🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።
✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼
👇🏾👇🏾👇🏾
@hamdquante
አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል
👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


🌙
    ረመዷን
               🌙

📖 {وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ}
{ጌታህ የፈለገውን ይፈጥራል (የፈለገውንም) ይመርጣል (ይሾማል)።}


☝️አላህ ወራቶች ፈጠረ። ከወራቶች; የረመዷን ወር መረጠ!!


ረመዷን ማለት
🌙ሸይጣን የሚታሰርበት፣
  🌙ነፍስያ የምትዳከምበት፣
   🌙ቀልብ የምትረጥብበት፣
      🌙የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፣
        🌙የጀሀነም በሮች የሚዘጉበት፣
     🌙ወንጀልና በደል የሚቀንስበት፣
  🌙እዝነትና በረካ የሚሰፍንበት፣
🌙ወንጀለኞች የሚፀፀቱበት፣
  🌙ታዛዦች የሚጠነክሩበት፣
    🌙ዝንጉዎች የሚነቁበት፣
     🌙ንቁዎች የሚሸምቱበት፣
      🌙ሸማቾች የሚያተርፉበት፣
💫በአጠቃላይ
   💎የጀነት ገበያ የሚፋፋምበት ወር ነው!!


🌙እነሆ……
  ይህ ወደ ተመረጡ ህዝቦች, በተመረጠው መልዕክተኛ, ላይ በተመረጠው መላኢካ አማካኝነት የተላለፈው የተመረጠውና ታላቁ የረመዷን ወር ሊገባ በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ብቻ ቀርተውታል።

   🤲ደርሰው ከሚጠቀሙት ያድርገን🤲





🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙
https://t.me/hamdquante


🔥
ሸይጧን…………
ወሕኒ ከመወርወሩ በፊት "የዓመቱን ልዝጋ" ያለ ይመስላል; ሲረባረቡ።



🤲አላህ አደብ ይስጣችሁ🤲
https://t.me/hamdquante


🚫Attention!!

እንደ መብት ብናየው እንኳ…………
  ማንም ማንም ላይ ካመነበት ምንም መናገር ይችላል:


ግን……………
  የማይናገሩትን እንዲናገሩ ማስገደድ ወይም ባለ መናገራቸው ሌላ ግምት እንዲያዝባቸው መገፋፋት ግን ፍፁም ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው።




https://t.me/hamdquante



"የሚጨቃጨቁ ሰዎች አብረው ሆነው ሳሉ ድምፃቸው ከፍ አድርገው ለምን ይጯጯሃሉ?"
ብሎ ሲጠይቅ…………

"በአካል ቢቀራረቡም በዝያች ቅፅበት ልባቸው ስለ ተራራቀች የተራራቁ ይመስላቸውና አንደኛው ሌላኛው ለማሰማት ሲል ይጮሃሉ።"




https://t.me/hamdquante



"ለምን አረፈድክ?" ሲባል…………

የተገራው; "ከእናቴ ጋ ቆይቼ ነው" ይላል
ጋጠወጡ; "እናቴ አስቆይታኝ"



ትሁት ሁንና ቃላቶችን ምረጥ!!
https://t.me/hamdquante




🤲



    አላህ የረመዷንን ወር ሲያስተዋውቀን………


📖{شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ…}
{የረመዷን ወር (ማለት) ያ… ቁርኣን የተወረደበት……}
ይለናል።

ልብ በሉ………
  ወሩን አላህ ያስተዋወቀው {ጾም የተደነገገበት} በሚል ሳይሆን {ቁርኣን የተወረደበት} በሚል ነው: ጾም ግዴታ ከመሆኑን ጋ።


  ታድያ; መገለጫው ሁላ ቁርኣን በሆነው ወር ከቁርኣን ጋ ምን ያህል ለመተሳሰር ተዘጋጅተናል??





https://t.me/hamdquante



የጅህልና ትልቁ እርከን ማለት፦
ስለሱ ምንም የማታውቀው የሆነን ጉዳይ ማውገዝ ነው!!


👆ደግማችሁ አንብቡት።




https://t.me/hamdquante



ማንኛውም ሰው…………
ዕውቀት በመማር ላይ እስከቀጠለ ድረስ ዓሊም ነው።

"ዕውቀት በቃኝ" ብሎ ሲያቋርጥ;
የመሀይምነት መንገድ መጓዝ ጀምራል!!




https://t.me/hamdquante



የሰው ልጅ…………
አላህ በዓቅሉ የሚሄድ ነፃ ሰው አድርጎ ፈጠረው;

እሱ ግን………
ክዶና አምፆ ጅህልናው የሚነዳው ባሪያ መሆን መረጠ።




https://t.me/hamdquante



ሰው አንድን ሰው በጭፍን ከመከተልና አብዝቶ ከማድነቅ እንዴት ሊድን ይችላል??

"ተከታይህ ነኝ፣ አድናቂህ ነኝ ..." ብሎ ከልክ በላይ እያሞገሰ፣ እያወደሰ፣ አላስቆም አላስቀምጥ ብሎ ላስቸገረህ ሰው መድሃኒቱ ምን መሠለህ ...

ራስህን አታስወድድበት፣ ተፈላጊነትህን ከፍ አታድርግ፣ አትሸሸው፣ ቅረበው፣ አግኝተህ አውራው።

ከዚያ…………
ቀርቦ አይቶህ ሰው መሆንህ ሲያውቅ፣ ፍፁም እንዳልሆንክ ሲያስተውል፣ ጃሂል መሆንህን ሲገነዘብ፣ እንደምትዘባርቅ ልብ ሲል፣ እንደምትሳሳትና እንደምታጠፋ ሲረዳ ...ማድነቅ፣ ማወደስና በጭፍን መከተል ትቶ ለካ ይሄ ነው እንዴ ብሎ እሱ ራሱ ይሸሽሃል። ከዚያ ምን ሆኖ ነው ብለህ አንተው ራስህ ትፈልገዋለህ።
ጀርበው እስቲ:

እህእ!!
ሰው ቀላል ፍጡር መስሎሃል.……..




(Copy)
https://t.me/hamdquante



    ከመልካሞች አንደበት ስሞታ ሳይሆን ውለታ ነው የሚሰማው!!


    ነብዩላህ ዩሱፍ ከህፃንነቱ ጀምሮ ሙሉ ዕድሜው በስቃይ የተሞላ መራራ ሕይወት እንጂ ሰላም እና ዕረፍት ያለው የሕይወት ገፅታ ለማየት አልታደለም ነበር። ከመሆኑም ጋ: በንግግሩም ይሁን በተግባሩ ሁሌም ውለታን ሲጠቅስ እንጂ ስሞታ ሲዘረዝር ታይቶ አይታወቅም ነበር። 
ለምን????

  የዚህን ጥያቄ መልስ የታሪኩ መጨረሻ ላይ እናገኘዋለን። {… وَقَدْ أَحْسَنَ بِي…} ሲል። ያንን ሁሉ መከራ እና ሰቃይ ሲፈራረቅበት ጌታው እሱ ላይ የዋለው ውለታ እና አዘኔታ መሆኑን እንጅ ሌላ አይታየውም ነበር።


ለምሳሌ፦
  እነዝያ ሁሉ ዓመታት በግፍ ታስሮ ከእስር ሲወጣ: በበደል በመታሰሩ ማዘን እና ስሞታ ማቅረብ ሳይሆን ከእስር በመፈታቱ ጌታው የዋለለትን ውለታ ይጠቅሳል………
{…وَقَدْ أَحْسَنَ بِي إِذْ أَخْرَجَنِي مِنَ السِّجْنِ…}
{…(ጌታዬ) ከእስር ቤት ባስወጣኝ ጊዜ በእርግጥ ውለታ ውሎልኛል።…}



  ወንድሞቹ እንደዛ ጠልተው አሰቃይተው ከሸጡት በኋላ: እነርሱን ሲገናኝ ስለ ሰሩበት በደል ስሞታ ከማቅረብ ይልቅ በድጋሚ በሰላም ከእነሱ እና ከወላጆቹ እንዲገናኝ አላህ የዋለለትን ውለታ ይጠቅሳል………
{…وَجَاءَ بِكُم مِّنَ الْبَدْوِ مِن بَعْدِ أَن نَّزَغَ الشَّيْطَانُ بَيْنِي وَبَيْنَ إِخْوَتِي…}
{…ሸይጣን በእኔና በወንድሞቼ መሃል ካበላሸ በኋላ, እናንተን ከገጠር ወደ እኔ ሲያስመጣችሁም (ጌታዬ) በእርግጥ ውለታ ውሎልኛል።…}



  ያቺ ኣመፀኛ ሴት እንኳ ለብልሽት ስትጠራው: እሷ እንዲማግጥበት የፈለገችው ባልዋ ለእሱ ባለ ውለታው መሆኑን ይጠቅሳል………
{…قَالَ مَعَاذَ اللَّهِ إِنَّهُ رَبِّي أَحْسَنَ مَثْوَايَ…}
{…በአላህ እጠበቃለሁ: እሱ (ባልሽ) መኖሪያዬን ያመቻቸልኝ ዐለቃዬ ነው አላት።…}



  ሁሉም ዐይነት ፈተናም ይሁን መከራ ሲገጥመው: አላህ የሚውልለት ውለታ እንጂ ሰዎች ለፈፀሙበት በደል ወይም አላህ ላይ ተማሮ ስሞታ ሲያቀርብ አይታይም። የንፁህ ልብ ባለቤት የሆኑ ደጋጎች ሁሌም እንዲህ ናቸው። ተቆጥሮ የማያልቅ ውለታ ለጋሽ የሆነው ጌታቸው ከማመስገን የሚመልሳቸው ክስተት የለም። በመሆኑም ጌታቸው የዋለላቸው ሰፊ ውለታ ሁሌም ስለ ሚያስታውሱ: ሁሌም ለጌታቸው ተገዢ እና አጎብዳጅ ታማኝ ባሪያ ይሆናሉ።


  ነብዩላህ ዩሰፍ የአላህን ውለታ ብቻ የሚያስታውስ አመስጋኝ ባሪያ በሆነ ጊዜ: አላህም ከሰፊው ቱሩፋቱ ጨምሮ ጨማምሮ ከመስጠት አልተቆጠበም። በዚህም ሂደት ነው ባሪያ ተደርጎ በመሸጥ የጀመረው ሕይወት ንጉስ እና መሪ ሁኖ የተጠናቀቀው።


  ሁላችንም ቀን ከሌት በአላህ ፀጋ እና ውለታ የምንገለባበጥ ባለ ፀጋዎች ነን፤ ይህንን አውቆ የሚያመሰግን ልብ ግን አጣን።




🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante


ሰሞኑ እየተለቀቁ ያሉ ዐይነት አጫጭር ጥቅስ እና አባባሎች መቀጠል አለባቸው ወይስ ይቅሩ??
Опрос
  •   መካሪ እና አነቃቂ ናቸው ይቀጥል።
  •   ጥቅም የለውም ይቅር።
  •   ከእኔ ሕይወት ጋ ምን አገናኘው?
115 голосов



ስኬታማ መሆን ከፈለክ………
ለኪሳራ ካለህ ፍራቻ የበለጠ ለስኬት ያለህ ጉጉት ከፍ ሊል ይገባል!!





https://t.me/hamdquante



ስኬት ማለት፦
ከአንድ ውድቀት ወደ ሌላ ውድቀት ተስፋ ሳይቆርጡ መሸጋገር ነው።



https://t.me/hamdquante



እጆችህ በኪስህ ውስጥ አርገህ
የስኬት መሰላል ላይ መውጣት አትችልም!!





https://t.me/hamdquante


📖{إِنَّ لَكَ أَلَّا تَجُوعَ فِيهَا وَلَا تَعْرَى}
{ለአንተ እሷ ውስጥ አለ መራብም አለ መታረዝም አለልህ።}

[ጣሀ:¹¹⁸]


መራቆት ውበት ቢሆን ኖሮ ከጀነት ፀጋዎች ውስጥ ይገለፅ ነበር; ግን በተቃራኒው ነው።





https://t.me/hamdquante



ለራሱ ክብር ያለው ሰው ነው
ቃሉን ማክበር የሚችለው!!





https://t.me/hamdquante



የጊዜ አሳሳቢነት መረዳት
የጥበብ በር መክፈቻ ቁልፍ ነው!!





https://t.me/hamdquante

Показано 20 последних публикаций.