ማልከም ኤክስ - ሙሉቀን ታሪኩ.pdf
📔የመፅሐፍ አርዕስት - የማልከም ኤክስ የህይወት ታሪክ
📔📚የተፃፈበት ዘመን (የተረጎመበት ዘመን) - 2013
©📄የገፅ ብዛት - 501
🎤ደራሲ - አሌክስ ሃሌ
✔️ የነጭ የበላይነትን አብዝቶ የሚቃወመው ማልከም ኤክስ በነጭ ጉዳይ ለዘብተኛ የሆነው መካ ከሄደ ጀምሮ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በዚያ ጊዜ ያያቸው ነጮች ፍፁም ወንድማዊ የሆነ ቀረቤታቸው ነበር። እስልምና ይሄን የወንድማማቾች ድልድይ እንደገነባ ይምናል። በዚያ ጊዜ ያያቸው ነጭ ሙስሊሞች ፍፁም ንፁህ ወንድም ነበሩ።
✔️ ከስምንተኛ ክፍል በላይ ያልተማረው ማልከም ኤክስ በጥቁሮች ትግል ውስጥ ከፍተኛ ተፅኖ አድርጓል። ሰብአዊነቱን ከመለኮት ጋር አሰነሳሎ ያየው በነበረው ኤልያስ ሞሃመድ ተክዷል። ይህንንም ሲገልፀው "ሰውን የመለኮት ፀጋ ባለቤት ማድረግ ስህተት ነው" ይላል። ትልቅ እምነት ነበረው - በእሱ።
✔️እስር ቤት በሆነበት አስቸጋሪ ጊዜያት ሞሃመድ ኤሊያስ ነበር ከጥልቅ የብቸኝነት ጉድጓድ የታጣለውን ማልከም ያነሳው። ምናልባት ትልቁ ስህተት ያ ነበር። ማልከም ኤክስ "በኔሽን ኦፍ እስላም" ማህበር ውስጥ መምህር ሆኖ አገልግሏል።
✔️ከዚያ በፊት ግን ፍፁም ሊታመን የማይችል - አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ፣ ሌባ እና የጎዳና ማፊያ ነበር። "ለውጥ የሚፈልግ እስር ቤት ጥሩ መለወጫው ነው" የሚለን ማልከም ኤክስ በእርግጥም የተቀየረውም እስር ቤት ውስጥ ነበር። በመጀመሪያ ከፍተኛ የንባብ ጊዜ አገኘ።
✔️ በዚህም ነገሮችን ማስተዋል፣ ህይወቱን መመርመር ቀጠለ። በዚህ ሂደት ውስጥ ነበር በወንድሙ አማካኝነት እስልምናን የተዋወቀው። ከዚያ ህይወት ውስጥ ጎትቶ ያወጣ በእርግጥ እስልምናና ንባብ ነበር። የማልከም ኤክስ ታሪክ ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ ድንቅ መፅሃፍ ይመስለኛል።
✔️ለክርስትና የነበረው አመለካከት አደናጋሪ ነው - ማልከም ኤክስ። ነጮች ክርስትናን ዘረኝነት ለማስፋፋት፣ ጥቁር ለመጮቆንና ጥቁር ሰማያዊ መና ብቻ እንዲጠብቅ እጁን ጠምዝዘው አስገድደውበታል ብሎ ያምናል።
✔️ነጮች ጥቁሮች ላይ የፈፀሙት ግፍ በቃ ሊባል እንደሚገባ ያስተምራል። ከ "ኔሽን ኦፍ እስላም" ከታገደ በዃላ የራሱን ማህበር አቋቁሞ ለጥቁሮች መንቀሳቀስ ጀመረ። የታገደበት ዋና ምክንያት በ ኬኔዲ ግድያ ዙሪያ "ሰው የዘራውን ያጭዳል" ብሎ በመናገሩ ነበር።
🎤 ማርቲን ሎተር ኪንግ የማልከም ንግግር "ጥቁርን እያሰቃየው ነው" ብሎ ቢናገርም ማልከም መተዋወቅ እንደሚፈልግ አልደበቀም። በሁለቱ መሃል ያለው ልዩነት የሰላማዊ ትግል እና የሁከት ትግል (ትጥቅ ትግል) ነበር። ማልከም "ነፍጥን ለማስጣል ነፍጥ ማንሳት ተገቢ ነው" ብሎ ያምናል።
✔️አንድ ጊዜ ነጭና ጥቁር ጥንዶች የያዘ መኪና አጠገቡ ቆሟል። መስታወቱን አውርዶ ማልከም ኤክስን እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል:-
"ነጭን ለመጨበጥ ፍቃደኛ ነህ?"
"የሰው ልጅን ለመጨበጥ ፍቃደኛ ነኝ። አንተ የሰው ልጅ ነህን?" ብሎ ነበር ጥያቄውን በጥያቄ የመለሰው።
የማልከም ኤክስ ታሪክ ከአስገራሚነት ያለፉ አስደንጋጮችም ናቸው። ይሄን ሲያረጋግጥልን ስለ እራሱ እንዲህ ይለናል:-
"በአሜሪካ እንደ እኔ እጅግ በዘቀጠ ማህበራዊ ኑሮ ሁኔታ ያለፈ ሰው ማግኘት አይቻልም። የሕይወትን መራራ ፅዋ እንደ እኔ የተጎነጨ ሌላ ሰው መኖሩን እጠራጠራለሁ። ይሁንና ጥልቅ በሆነ ጨለማ የቆየ ሰው ብርሃንን ማጣጣም ይችላል። እስራትና ባርነትን ያየ ሰው ብቻ በሚመጣው ነፃነት ከወዲሁ ሐሴት ያደርጋል።"
"በድርጊት ከሚገለፅ ድንቁርና በላይ አስፈሪ ነገር የለም" የሚለን ማልከም ህይወቱን ሊሰጥ በተዘጋጀላቸው ታጣቂዎች በአስራ ስድስት ጥይት ተመቶ ሞተ።
አሟሟቱ በምፀት የተሞላ ነው። ለጥቁሮች ያደረገውን ትግል ላየ የዚህ ሰው አሟሟት በእርግጥ ያሳዝናል። አባቱንና አጎቶቹን በጥቃት የተነጠቀው ማልከም በመጨረሻም እንዲህ ይላል:-
"እኔም አንድ ቀን በጥቃት እንደምሞት እርግጠኛ ነበርኹ። የአቅሜን ያህል ተዘጋጅቼ ሞቴን ጠብቄያለሁ።"
⭐⭐@Enmare1988