በማስተዋል ዘምሩ ✨


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


⚠️ Contact us through our bot: 💬 @zemeru_bot
⚠️ Chat Group: https://t.me/bemastewalzemeru

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


#Update

ዛሬ የካቲት 7 የእግዚአብሔር ሰዉ ቢሾፕ ደጉ ከበደ በከፋ ሸካ ሰበካ አመታዊ ኮንፍራስ ላይ ተገኝተው በቴፒ ሐዋሪያዊት ቤተ-ክርስቲያን ቅጥር ግቢ የተሰራውን የሰበካ ቢሮ መርቀው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚደረገውን መንፈሳዊ ጉባኤ በጸሎት ከፍተዋል።

ምንጭ፦ የቴፒ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን

@zemeru
@zemeru


የሆሳዕና ኮንፍረንስ Live መከታተል የምትፈልጉ Visit 👉 https://www.youtube.com/live/66coGydmJwA?si=8-Lj0rRe7HRnLCSE


New Released Song
የተፈታሁበት ታላቅ ስምህ

የተፈታሁበት ታላቅ ስምህ ይንገስ
የዳንኩበት ስምህ ኢየሱስ ይቀደስ
ሥልጣን ያገኝሁበት ኃይልን የያዘው ስምህ
ይባረክ ለዘላለም አሜን ብሩክ ይሁን

Original song: Hibret 17

Via Salem Spiritual Events

@zemeru
@zemeru
በማስተዋል ዘምሩ Telegram Channel JOIN US for more Updates!

997 0 11 2 18

ጳውሎስ በመልዕክቱ በብዛት "ትንሿ እስያ" ብሎ የሚጠራት አገር በአሁኑ ሰዓት ማን ናት?
Опрос
  •   ሮም
  •   ሶሪያ
  •   ግሪክ
  •   ቱርክ
79 голосов


በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ በመጽሐፍ እውቀት የበረታ ሰው ነበር የተባለው ማን ነው?
Опрос
  •   በርናባስ
  •   አጵሎስ
  •   ሲላስ
  •   አግርጳ
70 голосов


እስራኤላውያን ለ70 አመታት ወደ ባቢሎን ተማርከው እዚያው በምርኮ አገር ሳሉ እግዚአብሔር ወደ እነሱ የላካቸው ነቢይ ማነው?
Опрос
  •   ኤርምያስ
  •   ኢሳይያስ
  •   ሕዝቅኤል
  •   ሚክያስ
79 голосов


በመሳፍንት ዘመን እስራኤላውያን ከገዛ ወንድሞቻቸው ጋር ባደረጉት ጦርነት ልጠፋ ደርሶ በእግዚአብሔር ምህረትና ለአባቶቻቸው ከገባው ቃልኪዳን የተነሳ ከመጥፋት የተረፈው ነገድ የማን ነገድ ነበር?
Опрос
  •   የዳን
  •   የይሁዳ
  •   የሮቤል
  •   የቢንያም
76 голосов


በእስራኤል ነገስታት ታርክ ውስጥ በሴት የተመራ ንጉስ የተባለው ማን ነበር?
Опрос
  •   አሞጽ
  •   ኢዮርብዓም
  •   አካዝያስ
  •   አክዓብ
100 голосов


"መንገድህንና ትንፋሽህን በእጁ የያዘውን አምላክህን አላከበርክም" የተባለው ንጉስ ማን ነበር?
Опрос
  •   ሳኦል
  •   ናብኩደነጾር
  •   ብልጣሶር
  •   አክዓብ
107 голосов


በብሉይ ኪዳን ዘመን የእስራኤልን ሕዝብ ሀጢያት ለማስተሰረይ በአመት አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚገባው ማነው?
Опрос
  •   ሌዋዊ
  •   ከህዝቡ የተመረጠ አንድ ሰው
  •   ሊቀ ካህን
  •   የእስራኤል ነገድ አለቆች
118 голосов


ከእነዚህ መካከል አንዱ በጳውሎስ የወንጌል ጉዞ ላይ ከእርሱ ጋር አልነበረም።
Опрос
  •   ፊልጶስ
  •   ሲላስ
  •   ጢሞቴዎስ
  •   ቲቶ
122 голосов


ልጁ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናል የተባለው ማን ነው?
Опрос
  •   መጥምቁ ዮሐንስ
  •   ሙሴ
  •   ኤልያስ
  •   ሳምሶን
135 голосов


ኢየሱስ "በእውነት ተንኮል የሌለበት የእስራኤል ሰው" ያለው ማንን ነበር?
Опрос
  •   ፊልጶስን
  •   ናትናኤልን
  •   ኬፋን
  •   ዮሐንስን
151 голосов


ኢየሱስ የነጎድጓድ ልጆች ብሎ የጠራቸው እነማንን ነው?
Опрос
  •   ጴጥሮስና እንድርያስ
  •   ጳውሎስና በርናባስ
  •   ዮሐንስና ያዕቆብ
  •   ፊልጶስና ቶማስ
25 голосов


የዛሬው እለት የማጠቃለያ በረከት ቃል በወንጌላዊ ደረጀ ከበደ!


በሆሳዕና ከተማ አደባባይ

አንድ አምላክ ኢየሱስ ሲከብርም


WARA BETHEL 2025


የመሐል ሲዳማ ቅርጫፍ ሰበካን ልዩ ከሚያደርጉት አንዱ ከመላ አገሪቱና ከአለም ዙሪያ የሚመጡ ምዕመናን የሚሳተፉበት ታላቁ አለም አቀፍ ጉባኤ የሚካሄድበት ሰፊው የዋራ ሜዳ የሚገኝበት መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በዚያ ሜዳ ላይ በብሎኬት የታጠረ ሰፊ ቦታ አላት፤ በቦታው የኮንፍራንስ ማዕከል ተገንብቶ አለም አቀፍ ጉባኤ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በየአመቱ እየተካሄደ ይገኛል።

ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሲሄድ ድንጋይ ተንተርሶ የተኛበትን "ሎዛ" የምትባለውን ስፍራ እግዚአብሔር ተገልጦለት ካነጋገረው ቦኃላ ይህ የእግዚአብሔር ደጅ ነው ስል "ቤቴል" ብሎ እንደጠራት፣ እንዲሁ በዋራ አከባቢ እግዚአብሔር እራሱ እንዲመለክበት በደሙ ለዋጃት ቤተከርስቲያን አሳልፎ ሰጥቶ በዚያ ስፍራ እውነቱን ስላበራ ቤተክርስቲያን "ዋራ ቤቴል" ብላ ጠራችው።

የዋራ ኮንፍረንስ ማዕከል በኢየሩሳሌም ከተማ ምሳሌ የተሰራ ቅጥርና መሰረት አለው። ቅጥሩ አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ሆኖ በአራቱም አቅጣጫ እያንዳንዱ ሶስት ሶስት በሮች በድምሩ አስራ ሁለት በሮች አሉት። የዋራ ቤቴል የኮንፍራንስ ማዕከል 12 ትላልቅ ሼዶች የተገነቡለት የተንጣለለ ሰፊ ሜዳ ነው።

ከመጋቢት 5 ቀን 1984 ዓ.ም ጀምሮ ህዝቡን በበረከትና በምህረት እየጠበቀና እየጎበኘ፣ በድንቅና የሰው ልብና አዕምሮ ልገምተው ከምችለው በላይ ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ያከናወነበት ዋራ ቤቴል የአምላካችን የእግዚአብሔር ተአምራት የሚገልጽ ነው።

ዋራ ሜዳ ላይ የማያቋርጥ ሃሌሉያና እልልታ በሽብሸባ ታጅቦ አስተጋባ። ግማሹ ይሰግዳል፣ ግማሹ ያመሰግናል፣ ሌላው ኢየሱስ እያለ ይጮሃል፤ እጆቹ ተዘርግተው ሞትን ለዘላለም የዋጠውን ኢየሱስን ያመሰግናሉ። ከኢየሱስ ፈውስ፣ በረከትንና ምህረትን የሚሹ ሁሉ ኢየሱስን ዝቅ ብለው፣ ሜዳ ላይ ተንበርክከው እንዲሰማቸው ይማጸኑታል።

በዚህ የሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን የሰማይ መላዕክት ጭምር በተገኙበት ቢሾፕ ተክለማርያም ገዛኸኝ "ኢየሱስ በመካከላችን ነውና ምስጋናን አታቋርጡ" ብሎ ሲናገር የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በዋራ ቤቴል ፈሰሰ። በህመም ስሰቃዩ የነበሩ ተፈቱ፣ "አምላኬ ዛሬስ አያልፈኝም የእስራቴን ገመድ ይበጥሳል" ብለው የሚጠብቁ ነፍሳት ዘመናትን በአጋንንት እስራት ያሳለፉ ተፈትተው ለምስጋና እጃቸው ሲዘረጉ ታየ።

እግዚአብሔር የጠራው ጉባኤ ለመሆኑ መንፈሱን እያፈሰሰ በደዌና በሕመም የታሰሩትን እየፈታ በዋራ ቤቴል አምላካችን በሕዝቡ መካከል እንደነበረ መሰከረ።

በብሉይ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔር ህዝብ አንድም ሳይቀር በእግዚአብሔር ፊት ሊታይ ከነቤተሰቡ ይወጣ እንደነበርና እግዚአብሔርም ለህዝቡ ህጉን ያስተምርና ይባርክ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክርልናል።

ዛሬም በአዲስ ኪዳን የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ሕዝቡን በጉባኤ ሰብስቦ መንፈስ ቅዱስ እያፈሰሰ ሲባርክና የደመና ዓምድ ሲያወርድ የሚታይበት ጉባኤ አዘጋጅቷል።

ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምስራቅና ከምዕራብ የሃገሪቱ ክፍሎች የተሰበሰቡ በደሙ የተዋጁ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራበት ስም ሁሉ በላይ የሆነውን የታላቁን የአምላካችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እየጠሩ በፊቱ ሲሰግዱና ሲዘምሩ፣ በደዌና በአጋንንት የታሰሩ ሲፈቱ፣ ያየንበት፣ ከዚህ ጨለማ ዓለም አንዱን አምላክ ከምያስክድ ክፉ ትምህርት ሰዎች በንስሐ ሲመለሱ የታየበት ድንቅ ጉባኤ ነው።

ብቻውን በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ያለውን አንዱን አምላክ በአንድ ልብና በአንድ መንፈስ ከተሰበሰበ ህዝብ ጋር ማምለክ ምንኛ መታደል ነው! ህዝቡም በአንድ ልብ እጁን ዘርግቶ በመካከሉ ያለውን አምላክ ሲያመሰግን ማየትም ነፍስን በሃሴት የሚሞላ ድንቅ ትዕይንት ነው። እግዚአብሔር የሚገለጥበት ጉባኤ!!

ለ34ኛው ዋራ ቤቴል አለማቀፍ ኮንፍረንስ እንኳን ጌታ ኢየሱስ በሰላም በጤና አደረሰን! ጉባኤም ከመጋቢት 5-7/2017 ዓ.ም ይካሄዳል። ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ተጋብዛችኋል።

@zemeru
@zemeru
በማስተዋል ዘምሩ Telegram Channel JOIN US for more Updates!




ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ 100 የእግዚአብሔርን ነቢያትን በዋሻ ደብቆ በየእለቱ እንጀራና ውሃ እየሰጠ እነዚያን የእግዚአብሔርን ነቢያትን የመገበ የአክዓብ የቤቱ አዛዥ፣ ያ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ይባላል?
Опрос
  •   አብድዩ
  •   አቤሜሌክ
  •   ባሮክ
  •   አቤኔር
6 голосов


ጢሞቴዎስ ማን ነው?


◉ ጢሞቴዎስን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚናገኘው በሐዋ 16፡1-5 ነው፤ ያደገው ደግሞ ልስጥራን በምትባል ከተማ ነው፡፡

◉ አባቱ የግሪክ ሰው፣ እናቱ አይሁዳዊት ነበረች። በእናቱ ኤውንቄና በአያቱ ሎይድ በኩል የብሉይ ኪዳንን ተምሯል (2ኛ ጢሞ 1፡ 5፤ 2ኛ ጢሞ 3፥14-15)፡፡

◉ ጢሞቴዎስ የጳውሎስ አጋዥ ነበር፡፡ ለ15 ዓመታት ከጳውሎስ ጋር አብሮ ሲያገለግል ነበር፡፡

◉ ጢሞቴዎስ ወጣት ቢሆንም እንኳ ጠንካራ የቤተ ክርስቲያን መሪ ሊሆን እንደሚችል ጳውሎስ ስለተረዳ ይዞት ለመዞር ፈለገ፡፡ ሆኖም ጢሞቴዎስ በእናቱ ምክንያት አይሁዳዊ ቢሆንም፤ ካልተገረዝ በቀር በአይሁዶች ዘንድ ተቀባይነት ስለማይኖረው ገረዘው፡፡

◉ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያጽናና በመጀመሪያ ወደ ተሰሎንቄ ተላከ (1ኛ ተሰ 3፥2)። ከዚያም ወደ መቄዶንያና ወደ ቆሮንቶስ ተላከ (1ኛ ተሰ 3፥4-7)። ከዚያም የተሰበሰበውን የእርዳታ ገንዘብ ይዞ ከጳውሎስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ (ሐዋ 20፡4)፡፡

◉ ጳውሎስ የፊልጵስዩስንና የቄላስያስን መልዕክቶች ሲጽፍ ጢሞቴዎስ አብሮት ነበረ (ፊል 1፥1፤ ቄላ 1፥1)፡፡

◉ ጳውሎስ ሁለቱን መልዕክቶችን ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ እርሱ በኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያገለግል ነበረ (1ኛ ጢሞ 1፡3)፡፡

◉ ጢሞቴዎስ ባልታወቀ ጊዜ ታስሮም ነበር (ዕብ 13፡23)

◉ ጢሞቴዎስ የጳውሎስ ታማኝ ረዳት በመሆን እስከ መጨረሻው ጸንቶ የክርስቶስን ወንጌል በታማኝነት አብሮት አገለገለ፡፡

@zemeru
በማስተዋል ዘምሩ Telegram Channel JOIN US for more Updates!

Показано 20 последних публикаций.