#ጥር_4
አንድ አምላክ በሚሆን በ #አብ በ #ወልድ በ #መንፈስ_ቅዱስ ስም
ጥር አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የሚወደው የሐዋርያው #ቅዱስ_ዮሐንስ የፍልሰቱ መታሰቢያ ነው፣ #አባ_ናርዶስ_ዘደብረ_ቢዘን እና #የአቡነ_መልከጼዴቅ_ዘዋሸራ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ
ጥር አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት #ጌታችን_፣መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ የፍልሰቱ መታሰቢያ ሆነ።
ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ ሀገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ከ #ጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ።
ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረሰው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።
ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ወዳለበት ወደ የብስ ባሕሩ ተፋው ስለ መገናኘታቸውም #እግዚአብሔርን አመሰገኑት በዚያን ጊዜም ተነሥተው ወደ ኤፌሶን ከተማ ገቡ ግን በክብር ባለቤት #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስም ይሰብኩ ዘንድ አልተቻላቸውም እነዚያ ያገር ሰዎች እጅግ የከፉ ናቸውና።
ስለዚህም ምክንያት ፈጥረው ዮሐንስ ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤት እሳትን የሚያነድ ሆነ ረድኡ አብሮኮ ሮስም አጣቢ ሆነ ያቺ ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ነበር መጻተኞችም ስለሆኑ ታጉሳቁላቸዋለች ትደበድባቸዋለች ትረግማቸዋለች ባሮቿም እንደሆኑ ጽፈውላታልና ለእርሷ ባሮች አደረገቻቸው በዚህ በታላቅ ጒስቊልና ውስጥ ኖሩ።
ከዚህም በኃላ በአንዲት ዕለት ይታጠብ ዘንድ የአገረ ገዥው ልጅ ገባ በዚያም የውሽባ ቤት ከተሠራ ጀምሮ የሰይጣን ኃይል አለ የመኰንኑንም ልጅ አንቆ ገደለው በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ለዚያ ለሞተው ሊያለቅሱለት ተሰበሰቡ የከበረ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር መጥቶ እንደ ሰው ሁሉ ሊያይ በዚያ ቆመ።
ሮምናም በአየችው ጊዜ ረገመችው አንተስ በጌታዬ ልጅ ሞት ደስ ብሎህ ልትዝትብኝ መጣህ አለችው ቅዱሱ ግን በቅንነት አይዞሽ አትዘኝ አላት ይህንንም ብሎ ወደ ሞተው ቀረብ ብሎ በ #መስቀል ምልክት አማተበበት በፊቱም ላይ እፍ አለበት። በዚያንም ጊዜ ያ ሞተው ድኖ ተነሣ የአገር ሰዎችም ደነገጡ ሮምናም ወዮልኝ #እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን አለች። እርሱም አይደለሁም እኔ አገልጋይ ሐዋርያው ነኝ እንጂ አላት በእነርሱ ላይ የሠራችውን በደል ሁሉ ይቅር ይሏት ዘንድ መሪር ልቅሶ በማልቀስ ሐዋርያትን ለመነቻቸው እነርሱም አረጋጓት አጽናኗትም።
ከሀገሩም ሰዎች ብዙዎቹ በክብር ባለቤት በ #ጌታችን_በመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በፊታቸውም ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ይህንንም አይተው የሀገሩ ሰዎች ሁሉም በ #ጌታችን አመኑ። ከጣዖታቱ አገልጋዮች በቀር እነርሱም ሰይጣን በእርሱ ላይ ስለሚያነሣሣቸው ሊገድሉት ይሹ ነበር ነገር ግን ምርጦቹን #እግዚአብሔር ጠበቃቸው።
የከበረ ዮሐንስም ሁሉንም #እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከመለሳቸው ድረስ ታላቅ ድካምና ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት። የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም ስለ ልቡናቸው ደንዳናነት ጣዖታትን ስለመውደዳቸውም ስለ እነርሱ መስክሮአል። እርሱም ዮሐንስ በታላቅ ድካም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው። ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትን ዲያቆናትን ሾመላቸው።
ከዚህም በኃላ ከእስያ በዙርያዋ ወዳሉ አገሮች ሁሉ ወጥቶ አስተማረ #እግዙአብሔርንም ወደማወቅ መለሳቸው። ይህም የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም። ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለም ሲስ የሚባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው። ራት ሲበሉ በ #ጌታ_ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው ያለው ይህ እርሱ ነው።
#ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም ጋር በ #መስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው።
ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስለርሱ #ጌታ_ኢየሱስን አቤቱ ይህስ እንዴት ነው ብሎ የተናገረ #ጌታ_ኢየሱስም እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደዱኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት ይህ ነው ።
የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የ #ጌታችን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም።
ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ። ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጐድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በ #ክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ #ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና።
ሁለተኛም እንዲህ አላቸው እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከ #እግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም።
ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው #እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
#እናት_ቤተ_ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
*ወንጌላዊ
*ሐዋርያ
*ሰማዕት ዘእንበለ ደም
*አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
*ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
*ወልደ ነጐድጉዋድ
*ደቀ መለኮት ወምሥጢር
*ፍቁረ እግዚእ
*ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
*ቁጹረ ገጽ
*ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
*ንስር ሠራሪ*ልዑለ ስብከት
*ምድራዊው መልዐክ
*ዓምደ ብርሐን
*ሐዋርያ ትንቢት
*ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
*ኮከበ ከዋክብት
=>በ #ቅዱስ_ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል #ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር::
=>ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን:: ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን::
#አባ_ናርዶስ_ዘደብረ_ቢዘን
ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ስንክሳሩ ‹‹ተጋዳይ የሆነ በጥላው ብቻ ከይሲን የገደለ የደብረ ቢዘኑ አባ ናርዶስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡ እርሱም እግሮቹ እስኪያብጡ ድረስ ቆሞ በመጸለይ የተጋደለ ነው›› በማለት በአጭሩ የገለጸው ጻድቁ አባ ናርዶስ ዕረፍቱ ነው፡፡
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእኚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo