👉አል-ኢሻራ👈


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


☞ሸሪዓዊ ጥቆማዎች የሚስተናገዱበት ቻነል!

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA
💡የህዳሴው ግድብና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች!

⚡️ውድ የ ☀️ሁዳ መልቲሚዲያ ቤተሰቦች
🕯 ስለ አባይ ግድብ የተወሰኑ ሙስሊሞችን ለማናገር ሞክሬ ነበር! ምላሻቸውን አጠናቅሬ በዚህ ቪዲዮ አያይዤዋለሁ!

📣ሁላችሁም ተመልክታችሁ ለሌሎችም ያጋሩ ዘንድ አደራ እላለሁ!!!

https://youtu.be/ubv2Hnao0qs


Репост из: ዲን መመካከር ነው
▪️የቴሌግራም ሊንኮች ስብስብ

🔻ሙሐደራዎች ፣ ተከታታይ ደርሶች ፣ ፅሑፎች እና ጠቃሚ ድምጾች የሚለቀቁባቸውን የቴሌግራም ቻናሎች ለመቀላቀል ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ .. ለሌሎችም ያስተላልፉ .. በአሏህ ፍቃድ ተጠቃሚ ይሆናሉ
👇👇


➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
☘ የሐቅ ጎዳናን ስም ለሚያጠፉ ☘
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
🍀 ❶ ከሽብር ጋር በተያያዘ 🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

⭕️ እነሆ ሽብርተኝነትና እስልምና ሆድና ጀርባ የሆኑ ጠላቶች ናቸው❗️ የቁርአን እና የሐዲስ ማስረጃዎችም ሽብርተኝነትን የሚያወግዙ መሆናቸው በብዙ መልኩ ይንፀባረቃል።

አላህ በቁርአን ውስጥ በአላህ ጎዳና ላይ በሚደረግ ትግል ድንበር እንዳናልፍ ይገስፀናል፦
وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
በአላህ መንገድ ላይ እነዚያ የሚጋደሏችሁን ተጋደሉ ፤ ድንበርም እንዳታልፉ፡፡ እነሆ አላህ ድንበር አላፊዎችን አይወድም!
(ምዕራፍ 2 ፤ አንቀፅ 190)

⭕️ ከዚህ አንቀፅና ከሌሎችም መሰል የቁርአን እና ሐዲስ መረጃዎች እንደምንማረው ሙስሊሞች ስነስርአቱን የጠበቀ ፍልሚያ የሚያካሂዱ ቢሆንም ድንበር ከማለፍ እንዲቆጠቡ ታዘዋል፡፡ የሽብር ጥቃት ደግሞ ድንበር ከማለፍ ተግባራት ውስጥ ይመደባልና የተወገዘ መሆኑን ከዚህ እንረዳለን፡፡ እስልምና እና ሽብርተኝነት ጠላት መሆናቸውንም በዚህ እንገነዘባለን፡፡

⭕️ እስልምናን ከሽብር ጋር ለማያያዝ የሚሞክሩ ሰዎች ቁርአን እና ሐዲስ ከዚህ አይነት አስተምህሮ የፀዱ መሆናቸውን ይወቁ❗️

ዙል ቀዕዳህ 7 - 1441

አል - ኢሻራ ቻናል


➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
☘☘ ሙስሊሞች ሆይ! ☘☘
⬇️⬇️⬇️
ኮሮና ከደረሰባችሁ አብሽሩ!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 ውዱ ነቢያችን ﷺ ከሙስሊሞች መካከል ህመም የገጠመውን ሰው ሊጠይቁ ሲሄዱ እንዲህ ይሉ ነበር
⬇️⬇️⬇️
‹ችግር የለም!› አላህ ከሻ የጠራህ ትሆናለህ!›

🔘 ነብያችን ﷺ በዚህ መልኩ የታመሙ ሙስሊሞችን ያፅናኑ እንደነበር ኢማም ቡኻሪ በሐዲስ መዝገባቸው ላይ ዘግበውታል።

➡️ 'የጠራህ ትሆናለህ' ሲሉ 'ከምን?' ከተባለ ---» ከወንጀሎች ነዋ!
🍀 አዎን! በአላህ መሺአ በሽታዎች ከወንጀል ቆሻሻዎች ያጠራሉ!
⬇️
🔘 ታዲያ ምናልባትም በኮሮና ወረርሺኝ መነካቱ ላጋጠማቸው ሙስሊሞች የምናስተላልፈው መልእክት የነብያችን ማፅናኛ ምሳሌ ይሆናል
⬇️⬇️⬇️
''‹ችግር የለም!› - አላህ ከሻው የጠራችሁ ትሆናላችሁ!''
لا بأس طهور إنشاء الله!
(بخاري)
🔘 ብቻ ግን ኢማናችሁን ጠብቁ❗️
➡️ ልብ አይታመም እንጂ በሽታ ያለ ነው ዘመዴ!

🔘 ወረርሺኝም ሆነ በጥቅሉ ማንኛውም በሽታ አማኞች ወንጀል እንዲሰረዝላቸው ማድረጉ የአላህን እዝነት ያስገነዝበናል፡፡ ወንጀሎችን ለማበስ ሁሌም ፍላጎት እንዳለውና መሃሪ እንደሆነ ያስታውሰናል።

➡️ ሰበብ እየፈለገ ወንጀሎችን የሚምር ጌታ መሆኑ አብዝቶ ያስመሰግነዋል።
الحمد لله رب العالمين!
🔘 ወላሂ ፍጡሮቹ በመሆናችን ታድለናል!

🌴 ስለዚህ ሙስሊሞች ሆይ!
⬇️⬇️⬇️
ኮሮና ሳይመጣ በፊት መጠንቀቁ ቢያሻም እንኳ ምናልባት ከመጣ ➡️አብሽሩ! ወንጀልን ያብሳል ኢንሻአላህ! ☘ የተያዙብንን አላህ ዓፊያ ያድርግልን፡፡

አል ኢሻራ


➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
☘☘ ኢሻራ (ጥቆማ) ☘☘
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
🍀 ከባድ ነገር ነው የገጠመን! 🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 የኮቪድ ወረርሺኝ ከተከሰተ በኋላ ምናልባትም የመስጊድ ኻዲሞችና ከነሱ ጋር የሚቀራረቡ አንዳንዶች ካልሆኑ በቀር የተቀረው ሰው ከመስጊዶች ከራቀ ሰንበትበት ብሏል።

🔘 በሳምንታዊው ዒዳችን ጁሙዓህ እንኳ ወደ መስጊድ መትመማችን ቀርቶብናል። ቀላል ጉዳይ አይደለም ወገን! ፤ ከባድ ነገር ነው የገጠመን!

➡️ እንደው አላህ ይድረስልንና ከድሮውም የተሻልን ሰጋጆች አድርጎ ወደመስጊድ ይመልሰን።

አል ኢሻራ


★★★★★★★★★★★★

💎 ረሱል ﷺ "ማንኛውም ሙስሊም ተክልን ተክሎ ወይም አዝርዕትን ዘርቶ ሲያበቃ፤አህዋፍ፣ሰዎች ወይም እንስሳት ቢበሉለት ሰደቃ የሆኖ ይቆጠርለታል። "ብለዋል።


➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
☘☘ ኢሻራ (ጥቆማ) ☘☘
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
🍀🍀 እንመለሳለን! 🍀🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 የሰው ልጅ ሁሉ በሰራው ስራ ፍርድ ሊያገኝ ወደ ጌታው የሚመለስ መሆኑ ከታላላቅ እውነታዎች መካከል ይመደባል፡፡ ይህ ጉዳይ እጅግ አንገብጋቢ ነውና በቁርአን እና ሐዲስ ላይ በብዙ መልኩ ተብራርቷል
➡️ አንዱን እናውሳ
⬇️⬇️⬇️
🔘 አላህ سبحانه وتعالى ሱረቱል ያሲንን በቋጨበት 83ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ይለናል ⬇️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✴️فَسُبْحَانَ الَّذِي بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
✴️ ያ የሁሉ ነገር ስልጣን በእጁ የሆነው ጌታ ጥራት ይገባው ፤ ወደርሱም ትመለሳላችሁ!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 አላህ ተመላሽ መሆናችንን በዚህ መልኩ አስገንዝቦ ምዕራፉን ቋጭቶታል፡፡
➡️ እጅግ ድንቅ አጨራረስ!
⬇️⬇️⬇️
ግና ካስታወስን ነዋ!

አል ኢሻራ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
۞ قَالَتِ الْأَعْرَابُ آمَنَّا ۖ قُل لَّمْ تُؤْمِنُوا وَلَٰكِن قُولُوا
أَسْلَمْنَا وَلَمَّا يَدْخُلِ الْإِيمَانُ فِي قُلُوبِكُمْ ۖ وَإِن تُطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ لَا يَلِتْكُم مِّنْ أَعْمَالِكُمْ شَيْئًا ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

════ ¤❁✿❁¤ ════

✨ የዐረብ ዘላኖች «አምነናል» አሉ፡፡ «አላመናችሁም፤ ግን ሰልመናል በሉ፡፡ «እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና (ጠልቆ) አልገባም፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ብትታዘዙ ከሥራዎቻችሁ ምንንም አያጎድልባችሁም፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡

http://t.me/MewedaChannel


➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
☘ ኢስላማዊው የሂጅራ ካላንደር ☘
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 የሂጅራ ካላንደር የነብያችንን ﷺ ከመካ ወደ መዲና የተደረገ ስደት መሰረት ያደረገ ሲሆን 12 ወራትን ይይዛል፡፡

🔘 ይህ የነብያችን ﷺ ከመካ ወደ መዲና የተደረገ ስደት የተፈፀመው እንደ ጎርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር በ 622 ዓ.ል ሲሆን ይህ ክስተት ለሂጅራ የዘመን አቆጣጠር እንደ መነሻ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

🔘 ሂጅራ የሚለው ቃል 'ስደት' የሚል ትርጓሜን የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ካላንደር ስያሜ ላይ ያረፈበት አገባብ ይህንኑ ስደት ያመላክታል፡፡

🔘 የሂጅራ አቆጣጠር የወራት ቅደም ተከተል የሚከተለውን ይመስላል
⬇️⬇️⬇️
❶ ሙሐረም
❷ ሰፈር
❸ ረቢዓል አወል
❹ ረቢዓ ሣኒ
❺ ጁማደል አወል
❻ ጁማደ ሣኒ
❼ ረጀብ
❽ ሸዕባን
❾ ረመዳን
❿ ሸዋል
⓫ ዙል ቂዕዳህ
⓬ ዙል ሒጃህ

አል ኢሻራ


➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
🍀🍀🍀
እስልምናን በገንዘብ ማስቆም አይቻልም
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 በገንዘብና በቁሳቁስ እርዳታ በኩል አድርገው እስልምናን ለማጥፋት የሚሞክሩ ሰዎች በአንድ በኩል ሙስሊሞችን ከዲናቸው ለመጎተት ሲጣጣሩ ይስተዋላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ለክህደት እንቅስቃሴዎች የገንዘብ እርዳታ በማድረግ ክህደት ከእስልምና በላይ እንዲያንሰራራ ለማድረግ ይንቀሳቀሳሉ፡፡

🔘 ይህ የጥፋት እንቅስቃሴ በነበሩበት የጥፋት ጎዳና ላይ ድርብ ጥፋት ሆኖ ጉዳት የሚጨምርባቸው መሆኑን ቢገነዘቡ መልካም ነበር። ግና ለዚህ አልታደሉምና ገንዘባቸውን በማፍሰስ እስልምናን የማዳከም ሙከራን ያደርጋሉ፡፡ አላህ ሂዳያ ይስጣቸው!

🔘 ይህን ተግባራቸውን አስመልክቶ አላህ በቁርአኑ በሱረቱል አንፋል 36ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ይለናል፦

🔆 إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ لِيَصُدُّوا عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ فَسَيُنفِقُونَهَا ثُمَّ تَكُونُ عَلَيْهِمْ حَسْرَةً ثُمَّ يُغْلَبُونَ
🔆 እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘባቸውን ያወጣሉ። በእርግጥም ያወጧታል ፣ ከዚያም በእነሱ ላይ ፀፀት ትሆንባቸዋለች! ፣ ከዚያም ይሸነፋሉ!

🔘 ከዚህ አንቀፅ እንደምንረዳው የአላህን ዲን ለማዳከም ገንዘብ ማውጣታቸው ፀፀት ላይ ያደርሳቸዋል፡፡

🔘 ፀፀታቸው በብዙ መገለጫዎች እውን የሚሆን ሲሆን ከነዚህ መካከል እንዳሃሳባቸውና እንደምኞታቸው እስልምናን ማስቆም ባለመቻላቸው የሚደርስባቸው የቁጭት ፀፀት ይገኝበታል።

🔘 እስልምና የአላህ ብርሃን እንደመሆኑ መጠን ሊያስቆሙት የሚቻላቸው አይደለምና ሁሌም እንደበራ ይቀጥላል❗️

🔘 ዋናው ፀፀታቸው የሚሆነው ግን ምናልባትም ወደ እስልምና የመግባት እድሉን ሳያገኙ ሞትን የቀመሱ እንደሆን በገንዘባቸው ይሰሩት የነበረው ስራ በቂያም ቀን ከፊት ለፊታቸው በሚቀርብበት ጊዜ ይሆናል። እንዲህ ያለ የክህደት ድርጊት ደግሞ እሳት ውስጥ መኖርን የሚያስከትል መሆኑ በብዙ ማስረጃዎች ተብራርቶልናል፡፡ ይህንን አስመልክቶ ከላይ የጠቀስነው አንቀፅ መጨረሻ ላይ አላህ እንዲህ ይላል ፦

🔆 وَالَّذِينَ كَفَرُوا إِلَىٰ جَهَنَّمَ يُحْشَرُونَ
🔆 እነዚያም የካዱት ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ!

🔘 ይህ አንቀፅ በዚህ መልኩ የተጠናቀቀው ከእስልምና መንገድ ሰዎችን ለማዘናጋት ገንዘብ የሚያወጡት ሰዎች ከመጠቀሳቸው ቀጥሎ መሆኑ ይህን መሰል ተግባር ላይ ለሚሳተፉ በሙሉ ማስፈራሪያና ዛቻ ያዘለ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በዚሁ የክህደት እንቅስቃሴ ላይ ለሚቀጥሉና የአላህን መሃሪነት ለማይታደሉ ሁሉ የፍፃሜያቸው ትምቢት ሆኖ በቁርአን ላይ ሰፍሮ ይቆያል፡፡

➡️ ማን ከሰረ ታዲያ⁉️

አል-ኢሻራ


Репост из: መወዳ ቻናል(MEWEDA CHANNEL)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ ሲከሰት ❗️

★★★★★★★★★★★★

✨ ይህ አይነት ክስተት ሲከሰት አላህ ባሮቹን የሚያሰፈራራበት ነውና በድንጋጤ ወደ ሰላት፣ዱዓ ወደ ማድረግና ሰደቃ ወደ መስጠት ...ተቻኮሉ ነበር የተባልነው !!!

⚡️ምንኛ ያማረ እምነት 👉ኢስላም
★★★★★★★★★★★★

✨ አይገርምም ክስተቱን እንደመዝናኛ ቆጥሮ ፣የፕሌን ከፍሎ፣ #ላሊበላ ድረስ መሄድ!!!

☀️አላህ አቅላችንን አይገልብጥብን

ይቀላቀሉን 👇👇👇
Http://t.me/MewedaChannel


➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
☘☘ አል-ኢሻራ (ጥቆማ) ☘☘
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
🍀🍀 በግርዶሽ ጊዜ 🍀🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔘 ቁተይባህ ኢብኑ ሰዒድ (رضي الله عنه) በዘገቡት ሐዲስ ድንቁ ነብያችን ነብዩ መሐመድ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን ተናግረዋል፦
💬 "إِنَّ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ آيَتَانِ مِنْ آيَاتِ اللهِ، وَإِنَّهُمَا لَا يَنْخَسِفَانِ لِمَوْتِ أَحَدٍ، وَلَا لِحَيَاتِهِ، فَإِذَا رَأَيْتُمُوهُمَا فَكَبِّرُوا، وَادْعُوا اللهَ وَصَلُّوا وَتَصَدَّقُوا..."

💬 "በርግጥም ፀሀይና ጨረቃ ከአላህ ምልክቶች ናቸው፡፡ እነሱም ለአንድ ሰው ሞት ወይንም ህይወት ሲባል አይጋረዱም፡፡ ባያችኋቸው ጊዜ ተክቢራ አድርጉ (አላሁ አክበር በሉ) ፣ አላህንም ለምኑ ፣ ስገዱም ፣ ምፅዋትንም ስጡ..."

አል-ኢሻራ ቻናል
@yenebiyatwrs


☀️እናታችን አዒሻ (አላህ ስራዋን ይውደድ) ዘንድ የተወሰኑ ሴቶች ስስ ልብስ ለብሰው ገቡ።

✨እንዲህ አለቻቸው ፦ "አማኝ ሴቶች ከሆናቹህ ይህ የለበሳችሁት ልብስ የአማኝ ሴቶች አይደለም።"


تفسير القرطبي ١٤| ٢٤٤ 📂


@yenebiyatwrs

አል—ኢሻራ ቻናል ይቀላቀሉን!!!!


☀️ አላህ (ሱ·ወ) እስልምናን ለኛ እኛንም ለእስልምና በመምረጡ ፤ እሱ ዘንድ ብቸኛው እና ተቀባይነት ያለው ዲን በማድረጉ ምስጋና ይገባው ።

☀️ እስልምናን ለአለም በማድረስ ለተላኩት እና የነቢያቶች መደምደሚያ በሆኑት በ«ሙሀመድ» ላይም የአላህ ሰላም ይስፈን ።

☀️ የሰው ልጆች ከተፈጠሩበት እለት አንስቶ ዓለም እስከምትጠፋበት ቀን ድረስ ሰዎች እንዲጓዙበት ከፈጣሪያቸው የታዘዙበት እምነት * ኢስላም * ነው ።

☀️ ይህ ስርዓት ዱንያ ላይ ለሰዎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ጠቅልሎ የያዘ ከመሆኑም በተጨማሪ፤ በቀጣዩም ዓለም ( በአኺራ) በምንም ሊተመን የማይችል ሽልማትና ደስታ የሚያስገኝ ነው ።

☀️ በተቃራኒው ይህንን ስርዓት ባልተቀበለና ባልተከተለ ላይ ደግሞ ማብቂያም ሆነ እረፍት በሌለው አሳማሚ ቅጣት ይስተናገዳል ።

☀️በሌላ አባባል በሁለመናቸው ሙስሊም ለሆኑ ‘ ጀነት’ ኢስላምን ላልተቀበሉ ደግሞ ‘ ጀሀነም ’ የተባለ ሀገርን ያዘጋጀ ስርዓት ነው ።

☀️ ማንኛውም ሰው "ሙስሊም " ነኝ በማለቱ ብቻ ወይም ደግሞ የሙስሊም ስም በመጠቀሙ ብቻ ‘ጀነትን’ ያገኛል ማለት አይደለም!!!

☀️ በመሆኑም የዱንያንም ሆነ የአኼራን ስኬት ለመቀዳጀት ኢስላም ያዘዘውን መታዘዝ ፣ የከለከለውን መከልከል የግድ ይላል ።

☀️ አላህ (ሱ· ወ) ለሰው ልጆች በየጊዜው #መፅሀፍትን በማውረድ ፣ ነቢያትን በመላክ፣ እነዚህንም ነብያት ትዕዛዛትንና ክልከላዎችን እንዲያስተምሩ በማድረግ በአጠቃላይ የሚድኑበትን መንገድ ያሳያቸዋል ።

☀️ለዚህ ኡመት ( ህዝብ) ደግሞ የቀደሙትን መፅሀፍቶች የሚሽር « ቁርአን» ፤ የነቢያቶች መቋጫ አድርጎ «ሙሀመድን» አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ልኮልናል ።

☀️ አልሀምዱሊላህ ‼ ይህም ማለት የእስልምና ምንጮች « ቁርአን» እና « የታላቁ ነቢይ "ሱና"» ብቻ ናቸው ማለት ነው ።

☀️ ከነዚህ ሁለቱ ምንጮች እንደተገኘው እስልምና ከአምስት [ 5] ነገራቶች የተገነባ ነው ።

እነርሱም ፦
① ከአላህ በቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ ሙሀመድም ( አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ) የአላህ ባርያ( ፍጡር): እና መልዕክተኛው መሆናቸውን መመስከር ፣

② “ሰላትን ” በተከታታይነት መስገድ ፣

③ "ዘካን" መስጠት ፣

④ " ረመዷንን ” መፆም እና

⑤ ለቻለ ሰው “ሀጅን” ማድረግ ናቸው ።

@yenebiyatwrs


•💥"በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል።"
ረሱል ﷺ

« اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِم عَلَى نَبِينَا مُحَمَّد
ْ ﷺ ».
★★★★★★★★★★

« اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ»

📖✏️📜
.
•┈┈• ❀ 🍃🌸🍃 ❀ •┈┈•


🔹የቁርአን ግብዣ 🔹

🎙 khalifah At-Tonaeijy

💎 ሱረቱል ሒጅር

@MewedaChannel


ለአንድ ወር የሚቆይ ልዩ የሸሪዓ ኮርስ በነሲሓ ቲቪ ከዛሬ ሰኔ 9/2012 ከ10: 00 ጀምሮ

💎 ነሲሓ ቁርኣን ቤት 💎

📚ቃዒደቱ ኑራኒያህ

📺 በኡስታዝ ሑሴን ሙንደታ

📚 የቁርኣን ሀልቃ

📺 በኡስታዝ ሚፍታህ ኑሪ

💎 የነብያት ውርስ 💎

📚 ኪታቡ ተውሒድ

📺 በሸይኽ ኻሊድ ዐብዱለጢፍ

📚 ኪታቡ ሰላት

📺 በሸይኽ ኸሊል ሐሚድ ኸሊል

📚 መንዙመቱል ፊቅህያ

📺 በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

💎 ነሲሓ መሰረታዊ 💎

📚 የዓቂዳ ትምህርት

📺 በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

📚 ቀዋዒዱል አርበዓ

📺 በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር

📚 አዱሩሱል ሙሒማህ

📺 በዶ/ር ዐብዱ ኸይሬ

💎 ነሲሓ ለእህቶች 💎

📚 የተፈጥሮ ደም እና ሸሪዓዊ ህግጋቶቹ

📺 በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

📚 የጋብቻ እና ፍቺ ህግጋት

📺 በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

@yenebiyatwrs


⚡️ነብዩ ﷺ አንድ ሰው ለቤተሰቡ አስቦ የሚያወጣው ወጪ እንደ ሰደቃ ይቆጠርለታል።

Http://t.me/yenebiyatwrs


💎የአደባባይ ጥሪ ነብያዊ ትውፊት!💎


☞ነብያት አውነተኛ ወደ ሆነው ቅናቻ ድምፃቸውን ከፍ አርገው በየገበያው፣ በየአደባባዩና ሰው በተሰበሰበበት ስፍራ ሁሉ ጥሪያቸው አጉልተው ያሰሙ ነበር። ይህን የተቀደሰ ጥሪ ከፊሉ ሲቀበል ከፊሉ ይሳለቅበታል። ከፊሉ ጥሪውን ላለመስማት በልብሶቹ ይከናነባል። ከፊሉ ይዘልፋቸዋል ይብስ ብሎም ይገፈትራቸዋል።

☞ይህ ሁሉ የሚደርስባቸው እኔና አንተን የመሰሉ ጫማችን ተረገጠ ብለው "ዘራፍ!" የሚሉ ትንንሽ ስብእናዎች አይደሉም። እጅግ የተከበሩ የአለማቱ ጌታን መድህን ለአደም ልጅ ለማደረስ መርጧቸው ቃሉን በልሳናቸው ላይ ያኖረ ክቡራን ነብያቶች ናቸው።

☞የአደባባይ ሰበካ ጥንታዊ የነብያት ፋና የቅኖች ልማድ ነበር። መለኮታዊ እዝነትን ለፍጡር ያነገበው ጥሪያቸው ዘልቆ ጆሮኣቸው ደርሶ ልቦናቸው ይመሩ ዘንድ ድምፃቸው እረፍት የለውም። ይሰማል።

☞ከገበያው መሀል ሰው ከተሰበሰበበት ሁሉ ሰተት ብሎ ይዘልቃል። "ህዝቦቼ ሆይ! ጌታቹህ አሏህ ነው ከሱ ሌላ እውነተኛ አምላክ የላችሁም!" የምትለው የተውሒድ ቃል ከአንደበታቸው ጎልታ ትሰማለች።

☞ይህቺን ቃል ሸምቶ የመጣ የእውነት ከንግዱ ያተረፈ ስኬታማ ሸማች አልያም ነጋዴ ነው። እነዛ በነብያት ጥሪ የተሞሉ ገበያዎችና አደባባዮች ዛሬ ታሪክ እንጂ ህዋስ አይደርስባቸውም። የድምፆቹ አሻራ በህሊናችን ቢኖርም፣ ፈለጋቸው ቢታየንም ከጆሮኣችን ግን ርቋል። ንግዳቸውም ከስሟል። ለዘልኣለም ያተረፉት የነብያት ጥሪዎችን በቅን ልቦናና በስል ምልከታ የተቀበሉ ትጉኃን ብቻ ናቸው።

☞ከዳንኪራና ዘፈን ከማስታወቂና ክህደት ጩኸት የነብያት ጥሪ የረበሸው ከንቱ ትውልድ ላይ ነህና እንዳያሰናክሉህ!! ድምፅህን የናፈቁ የተዘጉ ልቦች አሉና በአላህ ፈቃድ ትከፍታቸዋለህ።

☞የነብያት ጥሪ ከቧልትና ዛዛታ ይልቅ ከሰዎች ልብ ሰርፃ ትገባለች። ፍሬን ታፈራለች። ያኔ ጆሮን የሚያውኩ ሰይጣናዊ ድምፆች ይተናሉ። ምን አልባት ላይመለሱ ይሸሻሉ። ግና ይህ የነብያት የስብከት ስልት በግዜ ሂደት በሚገጥሙት እክሎችና ድክመቶች እየተመናመነ ሊጠፋ ጫፍ ደርሷል። አንዳንድ ጥቂት ወንድሞች ፋና ወጊ ሆነው ቢጀምሩትም ቅሉ ጠላትን አፍርቷል። ይህ ነብያት የሚገጥማቸው ፈተና ነውና ፅናቱን ተላበሱ። ህዝቤም ይመራልና! ከጨለማው ብርሃን የናፈቀው የሰይጣን ሲሳይ ታገኘዋለህና በርታ።


☞የኑሕ ምዕራፍ የነብያት ጥሪ ታላቁ ማሳያ የተከበረው ቁርአን ምዕራፍ 71!

71) ኑሕ፣ (የኑሕ ምዕራፍ)
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

71:1 - እኛ ኑሕን «ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ሕዝቦቹ ላክነው፡፡»

71:2 - (እርሱም) አለ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ ገላጭ የኾንኩ አስጠንቃቂ ነኝ፡፡

71:3 - «አላህን ተገዙት፣ ፍሩትም፣ ታዘዙኝም በማለት፤ (አስጠንቃቂ ነኝ)፡፡

71:4 - «ለእናንተ ከኀጢኣቶቻችሁ ይምራልና፡፡ ወደተወሰነው ጊዜም ያቆያችኋል፡፡ የአላህ (የወሰነው) ጊዜ በመጣ ወቅት አይቆይም፡፡ የምታውቁት ብትኾኑ ኖሮ (በታዘዛችሁ ነበር)፡፡»

71:5 - (ስለ ተቃወሙትም) «አለ ጌታዬ ሆይ! እኔ ሌሊትም ቀንም ሕዝቦቼን ጠራሁ፡፡

71:6 - «ጥሪየም መሸሽን እንጅ ሌላ አልጨመረላቸውም፡፡

71:7 - «እኔም ለእነርሱ ትምር ዘንድ (ወደ እምነት) በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ፡፡ ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ፡፡ (በመጥፎ ሥራቸው ላይ) ዘወተሩም፡፡ (ያለ ልክ) መኩራትንም ኮሩ፡፡

71:8 - «ከዚያም እኔ በጩኸት ጠራኋቸው፡፡

71:9 - «ከዚያም እኔ ለእነርሱ ገለጽኩ፡፡ ለእነርሱም መመስጠርን መሰጠርኩ

71:10 - «አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡

71:11 - «በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡

71:12 - «በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡»

71:13 - ለአላህ ልቅናን የማትሹት ለእናንተ ምን አላችሁ?

71:14 - በልዩ ልዩ ኹኔታዎች በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲኾን፡፡

71:15 - አላህ ሰባትን ሰማያት አንዱ ካንዱ በላይ ሲኾን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን?

71:16 - በውስጣቸውም ጨረቃን አብሪ አደረገ፡፡ ፀሐይንም ብርሃን አደረገ፡፡

71:17 - አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ፡፡

71:18 - ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል፡፡ ማውጣትንም ያወጣችኋል፡፡

71:19 - አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት፡፡

71:20 - ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ፡፡

71:21 - ኑሕ አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እነሱ አምመጹብኝ፡፡ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ፡፡

71:22 - «ታላቅንም ተንኮል የመከሩትን ሰዎች» (ተከተሉ)፡፡

71:23 - አሉም «አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡

71:24 - «በእርግጥም ብዙዎችን አሳሳቱ፡፡ ከሓዲዎችንም ጥመትን እንጅ ሌላን አትጨምርላቸው» (አለ)፡፡

71:25 - በኀጢኣቶቻቸው ምክንያት ተሰጠሙ፡፡ እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ፡፡ ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የኾኑ ረዳቶችን አላገኙም፡፡

71:26 - ኑሕም አለ «ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው፡፡

71:27 - «አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና፡፡ ኀጢኣተኛ ከሓዲንም እንጅ ሌላን አይወልዱም፡፡

71:28 - «ጌታዬ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ምእመን ኾኖ በቤቴ ለገባም ሰው ሁሉ ለምእመናንና ለምእምናትም ምሕረት አድርግ፡፡ ከሓዲዎችንም ከጥፋት በቀር አትጨምርላቸው፤» (አለ)፡፡

- ተፈፀመ-


✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ


https://t.me/joinchat/AAAAAEq8AN90dYXSHRVgZA


➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
☘☘ ከግጥም ማህደር ☘☘
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
🍀🍀 እውነተኛ ጀግና 🍀🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

እውነተኛ ጀግና - ምድር ላይ ነበረ
ለጌታው ሲዋደቅ - በትጋት የኖረ
ከወንጀል ማዕበል - ነፍሱን እየገታ
ህይወቱን ሲገፋት- ከፅኑዎች ተርታ
ነፍሲያው አረፈች- መበርታቱን አይታ
ማሸነፍ ሲሳናት - ወትውታ ወትውታ

እውነተኛ ታጋይ - ምድር ላይ ነበረ
ሸይጣን እንዳይጥለው - ሲታገል የኖረ
ከጥፋት ለመሸሽ - መፍትሄውን አውቆ
ህይወቱን ሲገፋት - እጅግ ተጠንቅቆ
ሸይጣን ተሸነፈ - ታጋዩን ሰልችቶ
አልሳካ ሲለው - ጎትጉቶ ጎትጉቶ

እውነተኛ ጠቢብ - ምድር ላይ ነበረ
በማስረጃ ጥበብ - ህይወቱን የኖረ
በምራቻ ጉዞ - በርትቶ ሲተጋ
ህይወቱን ሲገፋት - ጀሊልን ፍለጋ
ተደሰተ ጌታው - በዚህ ጠቢብ ኑሮ
ስኬትን ለገሰው - ጨምሮ ጨማምሮ

የሱው ተቃራኒ - እንዲህ ያልበረታ
በነፍሲያ ጥሪ - ልቡ ተወትውታ
ተጎትቶ ቀርቶ - በሸይጣኑ ገመድ
ተይዞ ታሰረ - ተገኝቶ ከወጥመድ
ከዚህ መጠበቂያው - መበርታት ነውና
ራሕማኑ ያድርገን - እውነተኛ ጀግና

🖌 ኢብኑ ሱልጣን አልኢትዮቢ

እርማትና ማስተካከያ
➡️️ ዓብዱረዛቅ አልሐበሺ

ግምገማ
➡️ ኢሻራ የሳንሱርና አስተያየት ክፍል
ሸዋል 22 - 1441

t.me/isharaChannel2

Показано 20 последних публикаций.

2 789

подписчиков
Статистика канала