የአውሮፓ ዩኒቨርስቲዎች አማርኛ ማስተማር ከጀመሩ 100 ዓመት አልፏቸዋል
ኔፕልስ፣ ፓሪስ እና ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲዎች አማርኛ ማስተማር ከጀመሩ 100 ዓመት አልፏቸዋል። በኔፕልስ አማርኛን ማስተማር የጀመሩት አፈወርቅ ገብረየሱስ ናቸው። ይህ ማለት በ1890ዎቹ መሆኑ ነው። ጥንት በዓድዋ ዘመን።
አማርኛ በጀርመን፣ ሐምቡርግም ዩኒቨርስቲም ይሰጣል። እዚያም ድሮ ነው የተጀመረው። ዛሬም ድረስ አለ፤ ለዚያውም ሳይቋረጥ። ይቆጠር ከተባለ 105 ዓመት ሆኖታል፣ ዘንድሮ። የመጀመሪያው መምህር ወልደማሪያም ደስታ የሚባሉ ሰው ናቸው። በ1909 ከአንኮበር-ሐምቡርግ ሄደው አምስት ዓመት አስተምረዋል።
በፖላንድ አማርኛን ማስተማር የጀመሩት ፕሮፌሰር ስቴፋን ስትሬልሲን ናቸው።የዛሬ 75 ዓመት ገደማ። እሳቸው አማርኛን ያጠኑት በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ነው። ቋንቋውን የተማሩት ደግሞ በፈረንሳይ ነው። እኚህ ሰው ከባድ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ ይባላል።
BBC Amharic
@Ethiopian_Digital_Library