አባ መዓዛ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትምህርት በቂ ችሎታ አላቸው ከሚባሉ መምህራን አንዱ ናቸው፡፡ እኒህ የቤተክርስቲያን ሊቅ ዕውቀታቸውን በበለጠ በዓለም ዐቀፍ ቋንቋ ለማሻሻል ባላቸው ፍላጎት መሠረት ወደ ኢየሩሳሌም አንግሊካን ቤተክርስቲያን ሴንት ጆርጅ ኮሌጅ ተላኩ፡፡ ወደፊት ጵጵስና የሚሾም ብለው ጃንሆይ በተናገሩት መሠረት የኤጲስ ቆጶስነት ትምህርት እንዲሠለጥኑ ነበር የተላኩት፡፡ ሁለት ዓመት ተኩል የቤተክርስቲያን አስተዳደር (Church History and Administration) ተምረው ተመለሱ፡፡ ከውጭ ሀገር እንደተመለሱ ከ1951-1960 ዓ.ም በተማሩት ትምህርት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የካህናት አስተዳደሪ ሆነው ቤተክርስቲያንን በማገልገል ምእመናንን በማስተማር ሐዋርያዊ ግዴታቸውን ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡
በዚሁ መካከል በ1958 ዓ.ም የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ምክትል አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል፡፡ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ምክትል አስተዳዳሪ ሆነው እንኳን በበጎ ፈቃደኝነት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም እየተመላለሱ ያስተምሩ ነበር፡፡ በኋላም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ወደ እንግሊዝ ሀገር ኦክስፎርድ ኦስሄትሮፕ የሚባል የካቶሊክ ኮሌጅ በ1961 ዓ.ም ተልከው በእንግሊዝ ሀገር ለአራት ዓመታት ትምህርታቸውን ተከታትለው (Bachelor of Divinity in Basic Philosophy Super mental and Developmental Psychology) ዲግሪ ተቀብለው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ከሀገርና ከቤተክርስቲያን የተቀበሉትን ታላቅ አደራ አክብረው ሀገራቸውን ለማገልገል በውጭ ሀገር የቀሰሙትን ሥልጣኔና ልምድ ለሀገራቸው የሚያውሉ ምሁራን በርካታ ናቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ካፈራቻቸው ሊቃውንት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በምዕራቡ ዓለም በትምህርት ቆይታቸው በትምህርትና በልምድ ያካበቱትን ዕውቀት በተግባር ላይ ለማዋል የቻሉ ምሁር ናቸው፡፡ በዚህም መነሻ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ፣ የሰበታ ቤተ ደናግል የበላይ ኀላፊና የቦርድ አባል ሆነው አገልግለዋል፡፡ በባሕል ሚኒስቴርም በቋንቋ ጥናት አካዳሚ ውስጥ መርሐ ልሳን ተብሎ በሚታወቀው ክፍል በመምህርነት ሠርተዋል፡፡
በተፈሪ መኰንን ት/ቤት ውስጥ ከውጭ ሀገር በልዩ ልዩ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኢየሱሳውያን ያስተምሩ ስለነበር ብዙ ጊዜ የሃይማኖት ግጭት ይፈጠር ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ተማሪዎች በመንፈሳዊ ዕውቀታቸው ጠንካሮች ስለነበሩ በሚያቀርቡት ጥያቄ በተማሪዎቹና በመምህራን መካካልም በየጊዜው ግጭት ይፈጠራል፡፡ ዐፄ ኃይለ ሥላሴም ጉዳዩን ሲያጣሩ የግብረ ገብነት መምህር እንደሌላቸው በተማሪዎቹ ስለተነገራቸው በአባ ሐና አቅራቢነት በዚያን ጊዜ ስማቸው አባ መዐዛ ቅዱሳን ወደ ጃንሆይ ቀርበው በግብረ ገብ መምህርነት እንዲቀጠሩ ስለፈቀዱ ለተፈሪ መኮንን ት/ቤት የግብረ ገብ መምህር ሆነው ተቀጥረው ከ1949 ዓ.ም እስከ 1954ዓ.ም ድረስ በግብረ ገብነት አስተማሪነታቸው አገልግለዋል፡፡
ብፁዕነታቸው በተፈሪ መኮንን ት/ቤት እያስተማሩ የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም በተጓዳኝ በትምህርት ቤቱ ግብረ ገብ የሚያስተምሯቸውን ተማሪዎች ሰፋ ያለ የሃይማኖት ትምህርት የሚቀስሙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲሉ በምስካዬ ኅዙናን መድኃ ኔዓለም ገዳም ወጣቶችን ስለሃይማኖት ማስተማር ጀመሩ፡፡ የዚህ አገልግሎት ፍጻሜም አንጋፋውን የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት ለመመሥረት አብቅቶታል፡፡ ብፁዕነታቸውም የዚህ ሰንበት ት/ቤት ከመሥራቾቹ አባላት አንዱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በወቅቱ ለምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ቋሚ ሰባኬ ወንጌል በመሆንም አገልግለዋል፡፡
ቅድስት ቤተክርስቲያን በሬዲዮ ትምህርት በምታስተምርበት ወቅት፤ አባ መዐዛ ቅዱሳን (በኋላ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል) በርቱዕ አንደበታቸው በብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ “ማኅበራዊ ኑሮ በቤተክርስቲያን'' እና “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት” በተሰኙ አርእስተ ትምህርት ይሰጡ ነበር፡፡ ብፁዕነታቸው በሕይወት ዘመናቸው ካከናወኗቸው ተግባራት ለምእመናን በሬዲዮ ስብከተ ወንጌልን በማስተላለፍ የሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላቸው ይናገሩ ነበር፡፡
በአርሲ ሀገረ ስብከት ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በመሆን ለ33 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በአርሲ ሀገረ ስብከት ቆይታቸውም በምእመናን የሚወደዱና የሚከበሩ ታላቅ አባት ነበሩ፡፡ ወደ አርሲ ሀገረ ስብከት በመጡበት የመጀመሪያ ሳምንታት ውስጥ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያሉትን ዐበይት ችግሮች ካጠኑ በኋላ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ አንድም የወጣቶች እንቅስቃሴ የሚደረግበት አጥቢያ አለመኖሩንና ሰንበት ት/ቤቶችም የተዘጉና ወጣቶችም በቤተክርስቲያን አካባቢ እንዳይታዩና ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር ይደረግባቸው እንደነበረ ካወቁ በኋላ በማለት አቋማቸውን በአደባባይ ከመግለጻቸውም በላይ በዘመኑ በሥልጣን ላይ ከነበሩት የደርግ ሹማምንት ፊት ለፊት በመጋፈጥ ልጆቻቸውን ከጥቃት ታድገዋል፤ ተቋርጦ የነበረው የሰንበት ትምህርት ቤት እንዲቀጥል አድርገዋል፡፡
ብፁዕነታቸው የነገይቱ ቤተክርስቲያን ተረካቢ ወጣቶች መሆናቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ስለሆነ በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩ አድርገዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ወደ አርሲ ሀገረ ስብከት ተመድበው ሲመጡ የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር 117 (አንድ መቶ አሥራ ሰባት) ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሳቸው በሕይወት በነበሩባቸው ዘመናት ከ300 (ሦስት መቶ) በላይ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን በማስከተል ምእመናን በርቀት ምክንያት ሳይንገላቱ በአቅራቢያቸው ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከማድረጋቸውም በላይ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የይዞታ ማረጋገጫ እንዲያገኙ አድርገዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዕረፍት ምክንያት ከነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ተመርጠው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ሆነው እስከተሾሙበት የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክነት ቅድስት ቤተክርስቲያን በመምራት አባታዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ልክ በዛሬዋ ቀን ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ዐርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም በደብር ቅዱስ ደብረ መዓዛ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ተፈጽሟል፡፡
የብፁዕ አባታችን በረከታቸው ይደርብን፡፡
@EotcLibilery