እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሦስት ዘመናዊ የመምህራን መኖሪያ አፓርትመንቶችን አስመርቋል
ዩኒቨርሲቲው ሦስት አፓትርትመንቶችን በ677 ሚሊዮን ብር ወጭ አስገንብቶ ለመምህራኑ አስረክቧል፡፡ መኖሪያ ቤቶቹ ባለ አንድ፣ ባለ ሁለት እና ባለሦስት መኝታ ዘመናዊ ቤቶች መሆናቸውን የገለፁት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) ፤ መኖሪያ ቤቶቹ ከ200 በላይ የተቋሙ መምህራንን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
መኖሪያ ቤቶቹ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ዘመናዊ ሻወርና ሽንት ቤት፣ ማዕከላዊ የቴሌቪዥን እና የዲሽ መቆጣጠሪያ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ፣ ዘመናዊ የፍሳሽ አገልግሎት ማስወገጃ እና የውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መንገዶች እንደተሟላላቸውም አብራርተዋል፡፡
በቀጣይ የተጨማሪ ሁለት አፓርትመንቶች ግንባታ ለማከናወን እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የጤና ኮሌጅን ለመገንባት ከከተማ አስተዳደሩ ቦታ መጠየቁንም አንስተዋል፡፡
@Ethiopian_Digital_Library