أبو هشام📡 አቡ ሂሻም 📡


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


አቡ ሂሻም
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
አቡ ሂሻም
ጠቃሚ ናቸው ያልነውን
1.ፈትዋ
2.ሙሀደራ
3.ቂርአቶች
እንድሁም የተለያዩ ጽሁፎችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን

https://t.me/abu_hisham_tita

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🔺👉የሚገርም ግጥም⚡️⚡️

🔺 ከግጥሙ አገጣጠሙ አንተዬ

አሏህ ይጠብቀው

👉
ቢአኺና አቡ ጁሀይፋ ሐፊዘሁሏህ

🟢 የሌባን ጠበቃ አደባልቀህ ውቃ 👌👌
ክክክ ከግጥሙ የተወሰደ 👆👆👆

🇸🇦አይቶ ማለፍ ያስቆጫል======@👈

🔴
http://t.me/beboruselasa

🔴
http://t.me/beboruselasa


🔺ኡመር ገነቴ የሚባል አሊም ሰምተን አናውቅም ‼️

📌"ሙፍቲነት እኮ በቁመት አይደለም ‼️
ስሙትማ እኔ ለካእባዉ እና ለሀጁ ሙራድ

የለኝም አሏህ ሺቶት ሄድኩኝ እንጅ እኔ ሙራዴ ሸኾቹን ማየት ነዉ አረ ስሙትማ ይሄንን ጠማማ አህባሺ


🎤"ሙፍቲነት በዒልም ነው ኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጠፋ ዓብደሏህ።


https://t.me/qenat_mohammed_surur_dessie/5474


https://t.me/qenat_mohammed_surur_dessie/5474


🚫ያስተውሉ‼️
   🟰➖➖🟰

🤲ዱዓ ከተደረገ በኋላ በእጆች ፊትን ማበስ በተመለከተ የተረጋገጠ የሆነ አንድም ሓዲስ አልተገኘም።
   [ኢማሙ አልባኒ]


ይህ ድርጊት ከፊል ዑለማዎች "ቢድዓ ነው" እስከ ማለት ደርሰዋል።

ስለ ሆነም አንድ ሰው ዱዓ ሲያደርግ እጆቹን ዘርግቶ ያደርግና ከጨረሰ በኋላ ወደ ቦታቸው ይመልሳቸዋል እንጂ በእጆቹ ፊቱን ማበሱ ከረሱልﷺ ያልተገኘ ተግባር በመሆኑ ሊቆጠብ ይገባዋል።

https://t.me/AbuEsmailEbrahim
https://t.me/AbuEsmailEbrahim


አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
ትንሽ ረዘም ብትልም በትግዕግሰት  አንብቧት

የግጥሜ ርእስ
🥀🥀ሶላትን ስገዱ🥀🥀🥀
ሶላትን ስገዱ
ለ አላህ አጎብድዱ
ቀጥ ለጥ ብላችሁ ሰአቷን ጠብቁ
እሳት እንዳትገቡ ሰወች ተጠንቀቁ
ወንድሜ ሆይ ስማኝ
እህቴ ሆይ ስሚኝ
ሶላትን እንስገድ ሰአቷን ጠብቀን
በዛ በጨለማ ነገ እንዳይጨንቀን
ነኪርና ሙንከር አፋጠዉ ሲይዙን
በዛ በጨለማ ስንቀር ብቻችንን
እስኪ አንዴ ንገሩንገሩኝ ምን ይሆን መልሳችን
መልካም ስራ የለን ሶላትን አልሰገድን
ታዲያ እስኪ ነገሩኝ ምን ይሆን መልሳችን
🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋
የተፈጠርንበት አላማ ምንድን ነዉ
ወደ ዱንያ ምድር እኛ የመጣነዉ
አላህ የፈጠረን እስኪ ለምድን ነው
እሱን ካልተገዛን ምን ልንሰራ ነው
የተፈጠርንበት ምንድን ነዉ ካላችሁ
ካላወቃችሁት ምንም ካልገባችሁ
እንግዴዉስ ስሙኝ እኔ ልንገራችሁ
በትንሹም ቢሆን እስኪ ላስታዉሳችሁ
አንደየ አድምጡኝ ከልብ ሁናችሁ
የተፈጠርንበት አላማ ይሄ ነዉ
አላህን በብቸኝነት እንድናመልክ ነው
ትእዛዞቹንም ልንተገብር ነው
በየህዝቦቹ ዉሰጥ መልእክተኛን ልኳል
ከጀሀነም እሳት ሁሉን አስጠንቅቋል
ታዲያ ለምን ይሆን እኛ ያልታዘዝነዉ
የድኑን ምንነት ያልተገነዘብነዉ
የዛኛዉን አለም ምነዉ ረሳነዉ
🥀🌷🥀🌷🌷🥀🌷🥀🌷
ሶላትን ሳንሰግድ መልካም ብንሰራ
ምንም አይጠቅመንም ሆነብን ኪሳራ
የስላም መሰረቶች አምስት አይደሉ እዴ
ነብዩስ በሀድስ ተናግረዉ የለዴ
ከነሱ መካከል ሶላት አንዱ ነው
በሷሂህ ሀድስ የተዘገበዉ
አብደሏህ ኢብኑ ኡመር ያስተላለፈዉ
አላህ በቁርአኑ የተናገረዉ
እንደ ቀላል ይተን እኛ አሳለፍነዉ
ኧረ ምን ማሳለፍ ጭራሹንም ተዉነዉ
የዛኛዉን አለም በጣም ዘነጋነዉ
እነዚያ ሰሀቦች ሰግደዉታል እኮ እጀሀድ ላይ ሁነዉ
እጀሀድ ላይ ሁነዉ ሶላትን እንዲተዉ አላህ አልፈቀደም
እጀሀድ ላይ ሁነዉ ሰግደዉታል ሁሉም
እኛ ግን እረሳን ይህን ሁሉ ነገር
የምንቆይ መሰለን በዱንያ ሀገር
🥀🌷🥀🌷🥀🌷🥀🌷🥀🌷
ጠፊ መሆኗን እኛ ዘነጋናት
ሶላትን አሳለፍን ለዱንያ ህይወት
አሔራን እረስተን ዱንያን አስቀደምን
የ አላህን ቅጣት በጣም ረሳን
ሶላትን ለመስገድ እንዴት ተዘናጋን
ወንድሜ ሆይ ለምን ❓
እህቴ ሆይ ለምን❓
የዛኛዉን አለም ምነዉ ዘነጋችሁ
በዱንያ ብቻ ተጠመዳችሁ
ሶላትን ለመስገድ ምነዉ ከበዳችሁ
ለምንድን ይሆን እንደ ተራራ የከበዳችሁ
ምነዉ ዘነጋችሁ
🌹🌹🥀🌺🥀🥀🌹🥀🌹
ወንድሜ ስማማ ልንገርህ
ኳስን ለማየት ስንት ደቂቃ ትቀመጣለህ
ፊልም በማየት ስንት ሰአታት ታባክናለህ
እህቴ ስሚማ ልንገርሽ
ፊልም ለማየት ስንት ደቂቃ ትቀመጫለሽ
ብዙ ደቂቃ ነዉ መቸም አትዋሹኝም
ምነዉ ደከማችሁ ለ አምስት ደቂቃ ሶላት ዉስጥ ለመቆም
🌹🌺🌹🌺🌹🥀🌹🌺🌹🎋🥀
ለምድን ይሆን እንደ ተራራ የሆነባችሁ
ፊልም ለማየት ተቀምጣችሁ
ኳስን ለማየት ተቀምጣችሁ
ለሶላት ግን አቃታችሁ
እስኪ ምን ይሻላል❗️
አንተ ሶላት ትተህ ሙስሊም ነኝ ልትል ነው
የ አላህን ትዛዝ ወዴት ልትጥል ነው
እኛ ዘንጊወች መሆናችንን አላህ ነገረን
ሶላትን ስገዱ ጌታችንም አለን
እንደምንዘናጋ ይሄዉ ጠቀሰልን
እስኪ ለማስረጃ  ከቁርአን አንቀጽ ልጨምርላችሁ
ዉሸቴን አይደለም ይሄዉ ልንገራችሁ
ከሱረቱል መርየም ትንሽ ላስታዉሳችሁ
💫💫💫💫💫💫💫💫💫
فَخَلَفَ مِنۢ بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّبَعُوا۟ ٱلشَّهَوَٰتِ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا
(ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ፡፡)
🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙
እስኪ ሌላም አንቀፅ ልጨምርበት ነዉ
አላህ በቁርአኑ የተናገረዉ
ያኔ በቂያማ እንጠየቃለን
በዱንያ ህይወት ላይ የዘነጋናትን
ምን ይሆን መልሳችን ያኔ ስንጠየቅ
ዱንያ ላይ ሁነን ስለ ድን ሳናዉቅ
ይሄዉ በቁርአኑ አላህ ነግሮናል
በሱረቱል ሙደሲር ይሄዉ ገልፆልናል
مَا سَلَكَكُمْ فِى سَقَر
قَالُوا۟ لَمْ نَكُ مِنَ ٱلْمُصَلِّينَ
وَلَمْ نَكُ نُطْعِمُ ٱلْمِسْكن
وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ ٱلْخَآئِضِينَ
وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوْمِ ٱلدِّينِ
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃
እስኪ ከሀዲስም ትንሽ ልንገራችሁ
ብቻ እናንተ አድምጡኝ ከልብ ሁናችሁ
وقد ثبت من حديث بريدة رضيالله عنه عند الترمذي، ان النبي صلاالله عليه وسلم قل፡
العهد الذي بيننا وبينهم اصلاة ،فمن تركه فقد كفر.
(ነብያችን አሉ በኩፋሮች መካከልና በሙስሊም መካከል ያለዉ ልዩነት ሶላት ነዉ
ሶላትን ከተወ እሱ ካፊር ነዉ).

እኔ አይደለሁም ይህንን ያልኩት
ነብዩ ናቸዉ የተናገሩት
በል ተነስ ወንድሜ ስገድ ሶላትህን
በይ ተነሽ እህቴ ስገጅ ሰላትሽን
ነገ በቂያማ መግቢያዉ እንዳይጨንቀን
ሰኔ 24/10/2015 E.C ይችን ሞካከርኳት
በትንሿም ቢሆን እንዲትማሩባት
በስተመጨረሻም እጨርሳለሁኝ
ስህተቴን አይታችሁ አደራ እንዳታልፋኝ
የሰዉ ልጅ ነኝና እሳሳታለሁኝ
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
كتبته✏️📝
ام ريان بنت حسن
🌸🌸🌸ከወሎ ጢጣ🌸

በድጋሜ የተለቀቀች ነች
ሊንክ መቁረጥ የተከለከለ ነዉ

https://t.me/kewollotita




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🌹🍀🌹🍀🌹🍀🌹🍀🌹
https://t.me/kewollotita
🌹🍀🌹🍀🌹🍀🌹🍀🌹


ልዩነቱ ግልጽ ነው


ከጣፋጭነቱ ጋ።

ምንም አይነት ቆሻሻ
እንዳይነካው ተሸፋፍኖ

ስለ ተቀመጠ ሁሉም ይወድዋ።
በሂጃብ የተሸፋፈነችውም

እንደዛው ተወዳጅ እና
ተፈላጊ ናት ምክንያቱም
የንጽህናዋ ምልክት ነው

ተገላልጣ የምትሄደዋል ግን
ተልጦ እንደ  ተጣለ ሙዝ

ሁሉም እየመጣ ስለሚለጠፍባት
የሚፈልጋት አይኖርም

https://t.me/AbuEsmailEbrahim


☞ጀሀነም የሚገባው ወደ ጀሀነም ጀነት የሚገባውም ወደ ጀነት ከገባ በኋላ
☞ አንድ ተጣሪ እንዲህ ሲል ይጣራል!
አንተ ሙሐመድ! ተደሰተክ ወይ?
እርሳቸው እንዲህ ይለሉ«ጌታዬ! ወላሂ አልተደሰትኩም። ከኡመቶቼ እሳት ውስጥ የቀረ አለ
አላህም ለመላኢኮች «ቅንጣት ታክል ኢማን በቀልቡ ያለውን ሁሉ ከእሳት አውጡ» በማለት ያዛቸዋል። ከዚያም ጀሀነም በሯ ይከፈትና የተወሰነው የሙስሊሙ ክፍል ወጥቶ ወደ ጀነት ይተማል።
አላህ በድጋሚ «ሙሐመድ ሆይ! ተደሰትክ?» ይላቸዋል።

«ጌታዬ ባንተ እምላለሁ! አሁንም ከህዝቦቼ የቀሩ አሉ» ብለው ያለቅሳሉ!
አላህም ለመላእክቱ «አይኑ የትንኝ ራስ የምታክል እንባም ብትሆን እኔን ፈርታ ያነባችን ሁሉ አውጡ» በማለት ያዛል።
ከዚያም «ያ ሙሐመድ! አሁንስ ተደሰትክ?» ይላቸዋል።
«ወላሂ አልተደሰትኩም። አሁንም ከኡመቴ የቀሩ ሰዎች አሉ። ይላሉ ረሱላችን ﷺ »
አላህ ለመላኢኮች «ላኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ያለውን በጠቅላላ ከጀሀነም አውጧቸው» በማለት ያዛል። ጀሀነም በሮቿ ተከፍተው ሁሉም ወደመስካሪዎች ጎራ ይነጉዳሉ።

ከወርቅና ከሉል በተሰራ ግንብ ውስጥ ይነዳሉ። ባማረ መዓዛ ይታወዳሉ። ውስጥ የነበሩት የጀነት ሰዎች የተበለጡ እስኪመስላቸው ድረስ እነዚህ ሰዎች ውብ ይሆናሉ። ከዚያም ወደ ጀናህ እንዲገቡ ይደረጋል። ይሄኔ ለመጨረሻ ጊዜና ለዘልዓለም ጀሀነም ትዘጋለች!!
በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ፦
« ﺭُّﺑَﻤَﺎ ﻳَﻮَﺩُّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ ﻟَﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻣُﺴْﻠِﻤِﻴﻦَ
እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ (ሱረቱ አል-ሒጅር - 2)
አላህ የርሳቸውን ሸፈዓ የምናገኝ ያድርገን!!
ሰሉ ዐለል ሐቢብ!(ﷺ)✅ምንኛ ያማር. እና የተቀደስ ንግግር. የአላህ. እንደኛ. ሳይሆን እንዳንተ እዝነት.  ጀንተን ወፍ ቀን ያውዱድ الله ይዘንልን አዩሀል ኢህወቱ ወለ አህዋት ያረብhttps://t.me/+sTvNfojxMXVjMTE8


እንደ ዝናብ  ሁን

ሲመጣ   ሲቀጣጭ
ሰወችበደስታ  ይበሰራሉ

ደርሶ  ከዘነበ
ይጠቀሙበታል

ጨርሶ ሲሂድ
   ፋናውን  ይተውላቸዋር
 
  ሳይመጣ ከቆየ
    ይናፍቁታ

https://t.me/AbuEsmailEbrahim


⛔️አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡
||
ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን...
*
እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:-
«አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል።

ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል።
:
ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ  ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ።
:
እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል...
ሃሃሃ!

ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው...
:
ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ...
(ያዝ እንግዲህ¡)

በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው።

ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት።
ሃሃ!
:
ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት።

ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ።

ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል።

ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው።
እህእ!
:
ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ።

ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ።

ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ  አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ።
:
ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ  እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም።
ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም።
:
አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ

ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ።
እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ።
ሃሃሃ!
:
ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው  መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ።
በዚህ መልኩ ሁሉም  ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...»
ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ። https://t.me/+sTvNfojxMXVjMTE8


☀️"ጅል እዳ ነው አሉ" ትላለች ኡሚ.................... ሰውየው እኮ ነው ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እናቱ የሞተችበት ሰው ቤት ለቅሶ ሊደርሱ ሄደው  አብሽር እሷንም አላህ ይርሃማት ያንተ እናት እኮ የሁላችንም እናት ነበረች ሲሉ ሰምቷል................ ከዚያም በሌላ ቀን ሚስቱ የሞተችበት ሰውዬ ጋር ለቅሶ ሊደርስ ይሄዳል ለሰውየውም "አብሽር  እሷንም አላህ ይርሃማት ያንተ ሚስት እኮ የሁላችንም ሚስት ነበረች " ብሎ አቧራ አስነስቶ ተመለሰ እላችኋለሁ..ክክክክክ https://t.me/+sTvNfojxMXVjMTE8


Репост из: قناة أبي زكريآ الأثري ከጦሳ ማዶ ደሴ
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
https://t.me/kewollotita


    ቆንጅዬ፣ ዓሊም እና የዓሊም ልጅ የተዳረችበት: ማራኪ እና እውነተኛ ታሪክ!!

  ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ብርቅዬ ከሆኑ የኢስላም ቀደምት ምሁራኖች ውስጥ አንዱ ነው። የዕውቀት ማዕዱ በጣም በርካታ የሆኑ የዲን ተማሪዎች ተሰብስበው ይጣዱት እንደነበር ታሪክ ያረጋግጣል። ከዕለታት በአንዱ ቀን ተማሪዎቹ ሲመለከት ከመሃል አንድ ወጣት ከትምህርት ቦታው ይጠፋል። ሲጠባበቀው ቆየና ወደ ትምህርት ቦታው የተመለሰ ቀን ጠየቀው።

"ወዳጄ ሆይ! የት ሆነህ ነው እስከዛሬ ያልመጣኸው?" ሲል ጠየቀኝ።  ይላል

"ባለቤቴ ሙታብኝ እሷን እየደፈንኩ እና በሷ ጉዳይ ተወጥሬ ነው።" ብዬ መለስኩለት

ሰዒድ:  "ታድያ አትነግረንም ነበርን? ቢያንስ እኮ መጥተን እንኳ እናፅናናህ ነበር።" አለኝ


አስከትሎም:  "እሺ አሁንስ ሌላ ለማግባት ያሰብከው ነገር አለን?" አለኝ

"ኣ…ኢ…ኢ እኔ እኮ ከሦሥት ዲርኸም ሌላ የሌለኝ ሰው ነኝ ማን ይድረኛል?" አልኩት።

ሰዒድ:  "ሱብሃነላህ!! ሱብሃነላህ!! ሦሥት ዲርኸም አንድን ሙስሊም አትሰትርም ማለት ነው??" አለኝ በመገረም

"ማን ይድረኛል??" አልኩት

"እኔ!!" አለኝ

"ያቺ መሪዎች እና ሚኒስትሮች እየጠየቁ የተከለከለችዋ የሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ልጅ!?" አልኩት

"እኔ እድርሃለው።"
  አለኝና እዛው ከመስጂድ አካባቢ የነበሩ ሰዎች ጠርቶ ሰበሰባቸውና
  "እከሊት የእከሌ ልጅ: የእከሌ ልጅ ለሆነው እከሌ በሁለት ዲርኸም ድረነዋል!!" ብሎ ኒካህ አሰረልን።


  በዚህ ጊዜ በደስታ የምከንፍ እየመ ሰለኝ ስፈናጠር ወደ ቤቴ ሄድኩኝ። የመግሩብ ወቅት ደረሰ፤ ጾመኛ ነበርኩኝና ለማፍጠር ዳቦዬ ምናምን ይዤ ቁጭ እንዳልኩ የቤቴ በር ተንኳኳ

"ማን ነው?" ስል

"ሰዒድ ነኝ።" የሚል ምላሽ ሰማሁ


  አእምሮዬ ላይ የማውቃቸው ሰዒዶች ሁሉ ተመላለሱብኝ; ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ሲቀር፤ ምክንያቱም ሳውቀው አርባ ዓመታት በሙሉ ከቤቱ ወደ መስጂድ: ከመስጂድ ወደ ቤቱ ሲመላለስ እንጂ ሌላ ቦታ አይቼው አላውቅም ነበር።

ተነስቼ በሩን ስከፍተው ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብ ነው

በውስጤ "በቃ ሀሳቡን ቀይሮ ነው" አልኩኝ

"በዚህ ሰዓት ለምን መጣህ? ብታስጠራኝ እኮ እኔ እመጣልህ ነበር።" አልኩት

"ኣ…ኣ…ይ የአንተ ዐይነቱ እኮ ወደ እሱ ይመጣል እንጂ እሱ እንዲመጣ አይጠራም።" አለኝ


  "እንግዲያውስ ድረንሃል: የዛሬዋ ምሽት ሚስትህ እኔጋ ሆና ላጤ ሆነህ ላሳድርህ ስላልፈለኩ ይዤልህ መጥቼ ነው።" ብሎ ከኋላው ጥቁር ለብሳ ቆማ የነበረችው ወደ ቤት ገፈተራት።

  በድንጋጤ መሬት ላይ ወደቀች።
"بارك الله لك وبارك عليك
እቺ ሚስትህ ናት"
አለኝና ትቶን ሄደ።


  ስመለከታት የውበት ማማ የተላበ
ሰች ሴት ናት። በአላህ እምላለሁ ዐይኔ ከእሷ በፊት እንደዚህ ያለ ውበት ዐይታ አታውቅም።


  እየሮጥኩኝ ወጥቼ ጎረቤቶቼን ጠራኋቸው "ሰዒድ ኢብ
ኑ ሙሰይብ ልጁን ድሮኛል: ይኸው አሁን ከመሸ ነው ይዟት የመጣው: ሄጄ ለእናቴ እስከምነግራት ገብታችሁ አጫውቷት።" ብያቸው ወደ እናቴ ሄድኩኝ።

ለእናቴ ሄጄ ስነግራት
  "እኔ መጥቼ ሦሥት ቀናት ድረስ ሞሽሬያት እስከምሰጥህ ድ
ረስ ብትጠጋት ፊቴ በፊትህ ላይ ዕርም አድርጌብሃለው: እኔ እስክመጣ እንዳትነካት" አለችኝ።


  እናቴ መጥታ ሦሥት ቀናት ሞሽራ አስዋበቻትና ገባሁኝ: "ወላሂ ዐይኔ እንደሷ ያለ ውብ ዐይቶ አያውቅም።"
ከተ
ናገረች ያማረ ንግግር ነው የምትናገረው: ዝም ካለችም ያማረ ዝምታ ነው ዝም የምትለው።


  ከእሷ ጋ አብሬ አንድ ወር ቆየሁኝ: ከሷ ያ
የሁት ነገር የለም; ቀን መጾም እና ለይል መስገድ ቢሆን እንጂ። ከወር በኋላ ወደ ሰዒድ ሄጄ ትምህርቴን ለመቀጠል ፈለኩኝ።

"ወዴት ነው ምቴደው?" አለች


"ለመማር ወደ ሰዒድ" አልኳት

"አርፈህ ተቀመጥ!! የሰዒድ ዒልም በአጠቃላይ እኔጋ አለ፤ እሱ የሚሰጥህ እኔ እሰጥሃለሁ።" አለችኝ


  ሆኖም ከአንድ ወር በኋላ ወደ ሰዒድ ሄድኩኝ: መቀመጫው ላይ ሆኖ ሲያየኝ ፈገግ አለ። ሁሉም ሰው ጨርሶ እስኪወጣ ድረስ ግን ምንም አላናገረኝም።

  የነበረው ሰው ጨርሶ ከወጣ በኋላ መጥቼ ከፊት ለፊቱ ተቀመጥኩኝ።
"እንግዳችሁ እንዴት ናት?" አለኝ

"በጣም ደስስስ በሚል ሁኔታ" አልኩት።

"እንግዲያውስ የማያስደስትህ ነገር ካገኘህ ዱላህን …………:"
አለኝና ሀያ ሺህ ዲናር በእጄ አስጨበጠኝና

"አንተ እና እሷ ለጉዳያችሁ ተጠቃቀሙባት።" ብሎ ተሰናበተኝ። ይላል።
                   ታሪኩ አበቃ

ምንጭ
📚[سير أعلام النبلاء ترجمة سعيد ابن مسيب /ج٤/ ص٢٣٤]



ታሪክህን መርምር: ዕውቀትህን ጨምር!


🪴https://t.me/kewollotita


Репост из: أبو الناموس الأثري ""ከጦሳ ማዶ ደሴ ""
⭕️ልዩ የውይይት ጥሪ📢📢📣📣📣

( ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ وَجَادِلْهُم بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ )
النحل (125)

👉አላህ በተከበረ ቁርአኑ እንድ ይላል:—

""""ወአ አላህ መንገድ ሰወችን በ ጥበብ(ሀቅን በመናገር) እና በመልካም ግሳፄ ጥራቸው፣ በመልካምም ተከራከራቸው፣ፈጣሪህ ከቀጥተኛው መንገድ የጠመሙ ሰወችን ያውቃቸዋል፣እንደዚሁም ቀጥተኛውን ነገር የተመሩትንም ያውቃል""""

⚠️ማሳሰቢያ:—ለውይይት የሚመጣ አካል መረጆ አቅርቦ የሚሰጠውን መረጃ አጣጥሞ ቁርአንና ሀድስ የሚደግፈውን ሀሳብ ለመቀበል ነይቶ አላህን ፈርቶ ይቅረብ‼️

⭕️ውይይቱ የሚሆነው

ኡዙር ቢልጀህል በተመለከተ ሁለቱ አቋም ያላቸው አካላቶች ነው

1⃣አንድ አካል ሳያውቅ ትልቁን ሽርክ ማለትም ለቀብር እየሰገደ፣ለቀብር ስለት እየተሳለ ፣ለቀብር እያረደ፤የሞቱ ሰዎችን ድረሱልኝ እያለና የመሳሰሉ ሽርኮችን እየሰራ ፦
🔥ልክ ሽርክ እንደማይሰራው ሙስሊም ሙስሊም አይባልም  ፤ ሙሽሪክ የሚል ስያሜ ይሰጠዋል ።የማስሊም መኗኗርም አንኗኗረውም ማለትም ( ያረደው አይበላም፣ኢማም ቢሆን ከኋላው አንሰግድም፣ቢሞት ከሙስሊሞች መቃብር አይቀበርም ፣አላህ ይማረው አይባልም፣ ሶደቃ አይሰጥለትም ወ.ዘ.ተ ) አይደረግለትም ልክ እንደሙሽሪኮች ነው በሚሉ አካላቶች(እኛ) እና ....

2⃣አንድ አካል ሳያውቅ ትልቁን ሽርክ ማለትም ለቀብር ቢሰግድ፣ስለት ቢሳል ፣እርድ ቢያርድ፤የሞቱ ሰዎችን ድረሱልኝ ቢል የመሳሰሉ ሽርኮችን ቢሰራም ፦
🔥ልክ ሽርክ እንደማይሰራው ሙስሊም፤ ሙስሊም የሚል ስያሜ ይሰጠዋል ።የሙስሊም መኗኗርም እንኗኗረዋለን ማለትም ( ያረደው ይበላል፣ኢማም ቢሆን ከኋላው እንሰግዳለን፣ቢሞት ከሙስሊሞች መቃብር ይቀበራል ፣አላህ ይማረው ይባልለታል፣ ሶደቃ ይሰጥለታል ወ.ዘ.ተ ) ይደረግለታል በሚሉ አካሎችና

👉 ማሳሰቢያ ፦ የአኼራውን በተመለከት ልዩነት የለም ማለትም ጃሂል ከሆነ ኡዙር ይሰጠዋል ይላሉ። በ አኼራ ጉዳይ የተለየ አቋም ያለው ካለ ቀድሞ ያሳውቀን

⭕️ለውይይቱ የተጋበዙ አካላቶች
—ጀማል ያሲን
—አቡ ቀታዳ አብደላህ ሙዘሚል
—አብራር እና አምሳያወቻቸው

⛔️ከ ጀምኢዮች
—ኢብኑ ሙነወር
—ሳዳት ከማል
—ከድር ከሚሴ

⭕️ለውይይቱ ዝግጁ የሆነ በ ተራ ቁጥር2⃣ የተቀመጠውን ሀሳብ ያለው በ እዚህ ቦት ስልክና ስሙን ይፃፍልን...❗️❗️❗️

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Abu_Ketada_Esmael_Bot

👇👇በዚች ኦን ላይን 👇👇👇
https://t.me/Mewweyaya_11


በሀበሻዊ ቃሪ ከረም መሀመድ

⭐️018 sura al-kehf


⭐️018 سورة الكهف

🎙️🎧 Qari kerem Mohhamed Al-Habashi


🎙️🎧 بصوت القارئ كرم محمد الحبشي حفظه الله



🚗🚕🚙ለወዳጂ ዘመዶዎ ሸር ሸር ያድርጉ የአጂሩ ተካፋይ ይሁ

ከተመቻቹ 👍👍👍👍👍


ካልተመቻቹ 👎👎👎👎👎

           አሳውቁን ይቀጥላል

የጁምአ ግብዣ በፊት የተለቀቀው ሙሉ ሱራው አይደለም የአሁኑ ሙሉውን ነው


http://t.me/qari_kerm_alhabeshi




➷◉አንዳንድ ወንድሞች ማግባት መፍታት ልምድ አርገውታል እንደት ታየዋለህ መልሱን በፈገግታ ያዳምጡ
ኡስታዝ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ ዓብደሏህ {{حفظه الله تعلى }


https://t.me/abureslan7370




Репост из: {وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَىٰ تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ}
አስቸኳይ መልዕክት ለደሴ ሠለፍዮች በሙሉ :-

🔴 👉 የወንድማችን መሃመድ አወል ( ሃያ
ት ሠፈር ጀጎላ ) እናት ወደ አኺራ አልፈዋል !!


ማንኛውም በደሴ ከተማ የምትገኙ ሠለፍዮች በሙሉ በቦታው ላይ በመገኘት የወንድማችንን እናት እንድትሸኙለት ስንል በጥብቅ እናሳስባለን !!

🔴 👉 መልዕክቱ አሁን ስለሆነ የደረሠን በየትኛውም ቦታ ያላችሁ ወንድሞች በስልክም እየተደዋወላችሁ በጧት በቦታው ላይ እንድትገኙ !!

የመቅበራ ቦታው :-  ጀጎላ ባለው ክሬቸር ፊት ለፊት በሚገኘው ተራራ ውስጥ ነው !!


Репост из: የሰለፍያ ሴቶች ጀመዓ
➴ምክር ከጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ«

ልጄ_ሆይ! ፧ በዝምታየ ተፀፅቼ
አላውቅም፡፡
ልጄ ሆይ ፧ ከጠጣህበት የውሃ
   ጉድጓድ ውስጥ ድንጋይ አታስገባ፡፡

ልጄ ሆይ ፧ ምላስክን 'አሏህ ሆይ ማረኝ
ማለትን አለማምድ ለአሏህ ጠያቂን
የማይመልስበት ሰዓታት አሉትና፡፡

ልጄ_ሆይከሌላ ሰው እጅ ካለ በሬ
      በእጅህ ያለች ወፍ ትበልጣለች፡፡


~ልጄ_ሆይ
፧ ከመገረም ጋር አትሳቅ;
ከማይመለከትህም ነገር አትጠይቅ፡፡
ልጄ ሆይ ፧ ሁለት ነገሮችን አታውሳ ፧ ሰዎች
ወዳንተ ያደረጉትን በደልና ፣ ለሰዎች ያደረከውን
መልካም  ነገር፡፡

ልጄ_ሆይ ፧ በጣም ጣፋጭ አትሁን
እንዳትዋጥ መራራ አትሁን እንዳትተፋ ፡፡
ልጄ ሆይ ፧ ከጥጋብ ላይ ጥጋብ ሆነህ
አትመገብ ; ከምትመገበው ለውሻ ብትጥለው
የተሻለ ነው ፡፡

ልጄ_ሆይ ፧ የአሏህን ፈራቻ ንግድ አድርገህ
ያዘው ; ትንሽ የማይባል ትርፋማ ሆኖ
ይመጣልሀል፡፡

ልጄ ሆይ ፧ ጥበብ (እውቀት ) ምስኪኖችን
የነገስታት ደረጃ አድርሳለች፡፡ ልጄ ሆይ ፧ አደራህን በብድር ላይ ; ብድር የቀን ውርደት
የማታ ጭንቀት ነው ፡፡

ልጄ_ሆይየማይረዳን ከማስረዳት
ቋጥኝን ከቦታው ማንሳት ይቀላል ፡፡


ልጄ_ሆይ ፧ ባወከው  ነገር  እስከምትሰራ
ያላወከውን አትማር፡፡ልጄ ሆይ ፧መጥፎ ጎረቤት
ከከባድ ብረት በላይ ይከብዳል ;መራራ ነገሮች
ሁሉ ቀምሻለሁ ከድህነት በላይ መራራ ነገር
አልቀመስኩም፡፡

ልጄ ሆይ ፧ አንድን ሰው ወንድም ለማድረግ
ከፈለክ መጀመሪያ አስቆጣው በቁጣው ጊዜ
ካለፍክ ...ካልሆነ ተጠንቀቀው ፡፡

ልጄ_ሆይበሰው ቤት ውስጥ ከሆንክ
አይንህን ጠብቅ፤በስብስብ መካከል ከሆንክ
ምላስክን ጠብቅ ፤ በሰላት ውስጥ ስትሆን
ልብህን ጠብቅ ፡፡


የእብነ ከሲር 'ቢዳያህ ወንኒሀያህ' ከሚለው
መፅሀፋቸው ውስጥ የሉቅማን ምክሮች
ተጠቅሰዋል ፡፡
       

https://t.me/Ye_setoch_Jemea

🛍ወደ ቁርአን ቻናላችን ጆይን ይበሉ ልበዎን በጌታዎ ቃል ያርጥቡ
👇👇👇👇👇
https://t.me/quranbchaquranbcha
ግሩፓችን
https://t.me/+XnkC6PRJm-llNGJk

                   👉ይ🀄️ላ🀄️ሉን👈

Показано 20 последних публикаций.