ዋሽግተን-ትራምፕ በBRICS አባል ሐገራት ሸቀጦች ላይ 100% የግብር ጭማሪ ለማድረግ ዛቱ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የBRICS አባል ሐገራት የአሜሪካዉን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለዩናይትድ ስቴትስ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ለማድረግ ዛቱ።ትራምፕ Truth Social በተባለዉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴያቸዉ ባሠራጩት ማስጠንቀቂያ እንዳሉት የBRICS አባል ሐገራት ከዶላር ለማፈንገጥ ማሰባቸዉ «ማብቃት አለበት።» ትራምፕ የBRICS አባል መንግሥታትን ለዩናይትድ ስቴትስ «የጠላትነት አዝማሚያ» የሚታይባቸዉ በማለት ወርፈዋቸዋልም።እነዚሕ ሐገራት፣ ትራምፕ «ግዙፍ» ያሉትን የአሜሪካን ዶላር ለመተካት አዲስ ገዘብ ካሳተሙ ወይም በሌላ ገንዘብ ለመጠቀም ከወሰኑ ከአሜሪካ ገበያ መሰናበት አለባቸዉ።ትራምፕ እንደሚሉት መስተዳድራቸዉ ወደ አሜሪካ በሚገቡ የየሐገራቱ ሸቀጦች ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ያደርጋል።ቡድኑን በመሠረቱት አምስት ሐገራት ስም የመጀመሪያ ፊደላት ተገጣጥሞ BRICS ተብሎ የሚጠራዉ ቡድን ባሁኑ ወቅት 10 አባል መንግስታትን ያስተናብራል። BRICS በኢንዲስትሪ የበለፀጉትን 6 ምዕራባዉያን ሐገራትና ጃፓንን የሚያስተናብረዉ ቡድን 7 የሚያደርሰዉን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያለመ ነዉ። ሩሲያና ቻይናን የመሳሰሉ የBRICS ጠንካራ አባላትና መሥራቾች የአሜሪካ ዶላር በዓለም ገበያ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና አጥብቀዉ ይተቻሉ።ማሕበራቸዉ አማራጭ መገበያያ እንደሚያስፈልገዉም ያሳስባሉ።የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ግን ዶላርን መተካት «አስደናቂ» ከሚሉት ከአሜሪካ ምጣኔ ሐብት መሰናበት ነዉ።[DW]
@Ethionews433 @Ethionews433