እግዚአብሔር ምርጫን የሚፈቅድልን፣ እያንዳንዱን የመንፈስ ፍሬ በተቃራኒ ሁኔታ በመጠቀም ነው። መጥፎ ለመሆን ተፈትነህ የማታውቅ ከሆንክ፣ጥሩ ሰው ነኝ ለማለት አትችልም። ታማኝነትህን በሚፈትን አጋጣሚ ውስጥ ካላለፍክ፣ ታማኝ ነኝ ማለቱ ይሳንሃል። ሀቀኝነት፣እምነት የማጉደል ፈተናን በማሸነፍ ይገነባል፣ ትህትና የሚያድገው ደግሞ መታበይ አሻፈረኝ ሲባል ነው። ጽናት የሚያድገው ተስፋ ቆርጠህ እንድትተወው ለሚያደርግህ ፈተና የማትበገር በሆንህ ጊዜ ሁሉ ነው። አንድን ፈተና ድል ባደረግህ ጊዜ ሁሉ ይበልጥ ኢየሱስን እየመሰልክ ትሄዳለህ።
መልካም ምሽት !
እወዳችኋለሁ!❤❤
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY