ጆ ባይደን ከ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር በመውጣታቸው እንደሚጸጸቱ ተናገሩ
ባይደን በሰኔ ወር በተካሄደው የምርጫ ክርክር ላይ ባሳዩት አቋም በደረሰባቸው ጫና ከእጩነት ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል
ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከ2024 ምርጫ እጩነት ራሳቸውን በማግለላቸው እንደሚጸጸቱ መናገራቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል፡፡
ባይደን በአስተዳደራቸው ውስጥ የፖሊሲ ውሳኔዎችን እና የተሳሳቱ እርምጃዎች እንደነበሩ ገልጸው፤ ከእጩነት ለመልቀቅ የገፏቸው ፈተናዎች ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ጭምርም በውድድሩ ውስጥ መቆየት እንደነበረባቸው እንደሚያምኑ ጋዜጣው የኋይት ሀውስ ምንጮችን ጠቅሶ አስነብቧል፡፡
ይህ የፕሬዝዳንቱ ጸጸት የተሰማው በቅርብ ጊዜ ከግለሰቦች ጋር ባደረጓቸው የግል ውውይቶች ውስጥ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
በተጨማሪ የፍትህ ሚኒስቴር ትራምፕን ለመክሰስ ባሳየው መዘግየት ሜሪክ ጋርላንድን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አድርጎ በመምረጣቸው እንደሚጸጸቱ ተናግረዋል ነው የተባለው፡፡
እንደ ምንጮች ገለጻ፣ የፍትህ ሚኒስቴሩ የ2020 ምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ የተደረጉ ሙከራዎች ፣ ሚስጥራዊ ሰነዶችን አላግባብ መጠቀምን ጨምሮ በትራምፕ ላይ በቀረቡ ክሶች ላይ ፈጣን እርምጃ ቢወስዱ ኖሮ በሪፐብሊካኑ ተቀናቃኛቸው ላይ ከምርጫው በፊት ፖለቲካዊ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ብለው ያምናሉ።
በ2021 ሪፐብሊካኑን አወዛጋቢ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማሸነፍ ወደ ስልጣን የመጡት ጆ ባይደን በቀጥታ ስርጭት በተላለፈ በአንድ የምርጫ ክርክር አጠቃላይ አስተዳደራዊ አቅማቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡
በሰኔ ወር የተካሄደው የምርጫ ክርክር በተሳናባቹ ፕሬዝዳንት የእድሜ ሁኔታ እና የግንዛቤ ችሎታ ላይ ትችት እና ጥያቄን ማስከተሉ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም ባይደን ከእጩነት ራሳቸውን በማግለል ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስ የእርሳቸውን ስፍራ እንዲተኩ ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡
የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ለመሆን አልመው በባይደን እግር በመተካት ሰፊ ቅስቀሳ እና የሚዲያ ዘመቻ ያደረጉት ካማላ ሃሪስ ከትራምፕ ጋር ባደረጉት የምርጫ ክርክር ማሸነፍ ቢችሉም ምርጫውን ግን በድል መወጣት አልቻሉም፡፡
47ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን የሚያስችላቸውን ድምጽ በማግኝት በሰፊ ልዩነት ያሸነፉት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤት ለመመለስ በአለ ሲመታቸውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡[አል አይን]
@Ethionews433 @Ethionews433