በደቡብ ኮሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ
የጀጁ አየር መንገድ ንብረት ነው የተባለው አውሮፕላኑ ቦይንግ ስሪት ሲሆን 175 መንገደኞችን ጭኖ ከታይላንድ ወደ በመጓዝ ላይ ነበር
ቦይንግ ሰራሽ የሆነው የጀጁ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የበረራ መስመሩ 7ሲ2216 የተሰኘ አውሮፕላን በደቡብ ኮሪያ ተከስክሷል።
ቦይንግ 737-800 ስያሜ ያለው አውሮፕላኑ 181 መንገደኞችን ከታይላንድ ባንኮጭ ጭኖ እየበረረ እያለ ሙዓን ኤርፖርት ለማረፍ ሲሞክር ተከስክሷል ተብሏል።
እስካሁን በወጡ ቅድመ ሪፖርቶች መሰረት 28 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ሁለት ሰዎች ደግሞ በህይወት ተርፈዋል ተብሏል።
የደቡብ ኮሪያ የአደጋ ጊዜ ተቋማት በአውሮፕላኑ ውስጥ ተጨማሪ መንገደኞችን ህይወት ለመታደግ እየጣሩ እንደሆነ የሀገሪቱ ዜና ወኪል ዮናፕ ዘግቧል።
ጀጁ አየር መንገድ እስካሁን ስለ አደጋው መግለጫ ያላወጣ ሲሆን በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል።
ቦይንግ እና የአሜሪካ አቪዬሽን በደቡብ ኮሪያ ስለተከሰከሰው የአውሮፕላን አደጋ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
@Addis_Reporter