ስለ አንዳንድ ካምፓኒዎችና ሰራተኞቻቸውን እንዴት እንደሚንከባከቡ ስናነብ አግኝተን ያስገረመን የጉግል ነገር .
...
የአለማችን ግዙፉ የግል ኩባንያ ጉግል ከ34 ሺህ በላይ ሰራተኞች አሉት ::
እና እድል እውቀት እና አጋጣሚ ቀንቶት የዚህ ካምፓኒ ሰራተኛ የሆነ አንድ ሰው በህይወት ሳለ አሪፍ የሚባል ደሞዝ ፡ እና ብዙ ጥቅማ ጥቅም የሚያገኝ ሲሆን ፡ በሆነ ምክንያት በሞት ሲለይ ደግሞ . ቤተሰቡ ችግር ላይ መውደቅ የለበትም ፡ ሚስቱ መቸገር የለባትም በሚል ለባለቤቱ .. ሌላ ሰው እስካላገባች ድረስ ለአስር አመታት ድረስ ፡ ሟች ባለቤቷ ሲከፈለው የነበረውን ደሞዝ ግማሽ በየወሩ ይከፈላታል ።
በህይወት እያለ የገዛቸውን አክስዮኖች ካሉም በስሟ ይዛወራል ።
ሰውየው ልጆች ካሉት ደግሞ 19 አመት እስኪሞላቸው በየወሩ 1 ሺህ ዶላር ደሞዝ የሚያገኙ ሲሆን ልጆቹ የሙሉ ጊዜ ተማሪ ከሆኑ ደግሞ ፡ ይህ የ1ሺህ ዶላር ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ እስከ 23 አመት እስኪሆናቸው ድረስ ይቀጥላል ።
ባጠቃላይ የጉግል ሰራተኛ አደለም እያለ ፡ በሞት ሲለይም አይቸገርም ።
@wasihune