° comedy ፊልሞች ሳቅን በመጫር ሰዎችን በማዝናናት ብዙ ተመልካቾችን ማፍራት ትልቅ አቅም አለው። ምክንያቱም የሰው ልጅ አይምሮ ከምንም በላይ ደስ የሚያሰኘውን ፣ ፈታ የሚያረገውን ነገር አጥብቆ ይፈልጋል። ሳቅ ደግሞ ከደስታም በላይ ለጤናም ጠቃሚ እንደሆነ ይታወቃል። እኔ በግሌ የዚህ ሀሳብ ደጋፊ ባልሆንም አልቃወመውም ምክንያቱም ሳቅ መሳቅ የአይምሮን መረጋጋት ይፈጥራል ሆኖም ግን ይሄን ሳቅ ለማግኘት የግድ የኮሜዲያኖችን ዘለልቆ ማየት ይኖርብናል ወይም ደግሞ ኮሜዲ ፊልም ማየት ይኖርብናል አልያም የሚያስቀን ጓደኛችን ጋር በመሄድ በሱ ቀልድ መሳቅ ሊኖርብን ነው። ሆኖም ይሄን ጓደኛችንን በፈለግነው ሰአት እና ቦታ አናገኘውም። ስለዚህ በፈለግነው ሰአት እና ቦታ አይምሮአችንን ለማዝናናት እንደ ልብ የሚገኘው የኮሜዲ ፊልም አልያም የኮሜዲያኖችን ፕሮግራሞች /ቀልድ/ ማየት ነው። አብወ
ዛኛው የአለም ህዝብ ማለትም በከተማ ውስጥ ከሚኖሩት ውስጥ ከ90% በላይ በላይ የሚሆኑት የኮሜዲ ፊልም ያያሉ። እንዲሁም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመልካቾች የሚመለከቱት የኮሜዲያን ፕሮግራሞች እንደ አሸን እየፈሉ ነው።
ብዙ ተመልካች እና ብዙ ኮሜዲያን እንዴት በዙ?
° በመጀመሪያ የተደረገው ነገር ቢኖር ተመራማሪዎች ተሰብስበው ባደረጉት ጥናት መሰረት የሚስቅ ሰው እድሜው ረጅም ነው ብለው ምርምራቸውን ይፋ አደረጉ። በዚህ ሀሳብ መሰረት ከሄድን የማይስቅ ሰው እድሜው አጭር ነው ማለት ነው። በመቀጠል ይሄን የምርምር ውጤት ያሉትን በየሚዲያው እንደጉድ አሰራጩት ህዝቡም ደግሞ አይጠይቅም እንደ ፈጣሪ ቃል አምነው ተቀብለው እድሜውን ለማርዘም ሳቅ ጀመረ። ሳቅ ደግሞ እንደፈለጉ ስለማይገኝ የሚያስቅ ነገር የግድ ማግኘት አለበት ስለዚህ የሚያስቁ ነገሮች የሚያስቁ ነገር የሚገኙበት መንገድ በማለት ፊልሞችን ፣ አጫጭር ድራማዎችን እንዲሁም የኮሜዲያን የመድረክ ስራዎችን (Stand up comedy) እንደ ዋና አማራጭነት አስቀመጡ። ከዛም
ይሄን ሁሉ ነገር ካቀረቡ በኋላ ፊልሞች እና የኮሜዲያን ስራዎች እንደ አሸን መፍላት ጀመሩ በዛው ልክም የተመልካች ቁጥር እየጨመረ መጣ። ይሄ ከሆነ በኋላ ደግሞ ድብቅ የሆኑ መልእክቶች (Subliminal Message) እና ግልፅ የሆኑ ሰበካዎች በነሱ አማካኝነት ያካሄዱ ጀመሩ።ይሄን ሁሉ ነገር ከጥንሰሳው የጨለማው አለም ሰዎች ያሴሩት ሴራ መሆኑ ግልፅ ነው።
° ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያዊውን ሰው በላቸው ግርማ ሎሬት የሳቅ ንጉስ በማለት ተሾመ።ሪከርዱን የያዘው ሶስት ሰዓት ከ ስድስት ደቂቃ ያለማቋረጥ በመሳቅ። ከዛም ሳምንት አልቆየም በየት/ቤቱ እየዞሩ በነሱ ስፖንሰርነት የሳቅ ውድድር በማለት በሚያጓጓ ሽልማት ተጀመረ። በእሱ የሰለጠነችው እና ለውድድሩ በቂ ዝግጅት ያደረገችው በሙሉ ድምፅ አሸነፈች። ሌሎች ግን በውድድሩ ቀን ውድድር እንዳላቸው ተነግሯቸው እድላቸውን ሊሞክሩ ሄዱ።ሆኖም ግን አሸናፊዋ የሱ ሰልጣኝ ሆነች። ይህ ውድድር ፍትሀዊ አልነበረም። ሁሉም ተወዳዳሪ እኩል ሰልጥኖ መዘጋጃ ጊዜ ተሰጥቶት መወዳደር ሲገባው አንዳንዶቹን ብቻ ለይት አሰልጥኖ የውድድሩ አሸናፊ ማድረግ እንደ ጨዋታ ነው የሚቆጠረው። ከሳቅ ውድድሩ ማግስት የሳቅ ት/ቤት መከፈቱ በየቦታው ተናገሩ በየቦታው ማስታወቂያ መለጣጠፍ ጀመሩ በፍጥነት ኢትዮጵያችንን ቀልብ ያዙት። ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያችንን ለሳቅ ልዩ ቦታ መስጠት ጀመሩ። ተቆጣጠሩን ማለት ይሄ አይደለ።በአለም ዙሪያ በሎሬት ደረጃ ስማችን መጠራቱ በጣም የሚያስደስት ቢሆንም ከጀርባው ያለ ሴራ ግን አደገኛ ነው። ሰውየው የነሱ አባል ነው እያልኩ አይደለም አውቆትም ይሁን ሳያቀው ግን ለነሱ አላማ ማስፈፀሚያነት ውሏል።
° እንግዲ ይህ ሁሉ ነገር ከሆነ 8 አመት ሆኖታል። በነዚህ አመታት ውስጥ የመጡትን ለውጦች እዩ የሚቀልዱ ቀልዶች በፊልሙም ሆነ በመድረክ ስራዎች የቃላት አጠቃቀማቸውን ለውጥ እዩ በጣም ለውጥ አለ። የሚያሳዝነው ግን በጣት የሚቆጠሩ ኮሜዲያን ብቻ ሌሎቹ የሚቀልዱት ቀልድ እንኳን ሊያስቀን ጭራሽ የሚያስለቅስ ነው ቀልድ ይሁን ምን ይሁን ማይታወቅ ነገር ነው ቀልድ ብለው የሚያቀርቡልን። ሲኒማ ቤት እራሱ በብዛት ሚቀበሉት ኮሜዲ ያለበትን ነው። የማያስቅ ከሆነ ታዋቂ ስም ያላቸው ተዋናዮች የሰሩበት እሱንም ብዙ ትችት ስለቀረበባቸው ነው ማሳየት የጀመሩት እንጂ እናንተ እራሱ መገምገም ትችላላችሁ።
°ለዛሬው እዚጋ ይብቃን በቀጣይ ደግሞ በምን አይነት መልኩ አይምሮ አጠባ እንደሚያካሂዱ እናያለን ማንኛውንም አስተያየት እና ጥያቄ በ
@Yotor_ab ላይ አድርሱኝ
t.me/elohe19