🌸ከቁርኣን ጥበቦች...
السلام عليكم ورحمةلله وبركاته
➰ዱዓ ስታደርግ ያ ረቢ "يا رب" አትበሉ ረቢ"رب" በሉ
ለመሆኑ ለምንድነው አሏሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ በቁርኣን ውስጥ የዱዓ አንቀፆችን ሲጠቅስ" يا" "ያ " የምትለዋን ሃርፈ ኒዳዕን የሚደብቃት? ምስጥሩና ጥበቡ ምንድነው?
እነዚህን አንቀፆች ልብ በሏቸው፦
َ رَبِّ أَرِنِىٓ أَنظُرْ إِلَيْكَ
«ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና»
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
رَبَّنَآ أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًۭا
«ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፡፡ »
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
ُۥ رَبِّ لَا تَذَرْنِى فَرْدًۭا وَأَنتَ خَيْرُ ٱلْوَٰرِثِينَ
«ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ »
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
َ رَبِّ إِنَّ ٱبْنِى مِنْ أَهْلِى
«ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው፡፡»
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
رَبِّ ٱجْعَلْنِى مُقِيمَ ٱلصَّلَوٰةِ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَآءِ
«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ፤
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
رَبِّ هَبْ لِى مِن لَّدُنكَ ذُرِّيَّةًۭ طَيِّبَةً ۖ إِنَّكَ سَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ
«ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለኔ ስጠኝ አንተ ጸሎትን ሰሚነህና» አለ፡፡
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربِ اغفر وارحم وانت خير الراحمين )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربِ ابن لي عندك بيتا في الجنة )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
(ربِ إني لما انزلت الي من خير فقير)
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربنا لاتزغ قلوبنا بعد إذ هديتنا )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربِ إني مسني الضر وأنت أرحم الراحمين )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربِ هب لي من لدنك ذرية طيبه انك سميع الدعاء )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
👌በተከበረው ቁርዓን በዱዓ ቦታዎች አንድም ቦታ አላህን በሃርፈ ኒዳእ አልጠራም ። ማለትም አንድም ቦታ ረቢ ከሚለው በፊት ያ ን አላስገባም። ባይሆን ሙሉ ቁርዓኑን ብታዩት አንድም ቦታ አልገባችም። ለምን?
ይህ ነው ምስጥሩ፦
🎁የአረብኛ ቋንቋ ምጡቆች በዚህ ዙሪያ ምስጥሩን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ "يا" (ያ) የምትለዋ ፊደል የምትገባው እሩቅ ያለን አካል ስንጠራ ነው። አሏህ ደሞ ለባርያው ከደም ስሩ በላይ ቅርቡ ነው። ለዚህም ለመነጠቀ ዕውቀት ሲል "ያ" ን አስወገዳት። 🎁
ይህንንም አለን፦
وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ ٱلْوَرِيدِ
... እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡
وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡
❓ታድያ አሁን የምትጠራው ጌታህ ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ አላወክም?ታድያ፦
وَٱسْجُدْ وَٱقْتَرِب ۩
ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡
➰ወደ ጌታህ ቅርብ ለመሆን መጓዝ አያስፈልግም። በጣራም መውጣትን አይጠይቅም።
✂️የድምፅህንም መጮህ አይፈልግም!! መስፈርትም አልተደረገም
ብቻ [ اسجد ] ስገድ... ከፊት ለፊቱ ትሆናለህ!! ከዛም የፈለከውን ጠይቀው!!
✍ጅብሪል ሱልጣን (አቡ ፈቲ)
ማንኛውም አስተያያት ካላችሁ፦
@SeluAlelHabibአድርሱኝ
ሼር ማድረጉ አትርሱት
ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ።
🌻 • • • ● ❀ 🎀 ❀ ● • • • 🌻
┏━━━━━━━━
🌷
@Abufetiya1┗━━━━━━━━
https://telegram.me/Abufetiya1