Репост из: Commercial Bank of Ethiopia - Official
CBE POS USERS PRIZE WINNERS LIST.pdf
ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
**********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለፖስ ተጠቃሚዎች ያዘጋጀው የሽልማት መርሀ ግብር የመጀመሪያ ዙር ዕጣ ወጣ፡፡
• እስከ ጥር 27 ቀን 2017 በባንካችን ፖስ በመገበያየት የ10 ሺ ብር ዕድለኛ ይሁኑ!
*****************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለፖስ ተጠቃሚዎች ያዘጋጀው የሽልማት መርሀ ግብር የመጀመሪያ ዙር ዕጣ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የብሄራዊ ሎተሪ ተወካይ፣ የባንኩ ሠራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ወጥቷል፡፡
ዕጣውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወጋየሁ ገብረማሪያም እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አውጥተዋል፡፡
የገና እና የጥምቀት በዓላትን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው እና ከታህሳስ 21 እስከ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆየው ይህ የሽልማት መርሀ ግብር ከብር 1,000 ጀምሮ በፖስ የሚገበያዩ 315 ደንበኞችን የ10 ሺ ብር ባለዕድል የሚያደርግ ነው፡፡
አሁን በወጣው ዕጣ ከታህሳስ 21 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በፖስ ከተገበያዩ እና መስፈርቱን ካሟሉ ደንበኞች መካከል 29 ተሸላሚዎች ተለይተዋል፡፡
ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን፣ በዛሬው ዕለት በባንኩ የተገኙ ዕድለኞች ሽልማታቸውን የተረከቡ ሲሆን፣ ቀሪ አሸናፊዎች ባንኩ በሚያሳውቃችሁ አድራሻ መሠረት ሽልማታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ እስከ ጥር 27 ቀን 2017 በባንካችን ፖስ በመገበያየት የሽልማት ዕድለኛ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የአሸናፊዎችን ዝርዝር ከተያያዘው መረጃ ይመልከቱ!