የጀርመን ምክር ቤት የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ ደንብን ዉድቅ አደረገ
የጀርመን ምክር ቤት በሐገሪቱ የሚኖሩና ወደ ሐገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን ለመገደብ የተረቀቀዉን አዲስ ደንብ ዛሬ ዉድቅ አደረገዉ።ተቃዋሚዎቹ ወግ አጥባቂ እትማማች ፓርቲዎች የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ሕብረት (CDU)ና የክርስቲያን ሶሻል ሕብረት (CSU) ያረቀቁት ደንብ የሐገሪቱን ፖለቲከኞች ሲያሟግት ነበር።ረቂቁ፣ ጀርመን የሚኖሩ ስደተኞች በየትዉልድ ሐገራቸዉ ያሉ የቅርብ ቤተ-ሰቦቻቸዉን አባላት እንዳያስመጡ የሚያግድ፣ ሕገ-ወጥ የሚባሉ ስደተኞችን ወደየመጡበት ለመመለስ ፖሊስ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ፣ ወደየመጡበትን በቀላሉ የመመለስ መብት እንዲሰጠዉ የሚጠይቅ ነበር።የዋናዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የCDU መሪ ፍሬድሪሽ ሜርስ ረቂቁን በቀኝ ፅንፈኛዉ AFD ፓርቲ ድጋፍ ሕግ ለማድረግ መጣራቸዉ ከሕዝብም፣ ከግራ፣ ከመሐልና ለዘብተኛ ፖለቲከኞችም ከፍተኛ ቁጣና ተቃዉሞ ቀስቅሶ ነበር።የሐገሪቱ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት (ቡንደስ ታግ) ዛሬ ባደረገዉ ስብሰባ ረቂቁን በ338 የድጋፍና በ350 የተቃዉሞ ድምፅ ዉድቅ አድርጎታል።(DW)
@Ethionews433 @Ethionews433