AWACH SACCOS Ltd.


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Экономика


ኅብረት ሥራ ማህበራችን የሚያከናውናቸው ተግባራት
የቁጠባ እና የብድር አገልግሎት
አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት
የትምህርት ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት
+251-11-557-97-98
+251-11-557-88-89
+251-11-557-98-99
+251-11-868-47-44
saccawach@gmail.com
https://www.facebook.com/AWACHSACCOS
@awachsaccos

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Экономика
Статистика
Фильтр публикаций


አዋጭ ከአርቲስት መቅደስ ፀጋዬ ጋር የገባውን የብራንድ አምባሳደርነት ውል አደሰ፡፡

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማኅበር ባለፈው አንድ አመት አርቲስት መቅደስ ፀጋዬን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ በመሾም ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ሶስት አመታት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የብራንድ አምባሳደርነት  የስምምነት ፊርማ በአዋጭ ዋና ቢሮ አድርገዋል፡፡  በመቀጠል የኅብረት ስራ ማኅበሩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ አርቲስቷ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ሰፋፊ ስራዎችን ከአዋጭ ጋር በመስራት መልካም ገፅታ መገንባትዋን እና አርቲስቷ ለቀጣይ ሶስት አመታት በጋራ መስራት የሚያስችላትን የብራንድ አምባሳደርነት ውል መፈራረሟን ገልጸዋል ፡፡
አርቲስት መቅደስ ፀጋዬም በበኩሏ ከአዋጭ ጋር መስራት ከሀገር ጋር መስራት ነው። በነበረኝ አንድ አመት ቆይታ አዋጭ ሰፊውን ማኅበረሰብ ያቀፈ ፣ለማኅበረሰብ የቆመ ኅብረት ስራ ማኅበር መሆኑን አይቻለሁ። የዚህ ኅብረት ስራ ማኅበር ብራንድ አምባሳደር በመሆኔም ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብላለች፡፡


አዋጭ ለኅብረት ስራ ማህበሩ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ሰጠ፡፡
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መሰ ኅብረት ስራ ማኅበር ከየካቲት 26-28/2017 ዓ.ም ድረስ ተቋማዊ ባህል ግንባታ  በሚል የስልጠና ርዕስ ላይ ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ለተከታታይ ሶስት ቀናት ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ስልጠና ሰቷል፡፡ ስልጠናውም አንድ ተቋም ምን ዓይነት የስራ ባህል ሊኖረው እንደሚገባ፣ መልካም ተቋማዊ ባህልን እንዴት ማስቀጠል እንደሚቻል እና ለሰራተኛ ምቹ የሆነ ባህልን እንዴት መፍጠር እንደሚገባም ጭምር ስልጠና ተሰቷል፡፡ የስልጠናው መዝጊያ ላይ የተገኙት የአዋጭ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ ኃላፊዎች የወሰዱትን ስልጠና በየስራ ክፍላቸው በስራቸው ላሉ ሰራተኞች  ማስተላለፍ  እና ተቋማዊ ባህል ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡


አዋጭ በፋውንዴሽኑ በኩል  ለዲቦራ ፋውንዴሽን የገንዘብ  ድጋፍ አደረገ።
ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም አዋጭ ፋውንዴሽን በዲቦራ ፋውንዴሽን ዋና ቢሮ በመገኘት የገንዘብ  ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ በድጋፉ ወቅት የአዋጭ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ሸለመ መልእክት ሲያስተላልፉ አዋጭ በአዋጭ ፋውንዴሽን በኩል ገንዘብ ነክ ያልሆነ ዘላቂ ድጋፎችንም በማድረግ ሁለቱ ፋውንዴሽኖች በአጋርነት መስራት የሚያስችላቸውን ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል፡፡
የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች  አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው አዋጭ ያደረገላቸውን ድጋፍ በማመስገን አዋጭ ሁሌም ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጎን እንደሆነና በተለያየ መንገድ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ያለ ተቋም መሆኑንም መስክረዋል፡፡ በድጋፉም ላይ  የአዋጭ ብራንድ አምባሳደር አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ  ተገኝታ መልዕክት አስተላልፋለች።






እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረስዎ!













Показано 12 последних публикаций.