ነፍሰጡር ሴትን በመምታት ፅንስ እንዲጨናገፍ ያደረገችዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዎ ወረዳ ዉስጥ ነፍሰጡር ሴትን በመምታት ፅንስ እንዲጨናገፍ ያደረገቸዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቷን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል።
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ተከሳሽ ስንቄ ተስፋዬ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ከግል ተበዳይ ቅድስት ሁንዴ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በተነሳዉ ድብድብ ፅንስ እንዲጨናገፍ ምክንያት መሆኗ ተገልጿል ።ተበዳይ ቅድስት ሁንዴ የ4 ወር ነፍሰ ጡር ስትሆን ከተከሳሽ ስንቄ ጋር በጉርብትና እየኖሩ ሳለ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ፀብ ተነስቶ ተከሳሻ የተበዳይን ሆድ በመርገጥ መሬት ላይ ከጣለቻት በኋላ ሁለት ጊዜ ሆዷን በመርገጥ ፅንሱ እንዲጨናገፍ ማድረጓ ተገልጿል ።
የግል ተበዳይ በደረሰባት ድብደባ ከፍተኛ ደም የፈሰሳት ሲሆን የአከባቢው ሰዎች ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል በመዉሰድ ህክምና እንድታገኝ በማድረጋቸዉ ህይወቷ መትረፉ ተገልጿል። ፖሊስ ጥቆማ እንደደረሰዉ ተከሳሿን በቁጥጥር ስር በመዋል የምርመራ መዝገቡን በተከሳሿ ቃል ፣በሰዉና በህክምና ማስረጃ በማደራጀት ለአቃቤ ህግ ልኳል ።
አቃቤ ህግም በወንጀል ህግ ቁጥር 540 እና 543 በፅንስ ላይ በሚደረግ ወንጀል ፅንስን ማስወረድ በሚል ክስ መስርቶባታል ። ክሱ የቀረበለት የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ተከሳሿ በፈፀመችዉ ድርጊት ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በአራት ዓመት እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ትግሉ ጨምረዉ ለብስራት ተናግረዋል፡፡
በመባ ወርቅነህ
@Ethionews433 @Ethionews433