ከነ መሀይምነቴ አስመርቆኛል በሚል ትምህርት ቤቷን የከሰሰችው ተማሪ
አሌይሻ ኦርቲዝ የተባለችው የ19 ዓመት ተማሪ ከአንድ ዓመት በፊት ነበር የሁለተኛ ደረጃ ትምህረቷን በከፍተኛ ውጤት አጠናቃለች የተባለችው፡፡ በአሜሪካዋ ኮኔክቲከት ግዛት ባለ ትምህርት ቤት ትምህርቷን የተከታተለችው ይህች ተማሪ፤ ከፍተኛ ውጤት ማምጣቷን ተከትሎ የስኮላርሽፕ እድል ተመቻችቶላት በመማር ላይ ነበረች፡፡
ይሁንና የተማሪ አሌይሻ መጻፍ፣ ማንበብ እና ተያያዥ ክህሎት አብረዋት ከሚማሩት ተማሪዎች በብዙ እጥፍ ወደኋላ እንደቀረች ትረዳለች፡፡ ከክፍል ጓደኞቿ ጋር እኩል መጓዝ ያልቻለችው ተማሪዋ፤ ትምህርቷን ለማቋረጥ መገደዷን ኦዲቲ ሴንተራል ዘግቧል፡፡
“እኔ መሀይም ሆኜ ሳለ ትምህርት ቤቴ ግን በከፍተኛ ማዕረግ ብሎ ማስመረቁ ትክክል አይደለም” ያለችው አሌይሻ የቀድሞ ትምህርት ቤቷ ላይ ክስ መመስረቷን ተዘግቧል፡፡ ተማሪዋ አሁን ላይ ያላት እውቀት አንደኛ ክፍል ካለ ተማሪ ጋር ተመሳሳይ ነው የተባለ ሲሆን እርሳስ መያዝ እና የተወሰኑ ቃላትን ብቻ ማንበብ ትችላለችም ተብሏል፡፡
የትምህርት ቤቱ አማራሮች በግዴለሽነት በእኔ ላይ ላደረጉት ጥፋት መቀጣት አለባቸው የምትለው ተማሪዋ ሌሎች ተማሪዎች መሰል ጉዳት እንዳይደርስባቸው በሚል ክስ መመስረቷ ተገልጿል፡፡
@Ethiopian_Digital_Library