የሩሲያ ጦር ግስጋሴ በታሪካዊቷ ኮንስታንቲኖፕል
፡፡።።።፡፡።።።፡፡።።።።።፡፡።።።፡፡።።።
የሩሲያ ጦር የዩክሬኗን ኮንስታንቲኖፕል መንደር መቆጣጠሩን አሳወቀ፡፡
የዩክሬን ጦር ከኮንስታንቲኖፕል ተጠራርጎ መውጣቱን ይፋ ያደረገችው ሞስኮ ወታደሮቼ ወደፊት እየገሰገሱ ነው ብላለች፡፡
በዶንባስ (ሉሃንስክ እና ዶኔትስክ) ግዛት የምትገኘው ኮንስታንቲኖፕል በባይዛንታይን አገዛዝ ወቅት የነበረን ስያሜ ከታሪክ እና ከእምነት ጋር በማስተሳሰር ዛሬም መጠሪያዋ አድርጋ ትጠቀማለች፡፡
"የቱርኳ ኮንስታንቲኖፕል በ1922 ዓ.ም ወደ አሁኗ ኢስታንቡል ስያሜዋ መቀየሩ ይታወሳል"።
ለዚህም ነው የሩሲያ ጦር አሁን ላይ የዩክሬኗን ኮንስታንቲኖፕል መቆጣጠሩን ከታሪክ አንጻርም ትልቅ ድል አድርጎ የሚቆጥረው፡፡
ሞስኮ ወታደሮቿ በአካባቢው ላይ የሩሲያን ባንዲራ ሲሰቅሉ የሚያሳይ ምስል በቴሌ ግራም ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ አጋርታለች።
እንደ አር ቲ ዘገባ በዚህ ግንባር በውጊያ ላይ የነበሩ ከ50 በላይ ወታደሮቿን ዩክሬን አታለች፡፡
አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ እና የሳተላይት አሊያም የመረጃ ልውውጥ ማቆሟ ሩሲያ አጋጣሚውን እየተጠቀመችበት እንደሆነ ያሳያል ተብሏል።
ላለፉት 24 ሰዓታት 1,300 የጦር ዓባላቷን ዩክሬን ከማጣቷም ባሻገር አሜሪካ ሰራሽ ሂማርስ የሮኬት ማስወንጨፊያ ስርዓትን ጨምሮ በርካታ ቁልፍ የጦር መሳሪያዎች ወድመዋል ብሏል የሩሲያ ጦር፡፡
ዩክሬን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት በጉዳዩ ላይ ያለችው ነገር የለም ሲል የዘገበው አር ቲ ነው፡፡
@Ethionews433 @Ethionews433