ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ
ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ !
"ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? "
ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል !
ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር
@JemalEndroAbuMeryem

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: SadatKemal Abu Meryem
አሁን የሱረቱ አን-ነባእ አጭር ማብራሪያ live https://t.me/SadatKemalAbuMeryem


ወንድምና እና እህቶቻችን ሆይ !
ለመልካም ነገር በር መክፈቻ መሆን ካልቻልን ለመጥፎ ነገር በር መክፈቻ እንዳንሆን እንጠንቀቅ !


https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15472


አስቼኳይ ክፍት የስራ ማስታወቂያ

~~~
bsc ners 3 ሶስትአመት የስራልምድያለው
ቦታው ቡታጅራ ነው
ደመወዝ 15000
ትራንስፖርት በነፃ
ዱቲአለው

ይሄን የሚያሟላ
0933519871 ይደውል

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15471


Репост из: የቡታጅራ አህለሱና ቂራኣትና ዳዕዋ ቻናል
ታላቅ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም      
           በቡታጅራ ከተማ!

=
እነሆ የፊታችን ሐሙስ ቀን 06/06/2017 ከመግሪብ ሰላት በኋላ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ቀን 08/06/2017 ድረስ የሚቆይ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም በቡታጅራ ተሰናድቶ ይጠብቅዎታል።

በዕለተ እሁድ ደግሞ ሰፋ ባለ መልኩ በኢንሴኖ ከተማ ደማቅ ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል። በዚህ ፕሮግራም የተለያዩ ጊዜውን ያማከሉ አርእስቶችና ረሳኢል በኮርስና ዳዕዋ መልክ ይሰጣሉ።

እርሶም የዚህ ታላቅ ፕሮግራም ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጥሪ ስናቀርብልዎ በታላቅ ደስታ ነው።

☞ ተጋባዥ እንግዶች፦
     * ሸይኽ አወል አሕመድ አልከሚሴ
     * ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አልከሚሴ እና ሌሎችም ኡስታዞችና ዱዓት ይገኛሉ።

«እውቀትን ፍለጋ መንገድን የጀመረ አላህ የጀነትን መንገድ ያገራለታል።» ረሱልﷺ

https://t.me/butajira_Qirat_daewa_group


የብዙዎቻችሁ መልክት ደርሶኛል ለሁላችሁም ጀዛኩሙሏህ ኸይረን ለዱዓችሁ ለሁሉም የሱና ወንድም እህቶቻችን አሏህ ያቆይልን አላህ ይጠብቅልን እናንተንም !

አሏህ ምንም ሳያጎድለን መልሶ ላገናኘን አልሃምዱሊላህ !


اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎

ያጀመዓ እንዴት ናችሁ ...?

በአሏህ እገዛ ትላንት ከእስር ቤት ተፈተናል አልሃምዱሊላህ !

ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ አቡ መርየም

اللهم لك الحمد

ولله الحمد والمنة


Репост из: SadatKemal Abu Meryem
ብርቅዬ የኢስላም ልጆች
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/7032




Репост из: SadatKemal Abu Meryem
በወጣትነት መቀለድ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/7030




Репост из: قنات لشيخ جمال الذهبي الصباح
🔗 📌 بِسْــــمِ ﷲِ الرَّحْمـٰــــــــنِ الرَّحِيمِ 📌


🎁በሸይኽ ጀማል ዘሀቢ ተቀርተው የተጠናቀቁ ቂርአቶች


📚الأصول الثلاثة
https://t.me/SheikhJemalZehabi/130

📚الأصول الستة
https://t.me/SheikhJemalZehabi/139

📚القواعد الأربعة
https://t.me/SheikhJemalZehabi/139

📚أصول السنة
https://t.me/SheikhJemalZehabi/160

📚لمعة الإعتقاد
https://t.me/SheikhJemalZehabi/173

📚العقيدة الواسطية
https://t.me/SheikhJemalZehabi/199

📚العقيدة الإسلامية
https://t.me/SheikhJemalZehabi/226

📚  شروط لا إله إلا الله ونواقض الإسلام
https://t.me/SheikhJemalZehabi/287


=ሪከርዶችን በነዚህ ሊንኮች ታገኙታላቹህ

🔗 https://t.me/SheikhJemalZehabi


ወቅታዊ የሆነ ጥያቄና መልስ የኦን ላይን ግብይትን በተመለከተ

أبو حاتم
https://t.me/UstazKedirAhmed




Репост из: ጃዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የዳዕዋና የቂርዓት ማዕከል {Official Channel }
የደዕዋ ድግስ በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ


ታላቅ የምስራች ለደሴ እና አከባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰብ  በሙሉ እነሆ የፊታችን እሁድ በቀን 25/05/2017 ዓ·ል  በአላህ ፍቃድ የወሎ መናገሻ እና እንብርት በሆነችው  ደሴ  ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ  ከአድስ አበባ ፣ ከአፋር፣ ከኸሚሴ፣ እና  ከሌሎችም ሀገራት በሚመጡ ብርቅዬ መሻይኾችና ኡስታዞች   ከጧቱ 3:00 ጀምሮ  እጅግ በደመቀ እና ባማረ መልኩ  የደዕዋ ድግስ ተዘጋጅቶ ሲጠብቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው
 
የዕለቱ ተጋባዥ መሻይኾችና ኡስታዞች


① ሸይኽ አወል አህመድ አል ኸሚሴ
ርዕስ:– ረመዷንን እንዴት እንቀበለው

② ኡስታዝ አብዱረህማን ሰዒድ(አቡ ሒዛም)
ርዕስ:–ሱናን አጥብቆ መያዝና ቢድዓን መራቅ(መጠንቀቅ)

③ ኡስታዝ አቡል አባስ (ናስር)
ርዕስ:– የተውሂድ አሳሳቢነትና የሽርክ አደገኝነት እንድሁም በምን ላይ ነው  አንድ የምንሆነው

④ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሙሀመድ አህመድ)
ርዕስ:–ኢልምን በመፈለግ ላይ መበርታት፣የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችን ምን መምሰል አለበት እና መልካም ስነ ምግባር

ማሳሰቢያ:–ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ‼

N·B :– የቻናልና የግሩፕ ባለቤቶች በሙሉ ሼር በማድረግ ተደራሽ አድርጉት 

አዘጋጅ፦ የጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የደዕዋና የቂርዓት ማዕከል


URGENT: - የደሴ ከተማና በዙሪያዋ ያላችሁ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ ፕሮግራሙ ዘንድ ትታደሙ ዘንድ ጥሪ አድርገንላችኋል።

ጆይን ይበሉ ቻናል

t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕ

https://t.me/yedesse_selfyochi_group


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ለወሎ መሻይኽ፣ ዱዓት እና ወጣቶች
~
ይህንን እያያችሁ እንዴት እንቅልፍ ይወስዳችኋል? ይሄ ወገን አያሳዝንም ወይ? ይሄው "ታቦታችን" እያሉ ነው። እነዚህ አካላት ከኢስላም ምን ቀራቸው? በጎጣቸው መስጂድ እያቃጠሉ፣ ሙስሊም እየ ~ ^ገደሉ ወሎ ላይ ሲደርስ "ዓለም ሲሰለጥን ወሎዬን ይመስላል" የሚሉት እንዲህ አይነቱን ደም እንባ የሚያስለቅስ የማንነት ቀውስ ለማስቀጠል ነው። እንዲህ ትኩረት ሰጥተው የሚዘግቡት ያለ ምክንያት እንዳይመስልህ። ወሎ የአፄ ዮሐንስ እና አፄ ምኒልክ አስገድዶ የማጥመቅ ዘመቻ ጥሎት ካለፈበት የማንነት ምስቅልቅል አልወጣም። እንዲወጣም አይፈለግም። ራሱም በምን ዓይነት ጫና እንዲህ አይነት ውጥንቅጥ ውስጥ እንድገባም አያውቅ።

ዱዓት እና ወጣቶች! ይህንን ወገን የማንቃት ትልቅ ኃላፊነት አለባችሁ። "ወሎ የመሻይኽ አገር"፣ "ወሎ አዝሃሩል ሐበሻ" የሚለው ራስን መደለል የትም አያደርስም። ለወገን የማይሆን ስም ቢከፍቱት ተልባ ነው፣ ጉራ ብቻ!
ከበፊቱ አንፃር ሲታይ ለውጥ እንዳለ ይገባኛል። ብዙ አካባቢ ይሄ ችግር ቀንሷል። ነገር ግን የተሻለ የሰው ኃይል ባለበት ደሴና ዙሪያዋ ላይ ይሄን ያህል አሳማሚ ነገር ማየት የመሻይኹን እና የዱዓቱን መተኛት ነው ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ወሊይ ማነው?
~
የአላህ ወሊዮች የታፈሩ የተከበሩ ሙእሚኖች ናቸው። ወሊይን መጥላት ከአላህ ጋር መጣላት ነው። ባይሆን ወሊይ ማለት ጀዝባ እና ገሪባ አይደለም። ወሊይ ማለት በምልጃ እና በተወሱል እያሳበበ ወደ ሙታን አምልኮ የሚጣራ ለሺርክ ጥብቅና የሚቆም ማለት አይደለም። ባጭሩ የተውሒድ ጠላት ሆኖ የአላህ ወሊይ መሆን አይቻልም።
ወሊይ ማለት አላህን የሚፈራ ሙእሚን ነው። አለቀ። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦
{ أَلَاۤ إِنَّ أَوۡلِیَاۤءَ ٱللَّهِ لَا خَوۡفٌ عَلَیۡهِمۡ وَلَا هُمۡ یَحۡزَنُونَ (62) ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَكَانُوا۟ یَتَّقُونَ (63) }
"ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም። (እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው።" [ዩኑስ: 62-63]

ስለዚህ በዚህ ቁርኣናዊ መልእክት መሰረት ወሊይነት ሁለት መስፈርቶች አሉት። እነሱም ኢማን እና ተቅዋ ናቸው። ይሄ ነው ቁርኣናዊው የወሊይነት መስፈርት። ኢማን እና ተቅዋ ያለው ሰው ሴት ወንዱ፣ ትልቅ ትንሹ፣ ዐረብ ዐጀሙ ሁሉም ወሊይ ነው፣ ከአላህ ዘንድ። ወሊይነት በተወሰኑ አካላት ላይ የተገደበ አይደለም። ይልቁንም "ሙእሚኖች ሁላቸውም የአርሕማን ወሊዮች ናቸው።" ይሄ የኔ ንግግር አይደለም። አጦሓዊይ በአልዐቂደቱ ጦሓዊያህ ላይ ለሰፊው ህዝብ ባቀረቡት መሰረታዊ እምነት ዝርዝር ውስጥ የሰፈረ ሐቅ ነው። እደግመዋለሁ! "ሙእሚኖች ሁላቸውም የአረሕማን ወሊዮች ናቸው!"

"የኔን ወሊይ ጠላት ያደረገ ጦርነት አውጄበታለሁ" በሚለው ሐዲሥ ስር "ወሊይ ሲባል እዚህ ላይ የተፈለገው ሙእሚን ማለት ነው" ይላሉ ነወዊይ የአርበዒን ሸርሓቸው ላይ።

ኢብኑ ከሢር ረሒመሁላህ ደግሞ ከላይ የተጠቀሰችውን የቁርኣን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፦
فكل من كان تقيا كان لله وليا
"አላህን ፈሪ የሆነ ሁሉ ለአላህ ወሊይ ሆኗል።" [ተፍሲር ኢብኒ ከሢር፡ 4/278]

አማኞች እንደ ኢማናቸውና ተቅዋቸው ልዩነት የወሊይነት ደረጃቸው ይለያያል። የነብያት እና የመልእክተኞች ወሊይነት ከተራ አማኞች ወሊይነት ጋር የሚቀራረብ አይደለም።
ወሊይነት በዘር የሚተላለፍ ንጉሳዊ ስርአት አይደለም። ይሄ የሱፊያ ሰፈር ልማድ ነው። ወሊይነት የሩቅ ሚስጥር ተናጋሪነት አይደለም። የአላህ ወሊዮች ለሸሪዐ ያደሩ ናቸው። ከሸሪዐ ያፈነገጠ ተግባር እየፈፀሙ፣ ሶላት እየተው፣ ኸምር እየጠጡ፣ ብልግና እየፈፀሙ፣ ... ከዚያ "ለምን ይሄ ይሆናል?" ሲባሉ "ወሊዮች የተራውን ህዝብ ሸሪዐ አይከተሉም። ሌላ ስውር የራሳቸው ሸሪዐ አላቸው" የሚሉ አካላት ከነ ጭራሹ ሙስሊሞች አይደሉም። ሺርክ የሚያጨማልቁ፣ ለሺርክ ጥብቅና የሚቆሙ፣ ወደ ራሳቸው ወይም ወደ ሌሎች ሙታን አምልኮ የሚጣሩ፣ የሩቅ እውቀትን የሚሞግቱ አካላት የሸይ ^ጧን እንጂ የአላህ ወሊዮች አይደሉም። "ሶላት ስገዱ" ሲባሉ "ዐርሽ ላይ ነው የምሰግደው" "መካ ሐረም በርሬ ሄጄ ነው የምሰግደው" የሚሉ የዲን ሽፍታዎች ማጅራት መቺዎች እንጂ የአላህ ወሊዮች አይደሉም። ከሶላት ብቻ ሳይሆን ከጦሀራም የራቁ፣ በጤና እክል ምክንያት ወሬ የሚቀላቅሉ መጅዙቦች ደግሞ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ወፈፌዎች እንጂ ወሊዮች አይደሉም።

ሌላው ወሳኝ ነጥብ ወሊይ አይመለክም የሚለው ነው። ለጭንቅ ለችግር ሊማፀኑት የሚገባው አንድ አላህ ብቻ ነው። ወሊይ ዝናብ፣ ልጅ፣ ሲሳይ መስጠት አይችልም። ሰዎችን ከመከራ የሚያወጣውም አላህ እንጂ ደካማ ፍጡሮች አይደሉም። አላህ እንዲህ ይላል፦

{وَٱلَّذِینَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا یَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِیرٍ (13) إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا یَسۡمَعُوا۟ دُعَاۤءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُوا۟ مَا ٱسۡتَجَابُوا۟ لَكُمۡۖ وَیَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ یَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا یُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِیرࣲ (14)}
{እነዚያም ከርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ (ስሷ) ሽፋን እንኳን የላቸውም። ብትጠሯቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም። ቢሰሙም አይመልሱላችሁም። በትንሳኤ ቀንም እነሱን ከአላህ ጋር ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ-አዋቂው ማንም አይነግርህም።} [ፋጢር፡ 13-14]

ዛሬ ለጭንቅ ለችግር ይደርሱልኛል ብሎ ወሊዮችን የሚማፀን ሰው ነገ በቂያማ ቀን ጠላቶቹ ነው የሚሆኑበት። ከራሴ አይደለም የማወራው። ምስክሬ ቁርኣን ነው፦
{وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن یَدۡعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا یَسۡتَجِیبُ لَهُۥۤ إِلَىٰ یَوۡمِ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَاۤىِٕهِمۡ غَـٰفِلُونَ (5) وَإِذَا حُشِرَ ٱلنَّاسُ كَانُوا۟ لَهُمۡ أَعۡدَاۤءࣰ وَكَانُوا۟ بِعِبَادَتِهِمۡ كَـٰفِرِینَ (6) وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَیۡهِمۡ ءَایَـٰتُنَا بَیِّنَـٰتࣲ قَالَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَاۤءَهُمۡ هَـٰذَا سِحۡرࣱ مُّبِینٌ (7)}
{እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ለሱ የማይመልስለትን ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ይበልጥ የጠመመው ማነው? እነሱም (ተጠሪዎቹ) ከጥሪያቸው የዘነጉ ሆነው ሳለ?! ሰዎች (ቂያማ) በተሰበሰቡ ጊዜም ለነሱ ጠላቶች ይሆናሉ። መመለካቸውንም የሚክዱ ይሆናሉ።} [አሕቃፍ፡ 5-6]

ዱዓእ ዒባዳ እንደሆነ ልንዘነጋ አይገባም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
"الدُّعَاءُ هُوَ الْعِبَادَةُ، قَالَ رَبُّكُمُ : {ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}"
"ተማፅኖ አምልኮት ነው። ጌታችሁ፡ {ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና} ብሏል።" [አቡ ዳውድ፡ 1479]

ተዘቅዝቆ የምታዩት የሱ ..ፊያ ወሊይ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የትግል አሊፍ ባ ታ
~
ሃገራችን ጥላቻ ህሊናቸውን ባወ -^ራቸው ሰዎች የተሞላች ናት። አንዳንድ አካላት ሃገሪቱ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ስላልተመቻቸው እንጂ ዛሬ ከምናየው በላይ ብዙ ግፎችን ያሳዩን ነበር። በነገራችን ላይ በአንዳንድ የትምህርት ተቋማት እየተከሰቱ ያሉት አድሎዎችና በደሎች የተቋማቱ የተናጠል እርምጃ እንዳይመስሉን። በሰፊው እየመጣ ላለው "ህግን" የተንተራሰ መዋቅራዊ በደል መንደርደሪያ ናቸው። እና የባሰ እንጂ የተሻለ እንዳትጠብቁ። ቀድሜ የማውቀው አሁንም የሰማሁት ፍንጭ ስላለኝ ነው ይህንን የምለው። አገሪቱን እግር ከወርች ጠፍሮ ከያዛት ብዙ አይነት መዓት በላይ የሙስሊም ሴቶች አለባበስ እንቅልፍ የሚነሳቸው አካላት አሉ። ስለዚህ ለባሰው ራስን ማዘጋጀት ጥሩ ነው። አንድ ቀን ድንገት ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና ልንሰማ እንችላለን። የፈለገ ቢደርስ ፈፅሞ ተስፋ መቁረጥ አይገባም። አንዳንድ ትግሎች ለውጥ ለማግኘት ብዙ ድካም ይጠይቃሉ። እጅ ሳይሰጡ በስሜት ሳይሆን በስክነትና በስሌት መጓዝ ይገባል። ትልቁ ሽንፈት ጭቆናን 'ኖርማል' አድርጎ መቀበል ነው።
አሁንም እላለሁ። ዝምታህ ያስጨንቅ ዘንድ፣ ተቃውሞህ ያስፈራ ዘንድ፣ ንግግርህ ክብደት ይኖረው ዘንድ፡
* አንድ፡ አጥብቀህ ዲንህን ተማር አስተምር። እምነቱን የተረዳ ሰው ለበደል እጅ አይሰጥም።
* ሁለት፡ አካደሚ ትምህርት ተማር። የዘመኑን ጭቆና ያለ አካደሚ ትምህርት መጋፈጥ ከባድ ነው።
* ሶስት፡ አድምተህ ተባብረህ ስራ። የፈረጠመ የኢኮኖሚ አቅም ጠንካራ የትግል መሰረት ነው።
* አራት፡ በየዘርፍህ ተደራጅ። ያልተደራጀ ህዝብ አቅሙንም አያውቅም። አቅምም አይኖረውም።
* አምስት፡ ሳትሰለች ጩህ። ጩኸትህ በደልህ እንዳይረሳ ያደርጋል። ተተኪ ትውልድ ላይ እልህ እንዲሻገር ያደርጋል። ዝምታ በደልን 'ኖርማል' ያደርጋል።
* ከምንም በላይ በጌታህ ላይ ተመካ። ልፋት ዋጋ የሚኖረው፣ ጥረት ፍሬ የሚያፈራው የአላህ እገዛ ሲኖር ነው።
አሁን ያለንበት ማንቀላፋት ደስ አይልም። በጣም እንቅልፍ በዝቷል። ይሄ ደግሞ መንናቅን ነው የሚያስከትለው። የተናቀ መንደር ባ'ህያ ይወረራል። የተናቀ ህዝብ እዚህ ግባ በማይባሉ አካላት ልጆቹ በገዛ ሃገራቸው ሲበደሉ እጁን አጣጥፎ ይመለከታል።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከደዕዋ ርእስ ጋር በተያያዘ
~
1 - የደዕዋ ርእስ ለመወሰን አዘጋጆች በራሳቸው ከሚጨርሱት ከተጋባዦቹ ጋር ቢነጋገሩበት መልካም ነው።
2 - በተቻለ መጠን ርእሶች ሰፊው ህዝብ ላይ ያነጣጠሩ ሊሆኑ ይገባል።
3 - ማስታወቂያ ላይ ርእስን ከማስተዋወቅ ይልቅ መተው ይሻላል። ታዳሚው ህዝብ ቀጥታ ቦታው ላይ ሲደርስ ቢያውቀው ነው የሚመረጠው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ
=
1- ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ (الطلاق المعلق) ማለት ለምሳሌ ሚስቱ ከሆነች ጓደኛዋ ዘንድ መሄዷ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ተረዳ። "አትሂጂ" ቢላት ልትቆም ፈቃደኛ አልሆነችም። በዚህን ጊዜ "ዳግመኛ እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" በማለት ተናገረ። ይህንን ካለ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ወርዶ ፍቺው ይቆጠራልን?
=> ይህንን ሸርጥ የተናገረው ብትሄድ የእውነትም ሊፈታት ከሆነ በመሄዷ ኒካሑ ይወርዳል። ፍቺ ተፈፅሟል።
=> ሸርጡን ያስቀመጠው መፍታትን አስቦ ሳይሆን ለማስፈራራት ከሆነ ኒካሑ አይወርድም።

2- ያስቀመጠው ቅድመ-ሁኔታ ቀድሞ በተፈፀመ ጉዳይ ላይ ይሰራልን? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀመጠ። ይህን ከማለቱ በፊት ቀድማ ሄዳ ከሆነ ፍቺው ይቆጠራልን?

=> ቅድመ ሁኔታውን ሲያስቀምጥ ሃሳቡ ቀድማ ሄዳም ከሆነ "ፈትቻለሁ" የሚል እሳቤን የሚያጠቃልል ከሆነ ፍቺው ይቆጠራል። ከዚህ በኋላ ቢከሰት የሚለውን ብቻ ነይቶ ካወራ ግን በቀደመ ተግባር ፍቺ አይታሰብም።

3- "ይህንን ካደረግሽ ፍቺ ነሽ" ቢልና አውቃ ሳይሆን ረስታው ያንን ነገር ብትፈፅም ኒካሑ ይወርዳልን?
=>አይወርድም።

4- ካስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መመለስ ይችላል? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀምጦ ነበር። ያስቀመጠውን ሸርጥ አንስቶ ቢፈቅድላትና ከዚያ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ይወርዳል?
=>ትክክለኛው አቋም አይወርድም የሚለው ነው።

5- ሚስቱን በሆነ ሰበብ ከፈታ በኋላ ሰበቡ ልክ እንዳልሆነ ካወቀስ? ለምሳሌ፦ ሚስቱ በሆነ ጉዳይ ላይ እንደዋሸችው ወይም ከቤቱ ወንድ እንዳስገባች ተረድቶ ፈታ። ሲያጣራ ግን ጉዳዩ እሱ እንዳሰበው እንዳልሆነ አወቀ። ኒካሑ ይወርዳል ወይ?
=>ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑ ባዝ እና ኢብኑ ዑሠይሚን ኒካሑ አይወርድም ብለዋል።
=
ከሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ፈትሑል ዐላም ኪታብ (8/543 - 554) ተጨምቆ የቀረበ።
ማሳሰቢያ:- መልእክቱ እንዲህ አይነት ጉዳይ ከገጠመ ሑክሙ ምን እንደሆነ ለማስታወስ የቀረበ እንጂ የኒካሕ እና የፍቺ ጉዳይ በሃላፊነት ሊያዝ ተገቢው ክብደት ሊስሰጠው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: "ኡማ ቲቪ " Tv
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው ኒቃቢስት መምህራንንም በኒቃብ መግባት እና ማስተማርን ከለከለ!

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአመታት እስልምናዋ የሚያዛትን ኒቃብ ለብሳ ስታስተምር የነበረች ሌክቸር ከትላንት ጀምሮ "ወይ ስራሽን ወይ ኒቃብሽን ምረጪ?" የሚል ትዕዛዝ እንደተላለፈላት ተገልፇል:: "ስራዬንም እምነቴንም ይዤ እቀጥላለሁ!" የሚል መልስ ብትሰጥም ለመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እና ክልከላ በዛሬው እለት ጠርተዋታል::

በተማሪዎቹ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ አይበቃው ያለው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ወደ እስታፍ ሰራተኞችም ተሸጋገረ:: ይህ ግልፅ የሆነ ሙስሊም ጠልነት ነው:: አዳጊ ወጣቶችን ከግቢ ውጭ ያለምግብ ያለትምህርት ያለማደሪያ የሚያሳድረው ተቋም የሀገሪቱን እናቶችንም በእምነት እየለዬ ማስለቀሱን ጀመረ::

ይህ አውሬያዊ ጭካኔ የተሞላበት ግፍ ነው!

ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም መምህራን!
ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ማህበረሰብ!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች!

Показано 20 последних публикаций.