የተሽከርካሪ አስመጪዎች በአዲስ የጥራት ደረጃ ሰርተፍኬት ላይ ቅሬታቸውን አቀረቡ
👉 መንግስት በበኩሉ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል
የኢትዮ ተሸከርካሪዎች አስመጪ ባለቤቶች ማህበር አባላት መንግስት ባስቀመጠው አዲስ የጥራት ደረጃ ሰርተፍኬት ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን መቸገራቸውንና ይህም በሀገሪቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል።
ማህበሩ አባላቱ በአንድ ተሽከርካሪ እስከ 200 ዶላር ወጪ እያወጡ መሆኑንና ይህም ከፍተኛ የዲሜሬጅ ወጪን እንደሚያስከትል እንዲሁም ይህ ሁሉ ገንዘብ ለጎረቤት ሀገር መከፈሉ አግባብነት እንደሌለው ትላንት የካቲት 13፤2017 ዓ.ም. በደብዳቤው አስታውቋል።
በተጨማሪም መንግስት አዲሱን የጥራት ደረጃ ሰርተፍኬት ተግባራዊ በማድረጉ ቀረጥና ታክስ ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩንና ይህም ሀገሪቱን እየጎዳ መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።
@Addis_Reporter