በቁጥጥር ስር የዋለው የካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት
ለተከታታይ ሶስት ሳምንት በሰደድ እሳት ስትታመስ በከረመችው ካሊፎርንያ እጅግ አውዳሚ የነበሩት የኢተን እና የፓሊሳዴስ እሳቶች ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።
በደቡብ ካሊፎርኒያ የተነሱት እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ቤት አልባ ያደረጉት ሁለቱ አውዳሚ የእሳት ቃጠሎዎች ከ24 ቀናት አድካሚ የማጥፋት ዘመቻ በኋላ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የካሊፎርኒያ የደንና የእሳት አደጋ መከላከያ ዲፓርትመንት የተገለጸው ።
የ12 ሰዎች ህይወት የቀጠፈው የፓሊሳዴስ እሳት 23,448 ሄክታር ሲያቃጥል ከ6,800 በላይ ህንጻዎችንና ቤቶችን ወደ አመድነት ቀይሯል ።
በተመሳሳይ የኢተን እሳት በአልታዴና እና ፓሳዴና ውስጥ 14,021 ሄክታር መሬት አውድሞ የ17 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
በካሊፎርንያ እና በአከባቢው ከተቀሰቀሱ እሳቶች እጅግ አውዳሚ የተባሉት የኢተን እና የፓሊሳዴስ እሳቶች በአጠቃላይ ከ250 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራን በኢኮኖሚ ላይ ማድረሳቸውም የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ዘገባው የኤን ቢ ሲ ኒውስ ነው
@Ethionews433 @Ethionews433