Репост из: Bank of Abyssinia
ለተከበሩ የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮን
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር ኢካገባ/ምዳ/019/17 በጻፈው ደብዳቤ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 መሰረት በሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች የተያዙ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤትነት መዝገቦች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት በሚዘጋጅ ባለቤትነት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በሚመዘገብበት የሂሳብ መዝገብ ስርዓት መተካት ያለበት በመሆኑ፤ ይህንን ለመፈጸም እንዲቻል የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤቶችን (የባለአክሲዮኖችን) መረጃ እስከ ታህሣስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ዝግጁ እንድናደርግ አሳውቆናል፡፡
በመሆኑም፣ የፋይዳ ልዩ ቁጥርዎን (FIN)፣ የብሔራዊ መታወቂያዎን ኮፒ፣ የአድራሻ ለውጥ አድርገው ከሆነ አዲሱን አድራሻ፣ ኢ-ሜል፣ ስልክ ቁጥር፣ የቤት ቁጥር፣ ወረዳ፣ ክ/ከተማ፣ ከተማ፣ ክልል እና ሀገር፤ ባለአክሲዮኑ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የወኪሉ ሰው ሙሉ መረጃ በዋናው መ/ቤት 8ኛ ፎቅ አክሲዮን እና ኢንቨስትመንት ክፍል እንዲያሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
#አቢሲንያ_ባንክ #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ