ኦርቶዶክስ ተዋህዶ️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ይህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርቶች መዝሙራት ቅዱሳት ሥዕላትን እንዲሁም ሌሎችን ምናጋራበት መንፈሳዊ ቻናል ነው።
👉"የአባቶቼን ርስት አልሰጥም"👈
ለማንኛውም አስተያየት @jermi123
ይጠቀሙ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


✝️እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk


🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️✟

         


. ✧ †††ዝክረ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ ††† ✧

" የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት እልቂት "

††† በ፲፱፻፳፱ [1929] ዓ/ም: የካቲት ፲፪[12] ቀን ከ፴፼[30,000] በላይ ኢትዮጵያውያን አባቶች: እናቶች: ወጣቶችና ሕፃናት በሮማዊው የፋሽስት ጦር ስለ ርትዕቷ ተዋሕዶ ሃይማኖት፡ ስለ ሀገራቸዉ ፍቅር ደማቸው እንደ ጐርፍ ፈሰሰ ...

ደብረ ሊባኖስ ገዳም ብቻ የገዳሙ መነኮሳት ከየካቲት ፲፪[12] ጥቃት ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት በሚል በ ግራዚያኒ ትእዛዝ በ ማሌቲ አስፈጻሚነት ከ ፳፻፪፻[2200] በላይ ዲያቆናትና መነኮሳት በግፍ ተፈጅተዋል ።

††† ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም በቅዱስ ዳዊት መዝሙር እንዲህ ታስባቸዋለች ፦

"አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ::
የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ::
ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት::
የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች አደረጉ::
የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት::
ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ::
የሚቀብራቸውም አጡ::"
(መዝ. ፸፰[78]:፩[1])

(በምስሉ ላይ እምናያቸው የደብረ ሊባኖስ መነኮሳትና ዲያቆናት... ናቸው ፤ ወደ ሚረሸኑበት ቦታ ሊሄዱ በመጨረሻዋ ሰአት እንዲነሱ የተደረገው ፎቶ ነው።)


ቅዱስ ያሬድ

< ሊቃውንትን (ሊቀ ሊቃውንት) እያልን የምንጠራቸው ቅዱስ ያሬድ ከደረሳቸው ድርሰቶችና ዜማዎች መካከል የተወሰነውን ክፍል አውቀው ነው ። >

ታድያ መምህራን የያሬድን ክፋይ እውቀት አውቀው ሊቀ ሊቃውንት ተብለው ከተጠሩ ቅዱስ ያሬድን በምን አይነት ስም እንጥራው ?


ሰላም ለአብራኪከ
ከጌታ ፡ ክርስቶስ ፡ ፊት ፡ ለሰገዱ ፡ ጉልበቶችህ ፡ ሰላምታ ፡ ይገባቸዋል ፡ ቅዱስ ፡ ወንጌልን ፡ የምትሰብክ ፡ ቄስ ፡ ያሬድ፡  በዕዝል ፡ ዜማ ፡ አማን ፡ በአማን ፡ እያልክ ፡ ቤተ ፡ ክርስትያንን ፡ ቀደስኻት።


ምክር ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የምንወደው ጓደኛችን ቢሞትብን ለቀናት ሐዘን እንቀመጣለን። ብር ቢጠፋብንም እንዲሁም እንቆጫለን። ዕለት ዕለት ሐጢአት ስንሠራ ግን ጥቂትስ እንኳ አናስብም ። መቼ ይሆን የምንነቃው?

ልብስ የተሰጠን ከብርሃናዊ ልብሳችን ስለተራቆትን ነው /ዘፍ. 3፥20/። ታድያ በኃጢአታችን ምክንያት በተሰጠን ልብስ ልባችንን ከፍ ከፍ የምናደርገው ስለምንድ ነው?

ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከእኛ መካከል የሚኖርበትን ቤት በቆሸሸ ቁጥር የማያጸዳው ማነው? ታድያ የእግዚአብሔር ማደርያ የኾነው ሰውነታችንን በንስሐ መወልወያ የምናጸዳው መቼ ነው?

ልጆቼ ንስሐ ግቡ እንጂ በኃጢአታችሁ ምክንያት በፍጹም ተስፋ አንዳትቆርጡ። ወዳጄ ሆይ! ማፈር የሚገባህ ኃጢአት ስትሰራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አይደለም። ኃጢአት ሕመም ነው። ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው። ከኃጢአት ቀጥሎ ህፍረት አለ ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ። ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን።
  


➥"ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ልደታቸው ነው "
- እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን -


”ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት የሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ ተዋደዱ” 
1ኛ ጴጥ. 1÷22


#አስተርዮ ማርያም

የማይታየው የታየበት፣ የራቀው የቀረበበት፣ የረቀቀው መለኮት በገዘፈ ሥጋ ማርያም የተገለጠበት፣ የወልድ ልጅነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ የተመሰከረበት፣ በልደቱ፣ በጥምቀቱ አንድነት በሦስትነት እንዲሁም መለኮት በሥጋ ሥጋም በመለኮት በተዋሕዶ ተገልጦ ምሥጢሩ ገሃድ የሆነበት የመገለጥ የመታየት ጊዜ የሆነው ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ  ዘመነ አስተርዮ እየተባለ ይጠራል፡፡
በዚሁ በዘመነ አስተርዮ መካከል የሚገኝ ስለሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “በዓለ ዕረፍት አስተርዮ ማርያም” እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ አስተርዮ ማርያም የምንለው ታላቅ በዓል እናታችን እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችበት መታሰቢያ ሲሆን ቀኑም ጥር ፳፩ ነው፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን የወሰነች፣ ሞትን በሞቱ የመሻር ሥልጣን ያለውን፣ ዓለምን በመዳፉ የጨበጠውን የወለደች ክብርት ቅድስት እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም የምታርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ይኸውም ጥር ፳፩ ቀን በዕለተ እሑድ በ፷፬ ዓመቷ፣ በ፵፱ ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ነግሯት በልጇ መቃብር ሆና ጸሎት ታድርስ ነበር፡፡ እንዲህም ብላ ጸለየች፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሐዋርያትን ሁሉንም፣ ነፍሳቸውንም የለየሃቸውን አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋንና የሙታን አምላክ ነህና›› አለች፡፡ (የጥር ፳፩ ስንክሳር)
በዚህ ጊዜ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ከኤፌሶን አመጣችው፤ ምስጋናም አቀረበላት፤ ሁሉም ሐዋርያት የሞቱትም ከመቃብር ተነሥተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ እንዲህም ስትል ጠየቀቻቸው፤ ‹‹ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፤ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ሰማችሁ?›› አለቻቸው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ‹‹ወደ አንቺ እንድንመጣ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፤ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወደ አንቺ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አላት፡፡ በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደ እርሷ መጣ፡፡ (ጥር ፳፩ ስንክሳር)
እንዲህም አላት ‹‹እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጥቻለሁ›› አላት፡፡ እርሷ ግን ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜህ፤ በድንግልና ወልጀህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ አሳያትና ‹‹እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ሁሉ ነፍሳት መዳን ምክንያት (ቤዛ) ይሆናቸዋል›› አላት፡፡ ‹‹እነዚህን ሁሉ ከማርክልኝስ ይሁን››  አለች፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥጋዋን ከክብርት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በይባቤ መላእክት በክብር ነፍሷን ዐሳረጋት፡፡ (መዝገበ ታሪክ ቁጥር አንድ ገጽ ፻፶፭፣ ጥር ፳፩ ስንክሳር)
የእመቤታችን አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!

ምንጭ 👉 ማኅበረ ቅዱሳን


አስተርዮ ማርያም ።
https://t.me/enabib


ብርብር ማርያምን የማያውቅ ኦርቶዶክስ የአንድ ብሔር ይመስለዋል
***

የኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ባለቤቷ ማን ነው ከተባለ በአንድ ቃል ....ኢየሱስ ከሚል ስም ላይ ይወድቃል።

ባህሪዋም ቅድስት እና ኩላዊት ሲሆን ብዛቷም አንድ ነው።

ጠላት ግን ሲከሳት የነፍጠኛ ሃይማኖት፣የገዢ መደብ ቤት ብሎ ባልዋለችበት ስሟን ይጠራሉ።

ባሻዬ ....

በእርግጠኝነት ብርብር ማርያም የሚባል ገዳምን ብታውቅ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከየትኛውም ብሔር ትከሻ ተንጠልጥላ እንዳልመጣች ትረዳለህ።

ደቡብ በሚባለው ስፍራ ህዝብ እንዲህ ሳይሰፍር ብርብር በምትባል ስፍራ ላይ ንጉስ ቆስጢንጢኖስ አርዮስን በኒቂያ ጉባኤ ይወገዝ ዘንድ ጉባኤ አበው ከዘረጋ ከ3 ዓመት በኃላ በ328 ዓ.ም 

ወደእዚህች ስፍራ ታቦተ ገብርኤል እና ታቦተ ማርያምን ይዞ በመምጣት ለ1100 ዓመት በስፍራው ተሰርቶ የነበረውን መሰዋተ ኦሪት ለውጦ ወደ ህገ ወንጌል ቀይሯል።

በእዚህ ስፍራ የነበሩት ቀደምት የጋሞ ህዝቦች ከእግዚአብሔር ጋር የተዋወቁት ክርስቶስ በቤቴልሔም ከመወለዱ ከ800 ዓመታት በፊት በካህኑ ሳዶቅ ልጅ አዛርያስ በኩል እንደሆነ ብነግርህስ?

አንተ ከምትከሳቸው ነገስታት የሥነ ህዝብ ስርዓት በፊት ብርብር በሚባል ማማ ላይ ከህገ ኦሪት እስከ ህገ ወንጌል ተዘርግቶ በአዲስ ኪዳን ዘመን ኦርቶዶክስ የምትባል የእምነት አስተሳሰብ የያዘች መቅደስ በእዚህ ከፍታማ ስፋራ ላይ ነበረች።

የዛሬን አያድርገው እና ይህቺ ስፍራ የእውቀት ፣የምስጋና እና የሊቃውንት መፍለቂያ እንደሆነች አባ ባሕርይ የተባሉ መኖክሴ አማናዊ ምስክር ናቸው።

የቅድስት ቤተክርስትያን የጸሎት እና የታሪክ መጽሐፍ ብርብር ከሚባል ማማ ላይ እንደሚገኝ መዝሙረ ክርስቶስን ብታገላብጥ ታውቅ ነበር።

ስለዚህ ባሻዬ.... ለኦርቶዶክስ ገዢ ፈላጭ እና ፈጣሪ አካል ስትሰጣት "ኢየሱስ" ከሚለው ስም ውጪ ዕጣ አትጣልባት።

ለኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ብሔርም ይመደብ ዘንድ ከተገባ ብሔሯ ሰማያዊት እንደሆነች ከእኛ ከልጆቿ አንደበት ሰምተህ አስተጋባ።

@ጥንታዊት ጽዮን ሰማያዊት ብርብር ማርያም 2015 ዓ.ም

እግዚአብሔር ይመስገን!!!
https://t.me/enabib


2.ቅዱሱ መልአክ እመ ብርሃንን በስደቷ ጊዜ ወደ ኢትዮዽያ መርቶ አምጥቷታል:: በክንፉ ተሸክሞ: በ4 አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጉዋል::

3.ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጐ በኢትዮዽያ ወንዞች ላይ አፍስሷል::

4.ለብዙ ቅዱሳን (አባ ጊዮርጊስን ጨምሮ) ጽዋዐ ልቡናን አጠጥቷል::

አምላከ ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ በጐ ምኞታችንን ይፈጽምልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

††† ጥር 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ እንጦንስ (የመነኮሳት አባት - የበርሐው ኮከብ /ልደቱና ዕረፍቱ)
2.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላዕክት (ለተጠሙ ጽዋዓ ልቡናን የሚያጠጣ: ምሥጢር ገላጭ መልዐክ)
3.ቅዱስ ሚናስ ኤዺስ ቆዾስ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ ደቅስዮስ ኤዺስ ቆዾስ
3.አባ ዻውሊ የዋህ

††† "እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል::"
(ማቴ. 16:24) †††

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††


††† እንኳን ለታላቁ ኮከበ ገዳም አባ እንጦንስ እና ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ እንጦንስ †††

††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::

ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::

እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

አባ እንጦንስ የመነኮሳት ሁሉ አባታቸው: ለገዳማውያን ሁሉም ሞገሳቸው ናቸው:: እንዲያውም ብዙ ጊዜ "ኮከበ ገዳም: ማኅቶተ ገድል (የበርሃው ኮከብ: የተጋድሎ መብራት)" ተብለውም ይጠራሉ::

ቤተ ክርስቲያን ለጀማሪዎች ትልቅ ትኩረት ትሰጣለች:: ለምሳሌ:- አባ ዻውሊን (የካቲት 2 የሚከበሩ) ለብሕትውና መሠረትን ስለ ጣሉ "አበ ባሕታውያን" ብላ ታከብራለች:: አባ እንጦንስን ደግሞ "አበ መነኮሳት (የመነኮሳት አባት): ቀዳሚሆሙ ለመነኮሳት (ለመነኮሳት ቀዳሚና ጀማሪ) ስትል ትጠራቸዋለች::

አባ እንጦንስ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚነሱ ቅዱሳን መነኮሳት ሁሉ መንገድን ይጠርጉ ዘንድ ብዙ መከራን በትዕግስትና በአኮቴት ተቀብለዋል:: ላለፉት 1,700 ዓመታት እንደ ሻማ እየቀለጡ ያበሩ አበው ቅዱሳን ሁሉ የአባ እንጦንስ ልጆች ናቸው::

ከምጥ የከፋ የዲያብሎስ ፈተናን ተቀብለው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ቅዱሳኑን ወልደዋል:: የመነኮሳት አለቃ የሆኑትን ታላቁን መቃርዮስን ጨምሮ በርካቶችን አመንኩሰው ለቅድስና አብቅተዋል::

አባ እንጦንስ ግብጻዊ ሲሆኑ የተወለዱት አቅማን በምትባል ቦታ አካባቢ ነው:: ጊዜውም በ252 ዓ/ም ነው:: የተባረኩ ወላጆች ለቅዱሱ እንጦንስና አስከትለው ለወለዷት ሴት ልጃቸው : አስቀድመው ፍቅረ ክርስቶስን: አስከትለውም ሃብት ንብረታቸውን አውርሰው ዐርፈዋል::

በዚህ ጊዜ የአባ እንጦንስ እድሜ አፍላ ወጣትነት ላይ ነበር:: በልጅነት ጊዜአቸውም አባ እንጦንስን ሲስቁ: ሲጫወቱ: አልያም ሲቀልዱ አየሁ የሚል ሰው አልነበረም:: ፍጹም ቁም ነገረኛና ታዛዥ: በዚያ ላይም አስተዋይ ነበሩና ሙሉ ጊዜአቸውንም ከቅዱስ ቃሉ በመመገብ: በትምሕርትና በማስቀደስ ያሳልፉ ነበር::

ዘወትርም ዜና ሐዋርያትን እያነበቡ በመንፈሳዊ ቅናት ይቃጠሉ ነበር:: በጊዜው የምናኔ ሕይወት ጐልቶ ባለ መገለጡ አባ እንጦንስ የሚያደርጉት ይጨንቃቸው ነበር:: ሲጸልዩም "አበው ሐዋርያት ይሕንን ክፉ ዓለም ንቃችሁ ጌታችሁን የተከተላችሁበት ጥበብ እንደ ምን ያለ ነው!" እያሉ ይደነቁ ነበር:: መሻታቸውን ያወቀ ጌታም ምሥጢርን ገለጠላቸው::

አንድ ቀን በቅዳሴ ላይ ወንጌል ሲነበብ ካህኑ ስለ ምናኔ የሚጠቅሰውን ክፍል አነበበ:: ለአንድ ባለ ጠጋ ሕግጋትን ከነገረው በሁዋላ "ፍጹም ልትሆን ከወደድክስ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ተከተለኝ" (ማር. 10:17) የሚለውን ጥቅስ ሲሰሙ ተገርመው "ጌታ ሆይ! ይህንን የተናገርኸው ለእኔ ነው" ሲሉ አሰቡ:: በቀጥታም ሃብታቸውን ለአካባቢው ሰው አካፍለው: እህታቸውን ከደናግል ማሕበር ደምረው እርሳቸው ወደ ዱር ሔዱ::

ከዚህች ቀን ጀምረው አባ እንጦንስ ከ80 እስከ መቶ ለሚገመቱ ዓመታት ከአጋንንት ጋር በጦርነት ነበር የኖሩት:: በንጹሕ አምልኮታቸውና በቅድስናቸው የቀና ጠላት ሰይጣን በብዙ ጐዳና ፈተናቸው:: አቅም ቢያጥረው አራዊትን መስሎ ታገላቸው::

በዚህ አልሳካ ቢለው የእሳት ሰንሰለትን አምጥቶ ገረፋቸው:: በሞትና በሕይወት መካከል ጥሏቸው ሔደ:: ወድቀው ያገኟቸው ሰዎች ለዘመዶቻቸው ሰጥተዋቸው አገገሙ:: ልክ ሲነቁ ግን ፈጥነው ወደ በርሃ ተመለሱ::

ሰይጣን በርሃው የቅዱሳን ማደሪያ እንዳይሆን ሰግቷልና ጨክኖ ታገላቸው:: ግን አልቻላቸውምና ተረታ:: አምላከ ኃያላን ክርስቶስ ከቅዱሱ ጋር ነበርና:: ከዚህ በሁዋላ ግን ጸጋው በዝቶላቸው ድውያንን የሚፈውሱና ሰይጣን የማይቀርባቸው ሰው ሆኑ::

በረዥም ዘመነ ቅድስናቸውም:-
1.ብዙ አርድእትን ከመላው ዓለም ሰብስበው: አስተምረው: ምናኔን ከግብጽ ማዶ በመላው ዓለም አስፋፉ::
2.በደመና እየተጫኑ ብዙ አሕጉራትንም እየዞሩ ሰበኩ:: በዚህም አሕዛብን ወደ እምነት: ኃጥአንን ወደ ንስሃ መለሱ::
3.ጊዜው ዘመነ ሰማዕታት ነበርና ወደ አደባባይ ሒደው ከሃዲዎችን ገሠጹ:: ማንም ደፍሮ ግን አልገደላቸውም::

እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን እየሠሩ በቅዱስ ሚካኤል እጅ መነኮሱ:: እርሳቸውም ብዙዎችን አመነኮሱ:: አርጅተው እንኩዋ ከተጋድሎ ያላረፉት አባታችን የጣመ ነገር ቀምሰው: ገላቸውን ታጥበው አያውቁም:: በ372 ዓ/ም በዚህች ቀን ሲያርፉም ዕድሜአቸው 120 ደርሶ ነበር::

የአባ እንጦንስን በዓል ለማክበር የምትሹ ቤተ ክርስቲያናቸው ጎንደር ከተማ ከቀሃ ኢየሱስ በላይ ይገኛል::

††† ለአባታችን እንጦንዮስ /እንጦንስ/ እንጦኒ ክብር ይገባል!

††† ቅዱስ ዑራኤል †††

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል:-
1.ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጉዋታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም ተሸክሞ: አስቅድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ: የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች::


"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
    ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:-  የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ  ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉  https://t.me/enabib


🕊እንኳን አደረሳችኹ ወርኃ ጥርን በሰላም ያስፈጽመን የንስሐ ልብ ይሰጠን::

🕊"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

💥ስለ ንስሐ💥

✝ከቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንማራቸው 7 ነገሮች።

፩, 🌿ቅዱስ አብርሃምን መምሰል( ፈጣሪውን ተመራምሮ አገኘ)::

፪,  🌿ዓለምንና የዓለምን ነገሮች መተው።

፫, 🌿የንስሐ ሕይወት( ንስሐን በትጋት መፈጸም)።

፬, 🌿መታዘዝ (የሚታዘዘውን ሳያጓድል መስራትን)።

፭, 🌿ለሌሎች መኖርን።

፮, 🌿በሰው አለመፍረድን።

፯, 🌿ትሕትናን።
        
1,💥ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡

2,💥ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡

3, 💥በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡

4,💥የበጎ ለውጥ እናት ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ ናቸው

4 ነገሮችን በደንብ ልብ እንበል!
    1, ✨አላማ

    2 ,✨እምነት

    3,✨ጥረት

    4 ✨ጥንቃቄ

9ኙ የቅድስና መንገዶች

፩💥ሃይማኖት
፪💥ጾም
፫💥ጸሎት
፬💥ስግደት
፭💥ምጽዋት
፮💥ፍቅር
፯💥ትህትና
፰💥ትዕግስት
፱💥የዋህነት

✨እነዚኽን ያዟቸው ተጠቀሙባቸው

🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤
እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።

✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት
🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)

ለ ፳፻፲፯ የቤት ሥራ የሚሆኑ ፭ መልእክቶች

፩.ለጸሎት ተነሱ
፪.ክርስትናን መኖርን እንጀምር
፫.የእውነት ንስሐ ያስፈልገናል
፬.ካቆሸሸን ማኅበራዊ ሚዲያ ጥቂት እንራቅ
፭.ትልቁ መከራ እንዳያገኘንhttps://t.me/enabib


††† ቅድስት ኢላርያ †††

††† "ኢላርያ" ማለት "ፍሥሕት (ደስ የተሰኘች)" እንደ ማለት ነው:: ከተባረኩ ቅዱሳት አንስት ትልቁን ሥፍራ ትይዛለች:: ማን እንደ እርሷ!

ቅድስት ኢላርያ ማለት:-
*የታላቁ ንጉሠ ነገሠት: የደጉ ዘይኑን (Emperor Zenon) የበክር ልጅ
*በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደች
*ትምሕርተ ሃይማኖትን: ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የተማረች
*ምድራዊ ንግሥናን ንቃ ፍቅረ ክርስቶስን የመረጠች
*የአባቷን ቤተ መንግስት ትታ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ (ገዳመ አስቄጥስ) የወረደች:
*ስሟን ከኢላርያ ወደ ኢላርዮን ቀይራ በወንዶች ገዳም የመነኮሰች
*ራሷን በፍጹም ገድል ቀጥቅጣ ከወንዶቹ በላይ በሞገስ ከፍ ከፍ ያለች
*ትንሽ እህቷን ጨምሮ በርካቶችን የፈወሰች
*በእርሷ ምክንያት ለግብጽና በመላው ዓለም ለሚገኙ ገዳማት ብዙ ቸርነት በዘይኑን የተደረገላት ታላቅ እናት ናት::

ቅድስት ኢላርያ ማንም ሴት መሆኗን ሳያውቅባት: አባ ኢላርዮን እንደ ተባለች በዚህች ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስቲያንም እነሆ ላለፉት 1,400 ዓመታት: ቅድስቲቱንና የተባረከ አባቷን ዘይኑንን: ስለ በጐነታቸውና ውለታቸው ታስባቸዋለች::

††† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: †††

††† ጥር 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት
1.በዓለ አስተርዕዮ ማርያም (እመቤታችን ከእረፍቱዋ በሁዋላ ለደቀ መዛሙርት በዚሁ ቀን ተገልጣ ነበር)
2.ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ (ታላቅ ሊቅና ጻድቅ)
3.ቅድስት ኢላርያ እናታችን (የዘይኑን ንጉሥ ልጅ)
4.ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ሰማዕት
7.አባ ፊቅጦር

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ምዕመነ ድንግል
2.አባ አምደ ሥላሴ
3.አባ አሮን ሶርያዊ
4.አባ መርትያኖስ
5.አበው ጎርጎርዮሳት

††† "ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን::
እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን::
አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ::
አንተና የመቅደስህ ታቦት::
ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ::
ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው::
ስለ ባሪያህ ስለ ዳዊት. . ."
(መዝ. 131:7)

††† "ወዳጄ ሆይ! ተነሺ::
ውበቴ ሆይ! ነዪ::
በዓለት: በንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ!
ቃልሽ መልካም: ውበትሽም ያማረ ነውና:
መልክሽን አሳዪኝ::
ድምጽሽንም አሰሚኝ::"
(መኃ. 2:13)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††


✝†✝ እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✝†✝

†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†

†✝† ዕረፍተ ድንግል †✝†

†✝† እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::

*ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500 ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::

*ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::

††† የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ
*ከአዳም በሴት
*ከያሬድ በሔኖክ
*ከኖኅ በሴም
*ከአብርሃም በይስሐቅ
*ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
*ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::

*ከሌዊ ደግሞ በአሮን: አልዓዛር: ፊንሐስ: ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::

*አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7) "ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ)

ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12 ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::

*በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: (ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ)

*ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14) "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ2 ዓመታት ቆዩ::

*አርዌ ሔሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም: በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር ሲሆነው: ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::

*በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች:: እርሷ 45 ዓመት ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3 ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::

*የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች:: ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::

*ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች:: በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ: ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና: ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::

*ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ: ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ::
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ::" እንዲል::

*ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ::
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ::
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::

*በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ: እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል:: በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት ቆይታለች::

*ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል::

*በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ::

*ለ2 ሳምንታት ቆይተው: ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል::

††† ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን: ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: †††

††† ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሊቅ †††

††† ለዚህ ቅዱስ አባት ብጹዕ መባል ተገብቷል:: ክቡር: ምስጉን: ንዑድ ሰው ነውና:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቂሣርያ ቀዸዶቅያ የተወለደው ቅዱሱ ሰው ለደሴተ ኑሲስ ብርሃኗ ነው:: አባቱ ኤስድሮስ: እናቱ ኤሚሊያ: ወንድሞቹ ቅዱሳን "ባስልዮስ: ዼጥሮስ: መክርዮስና መካርዮስ" ይባላሉ::

የተቀደሰች እህቱም ማቅሪና ትባላለች:: ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ለቅድስና ያልበቃ አንድም ሰው የለም:: ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከማር በጣፈጠ ዜና ሕይወቱ እንደ ተጻፈው:-
*በልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል::
*ሥጋውያን ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድም የግሪክን ፍልሥፍና በልኩ ተምሯል::
*በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል::
*በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል::
*ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል::
*እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች 11 ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር 11 ብቻ ነበር::
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል::
*ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን (በ381 ዓ/ም) መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል::

ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ33 ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::


“ማግባት ለሚሹ”
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

አባቶች ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

እናቶች ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡

እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

እናንተ ልጃገረዶች ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡


🕊እንኳን አደረሳችኹ ወርኃ ጥርን በሰላም ያስፈጽመን የንስሐ ልብ ይሰጠን::

🕊"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"    /ማቴ ፫:፫/

💥ስለ ንስሐ💥

✝ከቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንማራቸው 7 ነገሮች።

፩, 🌿ቅዱስ አብርሃምን መምሰል( ፈጣሪውን ተመራምሮ አገኘ)::

፪,  🌿ዓለምንና የዓለምን ነገሮች መተው።

፫, 🌿የንስሐ ሕይወት( ንስሐን በትጋት መፈጸም)።

፬, 🌿መታዘዝ (የሚታዘዘውን ሳያጓድል መስራትን)።

፭, 🌿ለሌሎች መኖርን።

፮, 🌿በሰው አለመፍረድን።

፯, 🌿ትሕትናን።
        
1,💥ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡

2,💥ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡

3, 💥በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡

4,💥የበጎ ለውጥ እናት ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ ናቸው

4 ነገሮችን በደንብ ልብ እንበል!
    1, ✨አላማ

    2 ,✨እምነት

    3,✨ጥረት

    4 ✨ጥንቃቄ

9ኙ የቅድስና መንገዶች

፩💥ሃይማኖት
፪💥ጾም
፫💥ጸሎት
፬💥ስግደት
፭💥ምጽዋት
፮💥ፍቅር
፯💥ትህትና
፰💥ትዕግስት
፱💥የዋህነት

✨እነዚኽን ያዟቸው ተጠቀሙባቸው

🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤
እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።

✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት
🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)

ለ ፳፻፲፯ የቤት ሥራ የሚሆኑ ፭ መልእክቶች

፩.ለጸሎት ተነሱ
፪.ክርስትናን መኖርን እንጀምር
፫.የእውነት ንስሐ ያስፈልገናል
፬.ካቆሸሸን ማኅበራዊ ሚዲያ ጥቂት እንራቅ
፭.ትልቁ መከራ እንዳያገኘንhttps://t.me/enabib


††† እንኳን ለጻድቅ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን †††

††† በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን (በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
*ክርስትና ያበበበት::
*መጻሕፍት የተደረሱበት::
*ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
*ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-
¤አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤አባ ሰላማ ካልዕ::
¤አቡነ ያዕቆብ::
¤ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::

በተጨማሪም:-
¤12ቱ ንቡራነ ዕድ::
¤7ቱ ከዋክብት::
¤47ቱ ከዋክብት::
¤5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ::

ከእነዚህ ቅዱሳን የጻድቁ ፍሬዎች አንዱ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ናቸው:: ጻድቁ አንዳንዴ "አፍቀረነ እግዚእ" እየተባሉም ይጠራሉ:: ትርጉሙም "ጌታ ወደደን" እንደ ማለት ነው::

ያፍቅረነ እግዚእ የነበሩት በ14ኛው መቶ ክ/ዘ ሲሆን ቁጥራቸው ከ7ቱ ከዋክብት ነው:: ጻድቁ ከልጅነት ጀምሮ በሥርዓቱ ከማደጋቸው ባሻገር እጅግ የተማሩ እንደነበሩም ይነገርላቸዋል::

ለምናኔ ከወጡ በሁዋላ ከኖሩባቸው ቦታዎችም 3ቱ ተጠቃሽ ናቸው:: የመጀመሪያውና ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው ደግሞ ደብረ በንኮል ነው:: ጻድቁ በዚህ ገዳም ከታላቁ ቅዱስ አባ መድኃኒነ እግዚእ ሥርዓተ ገዳምን : ትኅርምተ አበውን : ተጋድሎተ ቅዱሳንን አጥንተው ለመዓርገ ምንኩስና በቅተዋል::

በገዳሙም ለተወሰነ ጊዜ አገልግለው ወደ ጣና አካባቢ ከአቡነ ያሳይና ከአባ ሳሙኤል ዘዋሊ ጋር መጥተዋል:: የመምጣታቸው ምክንያትም ስብከተ ወንጌልን ለማዳረስና ገዳማትን ለመመሥረት ነው::

ሶስቱ ቅዱሳን ለተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በሁዋላ አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሲሔዱ አቡነ ያሳይ ደግሞ ማንዳባን አቀኑ:: ያፍቅረነ እግዚእም ጌታ ባዘዛቸው መሠረት ጣና ውስጥ ገዳም አቅንተው ኑረዋል:: ይህ ገዳማቸው ዛሬም ድረስ በስማቸው ይጠራል::

ጻድቁ አፍቀረነ እግዚእ 3ኛው የሚታወቁበት ገዳም ማኅበረ ዴጌ (ጻድቃነ ዴጌ) ሲሆን ገዳሙ በአክሱም ዙሪያ ይገኛል:: እርሳቸው 3ሺ ቅዱሳን የተሠወሩበትን ገዳም በማገልገላቸውም ዛሬም ድረስ በአካባቢው የታወቁ ሆነዋል::

በተረፈም አክሱም አካባቢ ሌሎች ገዳማትን እንዳቀኑም ይነገርላቸዋል:: ጻድቁ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌልና ገዳማትን በማስፋፋት ከኖሩ በሁዋላ በዚህች ቀን ዐርፈው ለክብሩ : ለርስቱ በቅተዋል::

††† አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ይቅር ብሎ በረከታቸውን ያሳድርብን::

††† ጥር 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጻድቁ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ (አፍቀረነ እግዚእ ዘጉጉቤ - ጣና ውስጥ - ከሰባቱ ከዋክብት አንዱ)
2.አባ ባሱራ
3.ቅድስት ኔራ
4.ቅድስት በርስጢና
5.አባ ዝሑራ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላዕክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ታቦታቸው ጎንደር ከተማ ቀበሌ 09 አካባቢ ይገኛል)
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

††† ቅዱሳንን ታስቡ ዘንድ ቸል አትበሉ::

††† "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. 36:28-31)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††


"በዓላት ከመንፈሳዊ ለዛ እያፈነገጡ ተራ ሰርግ  እየመሰሉ ነው ፤ ለዚህም ተጠያቂዎቹ እኛው ካህናቱ ነን" ሲሉ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ተናገሩ።

ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ /አዲስ አበባ

በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ መሪነት የሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተክህነትና የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነት የሥራ ኀላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤያት ምክትል ሊቃነመናብርት በተገኙበት የከተራ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት አከባበር ትናንት ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተገምግሟል።

በውይይት መድረኩ ዓቢይ ኮሚቴው ኀላፊነት ከተሰጠው ጊዜ ጀምሮ የከተራ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላትን በድምቀት ለማክበር ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት አቅርቧል።

“ጥምቀትን በወልድያ” ሥርዓትና ትውፊቱን ጠብቆ በድምቀት ለማክበር በተደረገው እንቅስቃሴ በዓላቱን ከእስከ አሁኑ በተሻለ ማክበር መቻሉንና የሰበካ ጉባኤያት፣ የሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ የምእመናንና የወጣቶች ተሳትፎና ትብብር በጥንካሬ ተነሥቷል።

የዘንድሮው የበዓል አከባበር ካለፉት ዓመታት የተሻለ ቢሆንም ከተፈለገው መንፈሳዊ ግብ ለመድረስ  መስተካከል ያለባቸው ክፍተቶችንና የገጠሙትን ተግዳሮቶች ዓቢይ ኮሚቴው በሪፖርቱ አመላክቷል። 

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት ቃለ ምእዳን ኹሉም በተሰጠው ጸጋ
የድርሻውንና መንፈሳዊ ኀላፊነቱን በመወጣቱ በዓላቱን በሰላምና በጥሩ ሁኔታ አክብረናል ብለዋል።

ብፁዕነታቸው ለውይይቱ ተሳታፊዎች በተለይም በካህናት ኀላፊነቶች ዙሪያ ባደረጉት አጭር ገለጻ በዓላት በቤተመቅደስም ይሁን በዐደባባይ ሲከበሩ በዘልማድ ሳይሆን በጥንቃቄ እንዲሆን የካህናት ድርሻ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በበዓላቱ ላይ የኦርቶዶክሳውያን ሥርዓትና ትውፊት ያልሆኑ ከመንፈሳዊ ለዛ ያፈነገጡ እንቅስቃሴዎች መስፋፋትና የአባቶችን መመሪያ አለመቀበል እየተለመደ መምጣቱ የግንዛቤ ክፍተት መሆኑን የገለጹት ብፁዕነታቸው በዓላት የሚከበሩበትን ዓላማ በማስተማርና በማስገንዘብ ኀላፊነታችንን አለመወጣታችን ያስከተለው ችግር ነው ብለዋል።

ሕዝቡ በዓላትን ሲያከብር ከሥጋዊ ስሜት ወጥቶ እግዚአብሔርን የሚያነግሥበት እንዲሆን ዓላማውን ለማሳካትና ችግሮችን ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን የሚሠራ ከሀገረ ስብከት፣  ከወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነትና ከአድባራት የተውጣጣ ባለሙያዎችን ያካተተ የጋራ ዓቢይ ኮሚቴ በቅርብ ቀናት ይቋቋማል ተብሏል።

©የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት

Показано 20 последних публикаций.