#መልካምአዲስ
“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።”
— መዝሙር 65፥11
ለሁላችሁም በዓሉ የሰላም የፍቅር ይሁንላችሁ እንዲሁም ቅዱስ ቃሉ እንደሚነግረን👇 አዲሱን ዓመት ስንቀበል በአዲስ መንፈስ ይሁን ጌታም አዲስ ልብ ይሰጠናል እንዲሁም አዲሱን ዓመት ስንቀበል ኢየሱስን መልበስ ይገባናል።
“አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።”
— ሕዝቅኤል 36፥26
በሉ እንደባህላችን ክርስቲያናዊ ምርቃን ልመርቃችሁ😁
በአዲሱ ዓመት ክርስቲያናዊ ፍሬ አፍሩ።
በአዲሱ ዓመት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የባህሪይ አባቱ የእግዚአብሔር አብ ፍቅር እንዲሁም የባህሪይ ሕይወቱ የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ፍቅር ይብዛላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን የምትወዱበት ዓመት ይሁንላችሁ በእርግጥ አምላኩን የማይወድ ክርስቲያን የለም ነገርግን የቃሉ ባለቤት ክርስቶስ ኢየሱስ እንደነገረን እሱን መውደድ ፍቃዱን መፈፀም ነው ስለዚህ አዲሱ ዓመት የሥላሴን ፍቃድ የምትፈፅሙበት ይሁንላችሁ።
“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”
— ዮሐንስ 14፥15-16
በአዲሱ ዓመት የጌታን ስጋና ደም ለመቀበል ያብቃችሁ።
ጌታ በአዲሱ ዓመት ኃጢያትን ለመስራት የደነደነ ልብ ፅድቅን ለመስራት የበረታ የጠነከረ ልብ ያድላችሁ።
በአዲሱ ዓመት ጌታ ጸሎት ወዳድነትን፣ጥበብን፣ማስተዋልን፣ ትዕግስትን ያድላችሁ እንዲሁም ሰዉንሁሉ የሚወድ ልብ ይስጣችሁ።
አዲሱን ዓመት በማንበብ በክርስቲያናዊ ስራ እንድታሳልፉ ጌታ ይርዳችሁ።
#አሜንበሉ😁
#ማሳሰቢያ
በዓሉን ስታከብሩ ክርስቲያናዊ በሆነ መንገድ አክብሩ መስከር መጨፈር ክርስቲያናዊ ትውፊት አይደለም።
"ጌታሆይ ሰላምን ስጠን እንዲሁም ከጠላታችን እጅ አድነን...ጌታሆይ በርህራሄህ ወንዞችና ምንጮችን ዛፉንና ፍራፍሬውን ባርክ ዓውደ አመቱን ባርክልን" (Doxology for the coptic new year) የአስክንድርያ ቤተክርስቲያን ምእመናንም ነገ አዲስ ዓመትን ያከብራሉ በዓሉን ሲጠሩትም በዓለ ናይሩዝ (The feast of nayrouz) ብለው ነው😊ለነገሩ በግብፅ ያለችውን ቤተክርስቲያን ለአብነት አነሳሁ እንጂ መስከረም ፩ (1) የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም አዲስ ዓመቷን የምታከብርበት ነው በዓሉንም (church new year) ብለው ያከብሩታል ለሁላችንም መልካም በዓል
@APOSTOLICsuccession