በቦረና ባለቤቱን ከዛፍ ጋር በማሰር በአሰቃቂ ሁኔታ የገረፈውና እንድትገረፍ ትዕዛዝ የሰጡት ሽማግሌዎች በእስራት ተቀጡ
በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ቦረና ዞን ወጨሬ ወረዳ የሽማግሌዎችን ትዕዛዝ አላከበረችም በማለት ከዛፍ ጋር በማሰር ድብደባ እንዲፈጸም ያደረጉ ግለሰቦች ባለቤቷን ጨምሮ በቁጥጥር ስር ውለው በእስራት መቀጣታቸው ተገልጿል ።
የምስራቅ ቦረና ዞን የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ኮማንደር በቃሉ በለጠ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደገለጹት ተከሳሽ እና የተገራፊዋ ባለቤት የሆነው1ኛ ተከሳሽ ገልገሎ፣ 2ተኛ ተከሳሽ ጃርሶ ቦሩ የሀገር ሽማግሌ 3ተኛ ተከሳሽ ጀርጀሮ ባሌ የሀገር ሽማግሌ 4ተኛ ኢፓ ጉልቻ የቀበሌው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም ድርጊቱን መፈጸማቸው ተረጋግጧል ።
በወቅቱ ሃዋሳ ሆስፒታል የህክምና ከትትል እየተደረገላት የነበረችው ተጎጂ ግለሰብ በደረሰባት ድብደባ የአካሏ ግራ ክፍል እና የራስ ቅሏ ተሰብሮ እንደነበረ በህክምና ማስረጃ መረጋገጥ መቻሉ ተጠቁሟል። በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲጣራባቸው ከነበሩ ስምንት ግለሰቦች መካካል ቅጣት አስተላልፈዋል የተባሉት ሽማግሌዎች በዋስ ተለቀው የነበረ ቢሆንም ባለቤቷ ግን በእስር ላይ ሆኖ ጉዳዩን ሲከታተል እንደነበረ እና ውሳኔ እንደተላለፈበት ተነግሯል።
ተጎጂዋ በትዳር 12 ዓመት ከባለቤቷ ጋር የቆየች ሲሆን የሶስት ልጆች እናት ናት። ባለቤቷ ለውትድርና ከቆየበት አራት ዓመታት በኋላ ወደ ቤቱ ሲመለስ በተደጋጋሚ ይደበድባት እና በመካከላቸው ግጭት ይፈጠር እንደነበረ እና ወደ ቤተሰቦቿ ትሄድ እንደነበረ ተረጋግጧል ።
ሽማግሌዎች ወደ ባለቤቷ እንደትመለስ በነገሯት ሰዓት ይገድለኛል በማለት አልመለስም በማለቷ የሽማግሌ ትዕዛዝ አላከበርሽም በሚል ታስራ እንድትገረፍ ትዕዛዝ በማስተላለፍ ዛፍ ላይ አስረው ልጇ እያለቀሰ እና ሰዎች በተሰበሰቡበት ድርጊቱ እንድተፈጸመባት ተረግጧል ።ለሳምንት ያህል ህክምና ሳታገኝ የቆየች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከቀናቶች በኋላ በኤረር እና በያቤሎ እንዲሁም በሃዋሳ ህክምና እንድትከታተል ተደርጓል።
ፖሊስ ገዳዩን በማጣራት ለዓቃቢ ህግ ያቀርባል ። ዓቃቢ ህግ ክስ በመመስረት መረጃ በማሰባሰብ በከባድ የሰው መግደል ሙከራ እና የአካል ማጉደል ወንጀል በሚል ክስ ይመሰርታል ። ክሱን የተመለከተው የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ገልገሎ አርዮ፣ 2ተኛ ተከሳሽ የሀገር ሽማግሌ ጃርሶ ቡሩ ላይ 6 ዓመት ከ4 ወር እስራት የተወሰነባቸው ሲሆን 3ተኛ ተከሳሽ ጃርጀሮ ባሌ ግለሰቧን በገመድ በማሰር ስትገረፍ ሰው እንዳይጠጋ በመከልከል ወንጀል 7 ዓመት ከ2 ወር እስራት ሲቀጣ 4ተኛ ኢባ ጉልቻ በ4 ዓመት ከ5 ወር እስራት እና 5ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን ኮማንደር በቃሉ በለጠ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
Via: ዳጉ_ጆርናል
@Ethionews433 @Ethionews433