇👇
https://t.me/Tamrinmedia
✉️inbox 👉 @tamrin_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ተስፋ የተጣለበት ኤር ድሮፕ ነው ፈጥናችሁ ጀምሩት::
ከሜጀር ቀጥሎ በቴሌግራም መስራች እና ባለቤት የሚደገፍ ፕሮጀክት ነው !!
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=GP6ps2Zp
LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾










Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው በስመአብ ብለህ እረ*ደው የሚለው አሰቃቂ ቪዲዮ እንደ ሀገር ከጊዜ ወደ ጊዜ ጨካኝ እንደሆንን ያሳየ ነው።
ሰው የሆነ ሰው እንዴት የራሱን አምሳያ  በስምአብ/ቢስሚላሂ/ብሎ በቢለዋ ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ እንደበግ ያርዳል?😭😭😭
https://t.me/Tamrinmedia




ነገሩ ተካሯል!
ሁሉንም አስፈርቷል። ዩክሬን ትናንት በአሜሪካ ትዕዛዝ ወደ ራሽያ 6 ረጅም ርቀት ሚሳኤል ተኩሳ ነበር። 5ቱ ከሽፎ አንዱ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ፑቲን አስፈሪውን የዘመነ የኑክሌር ሰነድ በፊርማቸው አፅድቀዋል።

ሩሲያ ለራሷ እና ለቤላሩስ ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት አደገኛ ከሆነ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም ትችላለች ተብሏል። ይህ የሚወሰነው በሩሲያ ፕሬዚዳንት ፑቲን ነው::
https://t.me/Tamrinmedia




ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የምርጫ ውጤቱን እንደሚቀበሉ ኣስታወቁ፡፡

ባለፈው ሳምንት በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መደረጉ ይታወሳል።

በከፍተኛ ብልጫም የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) ምርጫውን አሸንፈዋል።

በምርጫው የተሸነፉት ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ "የምርጫውን ውጤት እንቀበላለን" ብለዋል።

ለተመራጩ ፕሬዜዳንትንም "እንኳን ደስ አልዎት!" ብለዋቸዋል።

“ሰላማዊና የተረጋጋ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ለማድረግ የተሟላ ድጋፌን አደጋለሁ " ሲሉም ቃል ገብተዋል።

6ኛው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አብዲራህማን ኢሮ በበኩላቸው÷ "ማንም ተሸናፊ ማንም አሸናፊ የለም ያሸነፈው የሶማሌላንድ ህዝብ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሌላንድ እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ምትቆጥር ናት፤ እጅግ ሰለማዊ፣ የተረጋጋ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግም ትወደሳለች።
https://t.me/Tamrinmedia


በሊባኖስ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ እስራኤል እና ሂዝቦላን ለማሸማገል ቤሩት ገቡ
በሊባኖስ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አሞስ ሆችስቴይን እስራኤል እና ሂዝቦላ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ለማሸማገል ቤሩት ገብተዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው በቤሩት ቆይታቸው የሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ባለስልጣናት እንደሚኒጋግሩ ይጠበቃል፡፡

የሊባኖስ መንግስት እና በኢራን የሚደገፈው ሂዝቦላ በዋሽንግተን የቀረበውን የተኩስ አቁም ስምምነት የጽሁፍ ምክረ ሃሳብ መቀበላቸውም ተሰምቷል፡፡

በአስራኤል በኩል በተኩስ አቁም ስምምነቱ ዙሪያ የተባለ ነገር አለመኖሩን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

የአሞስ ሆችስቴይን የቤሩት ቆይታም በአሜሪካ የሚመራው የዲፕሎማሲ ጥረት የሁለቱን ወገኖች ደም አፍሳሽ ግጭት መቋጫ እንደሚያበጅለት ይጠበቃል ተብሏል፡፡
Via#ኤፍ ቢሲ
https://t.me/Tamrinmedia


ኢትዮ ቴሌኮም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈ-ብዙ የመሠረተልማት ማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይህንን ስትራቴጂ እውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ አንዱ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሲሆን፣ ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ቁልፍ ሚና ያለው መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ በመደረግ ላይ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥረት በመደገፍ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የመመዝገቢያ መሳሪያዎችን በመግዛት፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት ማዕከላቱን በመጠቀም እና የሰው ኃይል በማሰልጠን የምዝገባ ስራ በስፋት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

አገልግሎት ደህንነቱ አስተማማኝ፣ ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው ካርድ በቀላሉ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ደንበኞች በቴሌብር ሱፐርአፕ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ የካርድ ህትመት መተግበሪያ ወይም በድረገጽ https://teleprint.fayda.et/ በመግባት፣ የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (FAN) በማስገባት፣ በአጭር ጽሑፍ የሚላከውን የማረጋገጫ መለያ ኮድ በማስገባት፣ የአገልግሎት ፍጥነት፣ ካርድ የመረከቢያ ቀን እና ቦታ እንደፍላጎታቸው መምረጥ ይችላሉ፡፡
የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ ደንበኞች በተለያየ የህትመት ማድረሻ ፍጥነት አማራጮች (delivery time) ማለትም ለመደበኛ በ7 የሥራ ቀናት (345 ብር)፣ ለፕሪሚየም በ6 የስራ ቀናት (600 ብር) እና ለኤክስፕረስ አስቸኳይ (800 ብር) በቀላሉ በቴሌብር በመፈጸም አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ ይሆናል፡፡

የመታወቂያ ህትመቱ አገልግሎቱ ዘመናችን በደረሰበት የመጨረሻ የህትመት ቴክኖሎጂ በላቀ የህትመት ጥራት ደረጃ የሚከናወን ሲሆን፣ በቀላሉ የማይጫጫር፣ ቀለሙ የማይለቅ እና ሳይበላሽ እስከ 10 አመታት የሚደርስ የአገልግሎት እድሜ ያለው ነው፡፡
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶችን ለዜጎች ለማቅረብ፣ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ተሞክሮን እውን ለማድረግ፣ የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት፣ የኢ-ኮሜርስን ግብይት ለማሳለጥ፣ የፋይናንስ አካታችነትን የሚጨምሩ የአነስተኛ ብድር አገልግሎቶችን ያለዋስትና ለማቅረብ፣ የክሬዲት ግብይት ለማስፋፋት፣ የብድር ምጣኔ (credit score) ለማሻሻል እንዲሁም የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ እና ቢዝነስን የሚያቀላጥፉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡
https://t.me/Tamrinmedia


ሰበር — ሶማሊላንድ ‼️

አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

የሶማሊላንድ ምርጫ ኮሚሽን የዋዳኒ ፓርቲ እጩ አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።

አብዲራህማን በምርጫው 63 ነጥብ 92 በመቶ ድምጽ በማግኘት ያሸነፉት ሲሆን፥ የወቅቱ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ 34 ነጥብ 81 በመቶ ድምጽ በማግኘት ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

በምርጫው ሂደት ውስጥ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ዋዳኒ፣ ኩልሚዬ እና ካህ ቁልፍ ተዋናዮች ሆነው መታየታቸው ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በሶማሊላንድ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን በመግለጽ ህዝቡ ላሳየው ተሳትፎ አመስግኗል።

አዲስ የተመረጡት ፕሬዚዳንት በሚቀጥሉት ቀናት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ያሳውቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሙስታክባል ሚዲያ ነው የዘገበው፡፡

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባለፈው ሳምንት ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም መካሄዱ ይታወቃል።
https://t.me/Tamrinmedia


ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህጋዊነት ውጪ ያሉ ስደተኞችን ለማባረር አስቸኳይ አዋጅ በማወጅ የሚሊቴሪ ሃይሉን እንደሚጠቀሙ ዛሬ አረጋግጠዋል::
https://t.me/Tamrinmedia


የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በሱዳን ጉዳይ ላይ ይወያያል ተብሏል።

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በሱዳን ባስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም እንዲደረግ በረቀረበለት ሰነድ ላይ ዛሬ ይወያያል።

ብሪታኒያና ሴራሊዮን በጋራ ያቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ፤ ተፋላሚ ወገኖች ባስቸኳይ ግጭት እንዲያቆሙ፣ ንግግር እንዲጀምሩና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የሚጠይቅ ነው።

የውሳኔ ሃሳቡ፤ ሁለቱም ወገኖች ንጹሃንን ከጥቃት ለመጠበቅ ቀደም ሲል የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች እንዲያከብሩ፣ ጾታዊ ጥቃትን እንዲከላከሉ፣ ያልተቋረጠ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲገባ እንዲያደርጉ ጭምር ይጠይቃል።

አባል አገራት ግጭቱን ከሚያባብስ ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠቡ፣ በዳርፉር ላይ የተጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲያከብሩ እንዲሁም ተፋላሚዎቹ ተኩስ አቁም ላይ የሚደርሱ ከሆነ የተመድ ዋና ጸሃፊ የስምምነቱን ተፈጻሚነት የሚቆጣጠር አካል እንዲሰይሙም ጥሪ ያደርጋል
https://t.me/Tamrinmedia


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የተከሰከሰ ሄሊኮፍተር የለም መግለጫ ሰምተን ነበር እና ይኸ ምንድነው?









Показано 20 последних публикаций.