ደቡብ ኮሪያ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 3ኛ ፕሬዝዳንት ቀየረች
የገንዘብ ሚኒስትሩ ቾይ ሳንግ ሞክ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል
በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የምትገኘው እስያዊቷ ሀገር ደቡብ ኮሪያ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 3 ፕሬዝዳንቶችን ቀይራለች፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዩል ምንም አይነት በቂ ምክንያት ሳይኖር የወታደራዊ አስተዳደር (ማርሻል ሎው) ማወጃቸውን ተከትሎ ከስልጣናቸው በጊዜያዊነት ወርደው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡
ይህን ተከትሎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃን ዳክ-ሶ በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል፡፡
ተጠባበቂ ፕሬዝዳንቱ የፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዩል ጉዳይን ለመመልከት በተቋቋመው ህግ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የዳኞች ስያሜ ላይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ነው ከስልጣናቸው ወርደው ምርመራ እንዲደረግባቸው ፓርላማው የወሰነው፡፡
በዚህም የፋይናንስ ሚኒስትሩ ቾይ ሳንግ ሞክ በ15 ቀናት ውስጥ ሶስተኛ ወደ መንበሩ የመጡ ፕሬዝዳንት ሆነው በጊዜያዊነት ተሹመዋል፡፡
የሃን ድንገተኛ ከስልጣን መነሳት በሀገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ እንዳያባብሰው ተሰግቷል፤ ኢኮኖሚውም የስጋቱ ተካፋይ ነው፡፡
ከ2008 የፋይናንስ ቀውስ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ዎን ከዶላር አንጻር የመገዛት አቅሙ በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል፡፡
ሬውተርስ የፋይናንስ ሚኒስትሩ ቾይ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሚመራው ፓርላማ ጋር ከተጋጩ የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች እጣ ሊያጋጥማቸው ይችላል ብሏል፡፡
ከሹመቱ በኋላ ከብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፣ ከጦር መሪዎች እና ቁልፍ ባለስልጣናት ጋር የተወያዩት አዲሱ ፕሬዝዳንት የፍርድ ውሳኔው እስኪታወቅ ድረስ ሀገሪቱን ለማረጋገት እንደሚጥሩ ተናግረዋል፡፡
በትላንትናው እለት የዮን ሱክ ዩል የፍርድ ሂደት የተጀመረ ሲሆን ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቱ በቀጣዮቹ 180 ቀናት ፕሬዝዳንቱ ወደ ስልጣን ይመለሱ ወይስ በቋሚነት ከስልጣናቸው ይነሱ የሚለው ጉዳይ ላይ ፍርድ ይሰጣል፡፡
ፍርድ ቤቱ የህግ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ፕሬዝዳንቱ በቋሚነት ከስልጣናቸው እንዲነሱ ከወሰነ ሀገሪቱ በ60 ቀናት ውስጥ ምርጫ የምታደርግ ይሆናል፡፡
ያልተጠበቀው የወታደራዊ አስተዳደር አዋጅ ያመጣው የፖለቲካ ውዥንብር በእስያ አራተኛው ትልቁ ኢኮኖሚ ሀገር ውስጥ አስደንጋጭ ማዕበልን የፈጠረ ሆኗል፡፡
ይህም ቻይናን፣ ሩሲያን እና ሰሜን ኮሪያን ለመቃወም በሚደረገው ጥረት ደቡብ ኮሪያን ቁልፍ አጋር አድርገው በሚመለከቱ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገሮች ላይ ስጋት ፈጥሯል።
@Ethionews433 @Ethionews433