የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ኢንደስትሪ ክትትል የሥራ ክፍል አገልግሎት፤
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ /SME/ ኢንዱስትሪ ክትትል ዳይሬክቶሬት ባንኩ ካላቸው ክላስተሮች አንዱ ሲሆን፣ ከዋናው መሥሪያ ቤት ከሚገኙ የኮርፖሬት አበዳሪ ክፍሎች ውጪ ያሉትን 101 ቅርንጫፎችና 24 ዲስትሪክቶች ስር ያሉ ሥራዎችን ያስተባብራል፤ ክትትል ያደርጋል፡፡
የሥራ ክፍሉ ዳይሬክተር አቶ ጌታሰው ፈንታው እንደገለጹት ክፍሉ በዋናነት ክትትል የሚያደርገውና የሚያስተባብረው አምራች ኢንዱስትሪ እንዲሁም ማእድንና ኤነርጂ ዘርፉን ጨምሮ ሁሉንም የዲስትሪክትና የቅርንጫፎችን እንቅስቃሴ ነው፡፡ በተጨማሪም የመመሪያ፣ የፖሊሲና የአሠራር ሥርዓት ክፍተቶችን ከሚመለከታቸው የባንኩ የበላይ አመራሮች ጋር በመነጋገር ሰነዶችን የማዘጋጀት፣ የአሠራር ስርዓቱን ግልፅ የማድረግ ስራዎች ይሰራል፡፡
ሁሉም ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በባንኩ አቅጣጫ መሰረት ተመሳሳይ በሆነ አሰራር አገልግሎት እንዲሰጡ ክትትል የማድረግ፣ ሁሉም አካባቢ ላይ የባንኩ ስራ ፍትሃዊ በሆነ አሰራር እየተከናወነ መሆኑን የማረጋገጥ፣ ሁሉም የባንኩ ቅርንጫፍና ዲስትሪክቶች በአካባቢያቸው ካሉ የባለድርሻ አካላትና ደንበኞች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራቸው ክትትል የማደረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
በተጨማሪም ሌሎች ተቆጣጣሪ አካላት በሚያስቀምጡት መስፈርት መሰረት ስራዎች መሰራታቸውን ክትትል ማድረግ፣ ደንበኞች በቅርንጫፍና ዲስትሪክቶች ላይ ቅሬታ ሲኖራቸው በባንኩ የቅሬታ አቀራረብ መመሪያ መሠረት ቅሬታቸውን እንዲያቀርቡና እንዲፈታ ክትትልና ድጋፍ ማድረግም የዚህ ዳይሬክቶሬት ኃላፊነት ነው፡፡
የዲስትሪክት ክትትል ዳይሬክቶሬት ብድር የፀደቀለት ደንበኛ ግዢዎችን በሚፈጽምበት ሰዓት ከግዥ ክፍል ጋር በመነጋገር ግዢው በተያዘለት ጊዜ በትክክል መፈፀሙን ክትትል ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ የሥራ ክፍሉ አሁን ላይ ከ1680 በላይ ለሚሆኑ የባንኩ ደንበኞች ክትትልና የማስተባበር ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
ሌላው በዳይሬክቶሬቱ የሚሰራው ቁልፍ ስራ የNPL /የተበላሸ ብድር ምጣኔ ቅነሳ/ ሲሆን የዲስትሪክትና የቅርንጫፍ ተበዳሪዎች ውስጥ ብድሩን በወቅቱ ያልከፈሉትን በመለየት ዲስትሪክት እና ቅርንጫፎች ተከታትለው ከባንኩ ጋር በገቡት የውል ስምምነት መሰረት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ብድራቸውን እንዲከፍሉ ክትትል ያደርጋል፡፡
ክፍሉ ከዲስትሪክትና ቅርንጫፎች ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ያለው ሲሆን ባንኩ ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ስራዎች መሠራታቸውን በመከታተሉ የባንኩ ስራ ስኬታማ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ደንበኞች ወደ ዳይሬክቶሬቱ ሲመጡ የሚፈልጉት አገልግሎትም ሆነ መረጃ በተገቢውን መንገድ አግኝተው ተደስተውና አመስግነው እንዲሄዱ ብርቱ ጥረት በማድረጋቸው ከደንበኞች ወደ ዳይሬክቶሬቱ የሚመጡ ቅሬታዎች እንዲቀንሱ አስችሏል፡፡
ደንበኞች ወደ ባንኩ ሲመጡ መጀመሪያ ስለባንኩ አሰራር ግልፅ የሆነ መረጃ እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ከባንኩ ምን እንደሚፈልጉ፣ ምን ምን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው፣ የብድር አገልግሎቱን ለማግኘት ምን ዓይነት ሂደቶችን ማለፍ እንዳለባቸው የተሟላ መረጃ እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡ በተቻለ መጠን የሚጠበቅባቸውን ማስረጃዎች /documents/ አሟልተው እንዲመጡ ይጠበቃል፡፡ በተሰጠው መረጃና በተደረገለት ማብራሪያ መሰረት የሚጠበቅበትን አሟልቶ የተገኘ ደንበኛ የባንኩን አገልግሎት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ማግኘት ይችላል፡፡
ከዚህ ባለፈ ደንበኞች በአሠራር ላይ ግርታዎች ካሉ ግልፅ ያልሆኑ መረጃዎች ካጋጠሟቸው ወደ ባንኩ በአካል በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!