✟እንዘምር✟


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


✟✟✟በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን✟✟✟
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአቱን የጠበቀየመዝሙር ግጥምናዜማውን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን ይጎብኙት✟
"ድምፁ መልካም በሆነ
ፀናፅል አመስግኑት
እልልታ ባለዉ
ፀናፅል አመስግኑት።"ሀሌሉያ
መዝ150÷5
ዮቲዩብ ቻነል ይቀላቀሉhttps://www.youtube.com/@enzmrbellta

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ
ዘማሪ አቤል ተስፋዬ

የበገና መዝሙር

__ን_ዘ__ም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ__ን_ዘ_ም____ር


✟በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ✟


በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ
'ወበጸሎት ትትኃሰይ መንፈስ/2/


መዓልትና ሌሊት በጾም ፀሎት ተግቶ
አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ
አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት
ስጋ ካልደከመ ች በጾምና ፀሎት

አዝ_

ሙሴ የተባለው ያ የእግዚአብሔር ሰው
ፊቱ የበራለት አርባ ቀን ፆሞ ነው
በሲና ተራራተቀብሎ ህግ
እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድ

አዝ_

የፀሎት እናቷ ስለሆነች ጾም
ትህትናን ይዘን ደግሞም አንድ ሆነን
ብንተጋ በፀሎት ከንሰሐ ጋራ
ጾም ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ

አዝ_

አንደበትም ይጹም አይንም ይረጋጋ
ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ
ድሃን ከመበደል ልብም ተመልሶ
መጾምስ እንዲ ነው የበደለን ክሶ

ዘማሪ አቤል ተስፋዬ


___ዘ___ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
___ዘ___ር


ቅዱስ ላሊበላ

ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ


እ_ን_ዘ__ም__ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን_ዘ__ም__ር


ቅዱስ ላሊበላ

ቅዱስ ላሊበላ ላሊበላ/2/
ዕፁብ ነው ድንቅ ነው የሠራው ምሳሌም የለው/2/
      

ዘውትር ብመላለስ ላሊበላ
ዐይኔም አይጠግበው ላሊበላ
የሠው ስራ አይደለም ላሊበላ
የሥላሴ ነው ላሊበላ
      
አዝ_

በማህጸን ሳለ ላሊበላ
ስለተመረጠ ላሊበላ
ቤተ-መቅደስ ሠራ ላሊበላ
ድንጋዩ ያጌጠ ላሊበላ
      
አዝ_

የአሰራሩ ዘይቤ ላሊበላ
ከላይ ወደ ታች ላሊበላ
ስነ ሕንጻው ሲታይ ላሊበላ
የማይሰለች ላሊበላ
ላዩ አረንጓዴ ነው ላሊበላ
ውስጠኛው ባሕር ላሊበላ
ጸበሉ የፈለቀው ላሊበላ
ከቋጥኙ ስር ላሊበላ
      
አዝ_

በዕምነት የመጡ ላሊበላ
ከቤተ ጊዮርጊስ ላሊበላ
አንቀላፉ  በዚያው ላሊበላ
ምፅአት እስኪደርስ ላሊበላ
ማርኳቸዋልና ላሊበላ
የእግዚአብሔር ቅዱስ ላሊበላ

ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ


__ን_ዘ_ም___ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
__ን_ዘ_ም___ር


ዛሬ ባይሆን

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም

በዚ ጥዑም ዝማሬ ፈጸምን ስለምትከታተሉን ክብር ይስጥልን በዝማሬዎቹ ፍሬ እንደምታፈሩ ተስፋ እያደረኩ ቸር ቆዩን።

እንዘ_ም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እንዘ_ም_ር


ዛሬ ባይሆን

ዛሬ ባይሆን እኔ ማስበው/2/
ለእኔ ያለው ቀን እግዚአብሔር አለው/2/


በሁኔታዎች ተስፋ አልቆርጥም
ጌታ ይረሳል ብዬ አልልም
ለበጎ ይሆናል የከለከለኝ
እኔ እርሱ ካለኝ ሁሌ ሙሉ ነኝ

አዝ____

የጠላት ወሬን እኔ አልሰማም
ታማኙን ንጉስ ፍፁም አላማም
ዘይግቶ መጥቶ እርሱ ይክሳል
አባት ነውና ከአፈር ያነሳል

አዝ____

ከእኔ የሆነ እኔ ምን አለኝ
እንኳን ዕቅዴ እኔም የእርሱ ነኝ
ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይላል
እርሱ ያለው ቀን ሁሉ ይሆናል

አዝ____

በመጠበቅያው ሆኜ ልጠብቅ
መጥቶ እንዳያጣኝ እምነቴን ላጥብቅ
ፈጥሮ የማይተወኝ ይመጣልኛል
መረቤን በአሳ ይመላልኛል


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


እ_ን_ዘ_ም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን_ዘ_ም_ር


ምን ልበል

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


እንዘ_ም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እንዘ_ም_ር


ምን ልበል

እንግዲህ ምን ልበል እንግዲህ ምን ላውራ
እጄን በአፌ አስጫነኝ የአማኑኤል ስራ


በሞት ጥላ ምድር ያሳለፈኝ መርቶ
ደግሞ ዛሬ አስነሳኝ በልጁ ሞት ጠርቶ
ክብሬን ለማይረባ ነገር አልውጥም
ከአመድ ስላነሳኝ ክብሩ ለዘለአለም

አዝ_

የሺ
ሖርን ውሃ ለምን እጠጣለው
ፊቴን የማዞረው ምን አግኝቼበት ነው
ሁልግዜ እየራራ ሳይዘነጋኝ ለአፍታ
እኔ የአይኑ ስስት እርሱ የኔ እርካታ

አዝ_

ስለ
ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ ብለህ
እኔ አልተነቀልኩም ስለፍጹም ፍቅርህ
ቢቀላ እንዳለላ ነጥታ እንደ ባዘቶ
የተከፋው ልቤ ሔደ ተደስቶ

አዝ_

ከወ
ዜ ላይ ቀለብ ምን አልባት ቢሰፍሩ
ወራቶቼ እንባ መከራን ቢያዘሩ
ልቤን ያስነከሰው ያ ቀን አለፈና
የበፍታዬን ኤፎድ ለበስኩ እንደገና


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


_ዘ_ም__ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
_ዘ_ም__ር


ብጽዕት ነሽ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


__ን__ዘ_ም_ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
__ን__ዘ_ም_ር


ብጽዕት ነሽ

ከእግዚአብሔር ተልኮ የነገረሽን ቃል
'አምነሽ የተቀበልሽ ብጽዕት ነሽ ድንግል/2/


በገሊላ ሳለሽ በናዝሬት ከተማ
ከመላዕክት አለም ከሰማይ ከራማ
ብርሃናዊው መልዓክ ተሸክሞ ዜና
ደስታን አበሰረሽ በታላቅ ትህትና
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል

አዝ__

ላም ለኪ ማርያም ድንግል ሆይ አትፍሪ
መዓዛሽን ወዷል እግዚአብሔር ፈጣሪ
ሞገስ አግኝተሻል በቅድመ ሥላሴ
ክብርን የተሞላሽ ምልዒተ ውዳሴ
      እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
      እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል

አዝ__

ትወልጃለሽ ጌታን በመንፈስቅዱስ
ትጠሪያለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ
በያዕቆብ ወገን ይነገሳል ዘለአለም
ለመንግስቱ ሽረት ፍጻሜ የለውም
      እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
      እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል

አዝ__

ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ሳትወልድ የኖረች
በእርጅና ዘመኗ ወንድ ልጅ ጸነሰች
እያለ ሲነግርሽ የሠማዩን ምስጢር
ይሁንልኝ ብለሽ ተቀበልሽ በክብር
      እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
      እንደብስራታዊው እንደ ገብርኤል


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


እ_ን_ዘ_ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ን_ዘ_ም____ር


ወረት የሌለው

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


_ን_ዘ_ም___ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
_ን_ዘ_ም___ር


ወረት የሌለው

ወረት የሌለው መውደድ
ወረት የሌለው ፍቅር
'አንተ ጋር ብቻ ነው
ያለው እግዚአብሔር/2/


ዘመን የማይዘው ጊዜ ማይገድበው
የአንተ ፍቅር ብቻ ቀን በቀን አዲስ ነው
ከዴማስ ጋር ስሔድ ትቼ የአንተን መንገድ
ከቶ መች ቀነሰ ለእኔ ያለ መውደድ

አዝ__

በአመጽ ብጠፋም ከመንጋህ መካከል
ይመሻል ይነጋል እኔን ስትከተል
እንደ ወጣ ይቅር ብለኽ መቼ ተውከኝ
ሴኬም ድረስ ወርደህ ልጅህን ፈለከኝ

አዝ__

ዝናዬም ዘመን ባለጸጋ እያለው
ቤቴ በወዳጆች ቀን በቀን ሙሉ ነው
እንደጤዛ ሲረግፍ ሀብትና ንብረቴ
ያላንተ ማን ነበር በፈረሰው ቤቴ

አዝ__

ታመንኩባቸው ወዳጆች ሲከዱኝ
ህመሜ ስር ሆነው ደጋግመው ሲወጉኝ
ለአንተ ጊዜ ባጣም ለ'ኔ ጊዜ ያለህ
ገፋ ክፉ ቀኔን ከ'ኔ ጋራ አብረህ


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


_ን__ዘ_ም_
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
_ን__ዘ_ም_


ልጁ ነኝ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


_ንዘም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
_ንዘም____ር


ልጁ ነኝ

ልጁ ነኝ የሚካኤል ልጁ
በቤቱ ያደኩኝ በደጁ
'የልቤ ብዬ የምጠራው
ሚካኤል ለኔ አባቴ ነው/2/


በክንፉ እኔን በእጁ ሰይፍ ይዟል
ሚካኤል ሊረዳኝ ቆሟል
እንዳስፈሪ እንደ ንጉስ ሠራዊት
በቀኜ ነው በቀንና በሌሊት
ሚካኤል አባቴ ለዚ እኮ ነው መመካቴ
       ሚካኤል አባቴ   ጋሻ ክብሬ ነው ማለቴ
       ሚካኤል አባቴ   ጎኔ ቆመኽ እንዳቆምከኝ
       ሚካኤል አባቴ   እኔ ለአለም ምስክር ነኝ

አዝ_

ልናገር ላውራ ላዚም ልዘምር
ከፍ አርጌ ልመስክር
መች ይረሳል ልጅነቴ ያሳደገኝ
እቅፍ አርጎ በክንፎቹ የከለለኝ
       ሚካኤል አባቴ   እስከዛሬ ያላልኩትን
       ሚካኤል አባቴ   በልቤ ውስጥ ያኖርኩትን
       ሚካኤል አባቴ   ዛሬ ላውራው በአደባባይ
       ሚካኤል አባቴ   ረድቶኛል ከአባቴ ጋር

አዝ__

ከተኛሁበት ከእንቅልፌ አንቅቶ
ነጻ አወጣኝ እስሬን ፈቶ
በጨለማ በወኅኒ ቤት በእስር
አብሮኝ ነበር ጠባቂዬ ሚካኤል
       ሚካኤል አባቴ   በክፉ ቀን ያለ ጎኔ
       ሚካኤል አባቴ   ያልተለየኝ በድካሜ
       ሚካኤል አባቴ   ሰው የሚወድ የማይንቅ
       ሚካኤል አባቴ   በጌታ ፊት ሚያስታርቅ

አዝ____

ብርቱ እና ኃያል ጽኑ ነው ስሙ
ሚካኤል ሞገስ የሆነው
ምን ይሆናል ሚካኤልን የያዘ ሰው
ምግቡ መና ደመና ነው ሚጋርደው
       ሚካኤል አባቴ   የአባቶቼ መንገድ መሪ
       ሚካኤል አባቴ   በእኔም ህይወት ታምር ሰሪ
       ሚካኤል አባቴ   በመንገዴ ቀድሞ ፊቴ
       ሚካኤል አባቴ   ይስበኛል ወደ ርስቴ



ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ቁ.2 አልበም

ን_ዘም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
ን_ዘም____ር


ያከበርከኝ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


_ን__ዘ__ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
_ን__ዘ__ም____ር


ያከበርከኝ

ያከበርከኝ እኔ ማነኝ
ያስከበርከኝ እኔ ማነኝ
ውለታህ በዛ አባቴ ውለታህ በዛ
ሞገስ ከበባት ቅጽሬ ሆንከኝ መዓዛ


ማዕበሉ አለፈ ባንተ ያለኝ አላሳልፍ
ስኬቴን ጻፈው ጣትህ የመኖሬን መጽሐፍ
'ቃልህ ባያዘው ጭንቄን ባያደላድለው
ዓለም ትለኝ ነበር እኔን መድረሻ የሌለው/2/

አዝ_______

ቀን አየች ነፍሴ ባ'ንተ ከመሶብህ በልታ
ከእሳት ማዕበል ነጥቀህ አኖርካት በከፍታ
'ቀን በቀን ቅኔን ይዤ በፊትህ ምንጓደደው
ሚዛንህ ጸጋ ሞልቶት በፍቅርህ ተምሬ ነው/2/

አዝ_______

በወኅኒ ብርሃን ሞላ ሰንሰለቱ ቀለጠ
በድካሜ እየራራ ሞት በሞትህ ተዋጠ
'ስለአንተ ማን አወቀ ጠንቅቆስ ማን ተረዳ
እኔ ግን ቀምሼ ነው የምለው ማራናታ/2/

አዝ_______

መፍረድ የማይሰለቻት ምድሪቱ ከሳሽ ሆና
ሲገርማት ውሎ ያድራል ስሰለፍ ለበገና
'የዘንዶ ጥርሱ ሲፏጭ ጉድጓድ እየተማሰ
በምስጋናዬ ብቻ ኑኖሬዬ ተዳበሰ/2/

አዝ_______

ያህዌን ያለ ሲወድቅ ማን አለ የከሰረ
አያይም አይኔ ጉድለት ይኖራል እየዘመረ
'ኑሃሚን እንዳየች በእንባ ማዕበል ሆና
ማግኘት ይመጣል ፈጥኖ አላዝንም በፈተና/2/


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


_ን__ዘ__ም____ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
_ን__ዘ__ም____ር




ስራኝ እንደቃልህ

ስራኝ እንደቃልህ አኑረኝ/2/
ከምርጦችህ መሃል እንደ አንዱ አድርገኝ
ስራኝ እንደቃልህ አኑረኝ


ለመንገዴ መብራት ይሁንልኝ ህግህ
አስተዋይ አድርገኝ በስራ እንድገልጽህ
ማንም የማይቀማኝ በጎ ዕድልን ልምረጥ
ቃልህን እንድሰማ ከእግርህ ስር ልቀመጥ

አዝ___

ትላንትን አስረሳኝ አልኑር በትዝታ
ስምህን ልሸከም ልታዘዝህ ጌታ
በቤትህ ተክለኸኝ በእቅፍህ ኖሬ
አንተን ማክበር ይሁን ዕለት ዕለት ግብሬ

አዝ___

በጸጋ አቁመኝ እርዳ አለማመኔን
አይለፍ በዋዛ ለአንተ አርገው ዘመኔን
አንተ የሰጠኸኝን መልሼ እንድሰጥህ
በአለም አልድከም ታሪኬን ለውጥ

አዝ___

አስጀምረኸኛል ደግሞም አስፈጽመኝ
የማልጠቅም ባርያ እኔ ደካማ ነኝ
የመናገረውን እንዳሳይ በስራ
ቅደም በመንገዴ ጨለማዬን አብራ


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


እ_ንም__ር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
እ_ንም__ር


በማይነገር ስጦታ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ተመስገን ቁ.2 አልበም


_ንዘ_ምር
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
@enzmrbellta ~ @enzmrbellta
_ንዘ_ምር

Показано 20 последних публикаций.