ስራውን ሰራ ወይስ ..?
በበርንማውዝ ሳለ የመልማዮች ክፍል ሀላፊ የነበረው የአሁኑ የክለባችን ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሪቻርድ ሂዩዝ በክለባችን ለ6 ወራት በድርሻው ይገኛል፤የአንድ የስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሰራተኛ ሀላፊነትም በዋነኝነት በክለቡ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ ዋነኛ ተዋናይ መሆኑ የተጨዋቾችን ኮንትራት በሚገባ በማስማማት ውል መፈራረምን እናም ሌሎች ጉዳዮች የሚሰሩት በሪቻርድ ሂዩዝ ሀላፊነት ነው !
ይሁንና ባሳለፍነው የክረምት የዝውውር መስኮት በማርቲን ዙቢሜንዲ ላይ የሙጥኝ ያለው ክለባችን ከጆርጂ ማማርዳሽቪሊ በስተቀር በተፈለገው ቦታ ላይ አስፈላጊ ተጨዋችን ሊያስፈርም አልቻለም፤ታድያ ሪቻርድ ሂዩዝ በመጀመሪያው እርምጃ ላይ ስኬታማ ነው ብሎ ለመናገር ያዳግታል !
ከዛም ደግሞ አሁን ላይ በክለባችን ሶስቱ ወሳኝ ተጨዋቾች ሳላህ ቫንዳይክና ትሬንት የኮንትራት ማራዘምያ ውል ጉዳይ ከረፈደ እንቅስቃሴ መጀመሩ ሳላህም በሚድያ ፊት እስከሚናገር ድረስ በተጨዋቹ ኮንትራት ጉዳይ ያዘገመ እርምጃን መውሰዱ ሌላ የሪቻርድ ሂዩዝ ስፖርቲንግ ዳይሬክተሮች ቦርድ አንዱ ድክመት ነው በተጨማሪም ትሬንት አርኖልድ በደሞዝ ጭማሪም ሊሆን ይችላል በኮንትራት ማራዘምያ ውሉ ላይ እንዲስማማ ለማድረግ አለመቻሉ የሪቻርድ ሂዩዝ ሌላኛው የነቀፌታ ምክንያት ነው።
አሁን ደግሞ የወርሀ ጥር የዝውውር መስኮት ሊጀመር 2 ቀናት ብቻ ከፊታችን ይገኛሉ እስካሁንም ድረስ ግን ወሳኞቹ ተጨዋቾቻችን የኮንትራት ማራዘምያ ውል ሊፈርሙ አልቻሉም በድጋሜም ደግሞ የትሬንት የመሸኘት ፍላጎትም መፍትሄ አልተበጀለትም ?
ታድያ ከመጪው የጥር የዝውውር መስኮት ምን እንጠብቅ .......?
@Ethioliverpool143