⚠️ የእሳተ ገሞራ ከመከሰቱ በፊት መወሰድ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች⚠️
በእሳተ ገሞራው ፍንዳታ መክንያት ከሚከሰቱ አደጎች ሰዎችን ለማዳን ከመኖሪያቸው ማስወጣት አስፈላጊ ሆኖ በሚግኝበት ሁኔታ ቤት መልቀቅ ሊኖር ስለሚችል ከመንግስት አካላት የሚሰጡ ትዕዛዞችን እና መልዕክቶችን በትጋት መከታተል። ከቤት ልቀቁ ከተባለ የሚከተሉትን እቃዎች ቀድመው ያዘጋጁ፥-
• ደረቅ ምግቦችና የመጠጥ ውሃ
• ማስኮች
• አስፈላጊ መድሃኒቶች
• ፊት መሸፈኛ ሻርፖች
• ሙሉ ሰውነትን የሚሸፍኑ ልብሶች
• ስልክ መረጃ ለመለዋወጥ
• የእጅ ባትሪዎች
• የመጀመሪያ እርዳታ መሳሪያ ኪቶች
• መነጽሮች
• ሬድዮ
• የጤና ባለሙያዎች ስልክ ቁጥር መያዝ
• እና የመሳሰሉት…
የእሳተ ገሞራ ከተከሰተ በኋላ መደረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
የእሳተ ገሞራው ጭስ የሚደርስበት አካባቢ ከሆኑ ጭሱ የተለያዩ ጎጂ ጋዞችን የያዘ በመሆኑ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያደረጉ
በቤት ውስጥ ከሆኑ
• ጭሱ እንዳይገባ መስኮቶችን እና በሮችን በመዝጋት ቤት ውስጥ መቀመጥ
• የመጠጥ እና የቤት ውስጥ መገልገያ ውሃዎችን በደንብ መክደን
• እንስሳቶችም በጭሱ ምክንያት አደጋ ሊደርስባችው ስለሚችል በቤት ውስጥ በርና መስኮት ዘግቶ ማስቀመጥ
• በተለያዩ ተዐማኒ ከሆኑ የመረጃ ሰጪ ተቋማት የሚሰጡ መረጃዎችን በንቃት መከታተል
• የአየር ማቀዝቀዣ ፋኖችን ማጥፋት
• በቤት ውስጥ ከሰል አለማቀጣጠል
ከቤት ውጪ ከሆኑ
• ወዳገኙት መጠለያ በመግባት መጠለል
• በጋዙ ምክንያት የአይን፣ የአፍንጫ፣ የጉሮሮ ማቃጠል ካጋጠሞት ጭሱ ካለበት ቦታ ወደቤት በመግባት እራስዎን ያርቁ። ይህን አድርገው ማቃጠሉ ካላቆመ ለህክምና ባለሙያ ደውለው ማሳወቅ።
• የተቃጠለ አካል ካለ ወዲያውኑ አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ
• ቅልጥ አለቱ ሊፈስ ወደሚችልበት ቁልቁለታማ ወደ ሆኑ ቦታዎች አለመሄድ
• ፊትን እና የተገለጠ የሰውነት ከፍሎችን መሸፈን፣ መነጽሮችንና የመተንፈሻ ማስኮችን ማድረግ
• የመኪና ሞተር ማጥፋት
• አቅመ ደካማ እና ህጻናትን መርዳት
https://youtube.com/shorts/haG2fnnr4Ps?si=p_8FRKJTmBj9uIsU