ከሱቢሂ ቂርአት የተወሰዴ ግብዣ
~
50 ኛው የጃሂሊያ ዘመን ሰዎች መሳኢል በመልዕክተኞች ላይ በተወረደው መፅሃፍቶች መካዳቸውና ማስተባበላቼው !
በጥቅሉ ሲጠቃለል 👇
አላህ እንዲህ ይላል፦
وَمَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ إِذْ قَالُوا مَا أَنزَلَ اللَّهُ عَلَىٰ بَشَرٍ مِّن شَيْءٍ ۗ قُلْ مَنْ أَنزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَىٰ نُورًا وَهُدًى لِّلنَّاسِ ۖ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا ۖ وَعُلِّمْتُم مَّا لَمْ تَعْلَمُوا أَنتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ ثُمَّ ذَرْهُمْ فِي خَوْضِهِمْ يَلْعَبُونَ
«አላህ በሰው ላይ ምንም አላወረደም» ባሉም ጊዜ አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ (እንዲህ) በላቸው፡- «ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፡፡ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ፤» ሱረቱል አንዓም :91
አላህ በነብያት ባወረደው መፅሃፍት በሁሉም በጥቅል ማመን ግዴታ እንደሆነ። በዚህ አለማመን ከእስልምና እንደሚያስወጣ። በስም የተጠቀሱ መፅሀፍት ካሉ በስም ማመን ግዴታ እንደሆነ። በቁርአን ደግሞ በዝርዝር መማንና መስራት ግደታ እንዳለብን ያስረዳል ።
ይሄን ለመካድ የመካ ሙሽሪኮችንና አይሁዶችን የገፋፋቼው ሰበቡ ዋነኛው ምቀኝነታቼው ነው ለሙሀመድ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ያላቼው ምቀኝነትና ለቁርአን ያላቼው ምቀኝነት እንደሆና አሁንም ድረስ የእነሱን አካሄድ እየሄዱ ያሉ እንዳሉ ተዳሷል ።
ስለ ጀህምያዎችም ቁርአን የአላህ ቃል አይደለም ያሉበትንና ከአይሁዶችና ከሙሽሪኮች አካሄድ ውስጥ እንደሆነ ተዳሷል
ሰለምቀኝነት ምንነትም በደምብ ተዳሷል
ምቀኛ ሰው በሂወት እያለ በራሱ ስራ ሲንገበገብ ይኖራል መመቅኜቱን እስካልተወ ድረስ በአኼራም ካልቶበተና ካልተመለሰ ከዚህ የባሰ ነው የሚያጋጥመው ።
አላህ ከምቀኛም ከመመቅኘትም በአዛኙ ጌታችን ይጠብቀን ።
ሙሉውን ከኪታቡ ተመልከቱት !
ሚያዚያ 12/2017
ከሱቢሂ ቂርአት የተወሰዴ
ወሎ_ወረኢሉ_ከፉርቃን መስጅድ
ከኡስታዝ ተውፊቅ ሃፊዘሁላህ የተወሰዴhttps://t.me/YewereiluMuslimWotatoch/5781