⚡️Motivation
አንድ ዓሣ አጥማጅ ገና ሳይነጋ በጠዋቱ ወደባህር ዳርቻ ሄደ ነገርግን ይህ ሰው የደረሰበት ሰዓት ጨለማ ነበር በወቅቱም ለሥራው ስላልተመቸው እስኪነጋ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ጀመረ ከባህር ዳርቻውም አጠገብ በድንጋይ ጠጠሮች የተሞላ ጆንያ አጋጠመው።
🌚ዓሣ አጥማጁም ከጆንያው ውስጥ ያለውን አንድ ጠጠር አውጥቶ ወደባህሩ ሲወረውረው እንቦጭ የሚል ድምፅ ሰማ። ይህም ድምፅ ስላስደስተው ወድያውኑ ሌሎች ጠጠሮች በየተራ እየወረወረ እንቦጭ እንቦጭ እየደረገ እየተደሰተ መወርወሩን ቀጠለ…
ይህ ዓሣ አጥማጅ በጆንያ ውስጥ የነበሩትን ጠጠሮች ወርውሮ አንዲት ጠጠር ብቻ በቀረው ሰዓት የብርሃን ወገግታ መምጣቱን አስተዋለ።
አጥማጁም የያዛውን ጠጠር ለመወርወር ከመቀመጫው ብድግ ሲል በእጁ የያዛውን ጠጠር በደንብ አገላብጡ ተመለከተ በድንጋጤም ሲያስተውለው ጠጠር ሳይሆን አልማዝ(💎) መሆኑን ተረዳ።
ዓሣ አጥማጁም በንዴት ሲቃ ተናነቀው ምክንያቱም እስኪነጋ ድረስ ሲወረውር የነበረው በጆንያ ሙሉ ጠጠር ሳይሆን አልማዝ መሆኑን አስተዋል።
ብዙ ሰዎች በህይወታቸው እንዲህ ናቸው። በእጃቸው ያለው ጊዜ አልማዝ መሆኑን ሳይረዱ እንቦጭ እንቦጭ የሚል ድምፅ ለመስማት ሲሉ ጊዜያቸውን በእንቅልፍ፣ በምንም፣ በፊልም፣ በማህበራዊ ድህረ-ገፅ፣ በወሬ፣ በክርክር እና በብስጭት ወደ ማይመልሰው ባህር ይወረውሩታል ጥቂቶች እንደ ዓሣ አጥማጁ በመጨረሻ ሰዓት ጊዜያቸው አልማዝ እንደሆነ ሲረዱ አብዛኞቹ ግን ጊዜ ምንም እንዳልሆነ ሳያውቁ በዚያው ይበቃል።
የሰው ልጅ በምድር ላይ የተሰጠው ጊዜ ውስን ነው። ይህን ውስን ጊዜ በወቅቱና በሰዓቱ ካልተጠቀመበት እድሉ ላይመለስ ይወሰድበታል። ምንም ቢለፋ፣ ቢያለቅስ እና ቢፀፀት ተመልሶ አያገኘውም። ይልቁንም በጊዜው የዘራውን መልካም ይሁን ክፉ በጊዜው ያጭዳል።
For more, join us ☞︎︎︎
@Elshio_Academy
@Ethio_students_only